03 -19 -2022
ኢዛና ኦስካር “Ezana Oscar” ከ አዲስ አበባ
500 ቀናት ለተጋሩ:-
ያለፉት 500 ቀናት ለተጋሩ እጅግ ከባድና በዓለም ላይ አሉ የተባሉና የሚባሉ ግፎች፣በደሎች፣ስቃዮች፣ ግድያዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣የጅምላ እስሮች፣ የተጋሩ ክቡር አስክሬን የተቃጠለበት፣ዝርፊያዎች፣ የስም ማጥፋቶች፣ መገለሎች፣ ኢኮኖሚያዊ ማጥቃት፣ ፓለቲካዊ ምገለሎች፣ የጦር ወንጀሎች፣የሚዲያ ክልከላዎችና ዓፈናዎች፣ለቁጥር የሚያታክቱ ክህደቶች – – – ወዘተ በወራሪዎች፣በአረመኔዎች፣ በአራዊቶች እና በሰብ በላ የፖለቲካ ፉንጋዎች፣ የተለያዩ ሰዎች የውስጥና የውጭ ኀይሎች የዘር ማጥፋት፣የጦር ወንጀልና ሰብአዊ ፍጡር ላይ እንኳንስ አይደረጉም የሚባሉ አይታሰቡም የሚባሉ በደሎች ሁሉ የተፈጸሙበት ጊዜያት ናቸው።
ይህን ሁሉ በደልና ግፍ ተፈጽሞበት በፅናት ለክብሩ፣ ለማንነቱ፣ ለመብቱ፣ ለሉዓላዊነት፣ለሰብአዊነቱ፣ ለፍትሃዊነቱ – – – እየታገለ ያለው የትግራይ ሕዝብ ተጋድሎውና ፅናቱ ከእንቁ ወታደራዊ እና ፓለቲካዊ መሪዎቹ ጋር ሆኖ የፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለው ታሪክ እጅግ እፅብ ድንቅ የተጋሩነት መለያ ሆኖ ቀጥሏል።
ያለፉት 500 ቀናት የሰው ልጅ ከክፋት። ከበደልና ከግፍ አንፃር አይፈፅመውም የሚባል ነገር እንደሌለ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለው ተግባር ትልቅ ማሳያ ሆኗል።
በዚህም የተነሳ:-
- የ’ኢትዮጵያ’ የሃይማኖት ተቋማት ከፈጣሪ ይልቅ ለምድራዊ ዲያቢሎሳዊ ገዥዎች የቀረቡ መሆናቸው፣
- የ’ኢትዮጵያ’ እና የ’ኤርትራ’ ምሁራን፣ ልሂቃን፣ activists፣ civic associations; media’s – – – etc በአብዛኛው ከሰብአዊነት ይልቅ ለአራዊትነት የቀረቡ መሆናቸውን፣
- አብዛኛዎቹ የ’ኢትዮጵያ’ እና የ’ኤርትራ’ ሕዝቦች ከነጻነት ይልቅ ለባርነት፣ ከሉኣላዊነት ይልቅ ለግዞት፣ ከመብት ይልቅ ዝምታ፣ ከክብረት ይልቅ ለውርደት፣ ለሰብዓዊነት መስዋዕትነት ከመክፈል ይልቅ ለአራዊትነት መስዋዕት መሆንን መምረጣቸውን፣
- በዓለም ላይ ምንም እንኳ ሐቅ፣መርህ፣ እሴት፣principle፣ ክብር – – – ወዘተ ቢኖርህ ሐይል ከሌለህ ማንም ሊሰማህ እንደማይችል፣ጉርብትና ሰብአዊነት በሐይል ድል እንደሚነሱ፣ካንተ ውጪ ላንተ ማንም አካል ያንተን ያክል ሊሆን እንደማይችል፣
- በትግራይ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን ግፍ፣በደልና ስቃይ የማያውቅ የለም፣ነገር ግን ከግፉ፣ ከበደሉና ከስቃዮ ፈፀሚዎች በላይ የፈፃሚዎቹ ደጋፊዎች ብዙ ናቸው። በዝምታ የሚተባበሩትና የተባበሩት እጅግ ብዙ መሆናቸው፣
- የአለም አቀፍ ድርጅቶች United Nation, African Union, European Union – – – etc በ”concern”፣ ከ”ያሳስባል” የዘለለ ፋይዳ ያለው ለውጥ ለማምጣት የኤሊ ጉዟቸው እጅግ ኋላ ቀርና አርፋጅ መሆኑንን – ለማወቅና ውሳኔ ለማስተላለፍ ከሚወስድባቸው ሰፊ ጊዜ በላይ ውሳኔውን ተፈጻሚ ለማድረግ እንደሚወስድባቸው፣enforcement mechanisms ብለው የሚያስቀምጡት በአብዛኛው ለዘር አጥፊዎችና ለጦር ወንጀል ፈጻሚዎች space & bargain power ስለመስጠቱ፣
- የተጋሩ ለማንነታቸው እና ለሁለንተናዊ ክብራቸው ያደረጉትና በማድረግ ላይ ያሉት ትግል ከአለም አቀፍ አጀንዳዎች አንዱ መሆኑንን፣ አሳይቶናል።
የትግራይን ሕዝብ ያለበትን ሁኔታ መረዳት ያቃታቸው ነውረኞች እና ተባባሪዎቻቸው 3 ቀን መብራት እና ባንክ ቢዘጋባቸው ሙሉ ጨለማ የሚሆንባቸው እንከፎች ናቸው።
የትግራይ ሕዝብ ግን ለ500 ቀናት መንገድ ተዘግቶበት፣ተወሮ፣መሰረታዊ አገልግሎቶች መብራት፣ስልክ፣ internet, banks, education, health centre, insurances, የንግድ መስመር፣ በጀት – – – ወዘተ በአራዊት ስርአቶች ተከልክሎ survive ማድረግ ብቻ ሳይሆን ጠላቶቹን ድል የነሳና በመንሳት ላይ ያለ ድንቅ ፈጣሪ ከርሱ ጋር የሆነ ኃያል ሕዝብ ነው።
የትግራይ ሕዝብ እንኳንስ ድል አድርጎ ለ500 ቀናት survive ማድረጉ ታላቅ ተጋድሎና ተዓምር ነው።
ትግራይ ትስዕር!
ትግራይ ትዕወት!
[…] ምንጭ፡ AigaNews […]