የ ዮሃንስ ታማኝ … ውድ የአገሩ አገልጋይ

ራእሲ ኣሉላ ኣባ ነጋ … ወዲ እንግዳ ቁቢ

ናይ ትግራይ ተንቤን … ዙቁል ወርቂ ፍራይ

ፍትህን የማያዛባ … ሁሉንም በአንድ አይን የሚያይ  

የጥቁራች ኩራት …የአፍሪካው ጄኔራል  

የኢትዮጵያን ስም ያስጠራ … በመላው አለም ላይ  

የጉራዕና ጉንደት፣ የኩፊት የዶጋአሊ

የሰሀጢ አምባላጀ፣ የመቐለ ዓድዋ … ድል ሀሌም አብሳሪ  

ማንም የማይክደው … የተዋጣለት ሰመ ጥሩ የጦር መሪ …

ለወዳጆቹ መሬት … ለጠላቶቸ እሬት

ራስ ኡሉላ አባነጋ … በል ይሄንን ጉድ ስማ  

አንተ … ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን ጠብቀህ … ከመሬት ስትገባ

ኢትዮጵያ እያለ የሚሰብክ መሪ … ከሀዲ ባንዳ ነግሷል

መች መንገስ ብቻ … ጦርነትና መዐት ግፍና ረሀብ …

ባዕድ አገር ጋብዞ … ትግራይን አውድሟል

መች ይሄ ብቻ … ኧረ መች ይሄ ብቻ

በኩራት በእብሪት … በንቀት በዝቅጠት

ትግራይን በሻሻ … አደርኳት ብሎም ለአለም አውጇል ።

ሰማህ ውይ አሉላ ?

የኢትዮጵያ መዐረግ … የጅግኖች መለኪያ

ይሄንን ብነግርህ … ልብህ ይሰበራል

ከጣሊያን ግፍ የሚያስንቅ … ትግራይ ምድር ላይ ወርዷል

ከሰሜን ጫፍ … እስከ ደቡብ ጫፍ ኢትዮጵያ …

ከምዕራብ ጫፍ … እስከ ምስራቅ ጫፍ ኢትዮጵያ …

ሁሉም አንድ ሆነው … ትግራይን ወግተዋል …

… ትግራይን አውድመዋል

ቄስና ጻጻሱ ሼክና ፓስትሩም … ለእምነት ሳይግዙ

… ጦርነቱን ባርከው … ዝመት ክተት ብለዋል  

ኣሉላ … ንገረው ለባሻይ ኣውኣሎም

ንገራቸው … ለሁሉም

ትግራይ የትውልድ አገርህ … እጅጉን ቆስላ ደም ታነባለች  

ህዝቧ ተፈናቅሎ … የሚበላው አጥቶ ስደት ላይ ይገኛል  

ምኑን ትቼ … ምኑንስ ልንገርህ …

ልጆችህ በነፍሳቸው … በእሳት ተቃጥለዋል

ሴቶች ልጆችህ …  በመንጋ ተደፍረዋል

ስማህ ወይ አሉላ?

ግን ብዙም ያን ያህል … አደራ አንዳትቆጭ …  

የልጅ ልጅ ልጅ ልጆችህም … እንቢ ለባርነት

እንቢ ለፋሺስቶች … እንቢ ለባንዳዎች ብለው

ፊት ለፊት ጦር ገጥመው …  ለእናት ትግራይ ሲሉ

… የጀግኖች ሞት ሞተዋል ።  

ራዕሲ ኣሉላ ኣባ ነጋ .. ወዲ እንግዳ ቁቢ …

ምትነሳ ከሆነ … ሳትዘገይ ተነሳ

ትግራይ ተሸራርፋ …  ትግራይ ተቆራርሳ

ትግራይ በደላሎች … ተሽጣ ሳትጠፋ

ተነሳ ተነሳ … አሁኑኑ በፍጥነት … ተነሳ ነፍስ ዝራ ።  

መታሰቢያነቱ የማይገባውን ግፍ ለወረደበት ለትግራይ ህዝብ ይሁን!

Eyob Gidey 02 Mar 2024

By aiga