ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በሂወት ሲለይን፣ ድፍን የኢትዮጲያ ሕዝብ መሪር ሃዘን ተሰምቶት ነበር።ያ ሕዝቡ ያሳየው ሃዘን፣ ቅንና ትኽለኛ ሃዘን፣ከልብ የመነጨ ሃዘን ነበር።ከማይረሱኝ መልእክቶች የገጣሚ “ታገል ሰይፉ” ገና እንሮጣለን የሚለው ግጥሙ ሕዝብን እምባ ያራጨ ነበር። ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊም በትክክል ገልፆታል። የሚያሳዝነው በወቅቱ ክቡር ጠ/ሚሩ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄና፣እሳቸው የሰጡት መልስ እዉን ሆኖ ማየት ደግሞ የክቡር ጠ/ሚ የዛኔው መልስ ሳይሆን ዛሬ በሃገሪቷ የተከሰተውን ተጨባጭ ሁኔታ የመተንበይ እውቀታቸውም ጭምር፣ ሳላደንቅ ማለፍ አልችልም።እንዲህ ብለው ነበር የመለሱት።ስጋት አሎዎት ? ካለዎትስ ምንድነው ? ተብለው ሲጠየቁ ስጋቴማ ይህች ሃገር በአንድ “ህፃን ልጅ እጅ” እንዳትወድቅ ነው። ነበር ያሉት (አቶ አባዱላ ገመዳ በአንድ ወቅት ፓርላማ ላይ ክቡር ጠሚ ለምንድነው ለኛ ስልጣን የማይሰጠን ? ሲሏቸው ክቡር አቶ አባዱላ ብርጭቆ “ለህጻን ልጅ” አይሰጥም) እንዳሏቸው አይነት መሆኑ ነው።ሃገሪቱ ክቡር ጠ/ሚ እንደፈሩት “በማይሆን ሰው እጅ ወድቃ” ልፋታችን እንዳይቀለበስ እሰጋለሁኝ። እንዳሉት መሆኑ ነው።

አብይ አህመድ ገና ወደ ስልጣን እንደመጣ፣የኢትዮጲያ ሕዝብን ሲዘልፍ “ሾርት ሚሞሪ” በማለት ነበር የጀመረው። በርግጥ ያን ሰውዬ የሃገሪቱ ሕዝብ ከስሜን እስከ ደቡብ፣ከምእራብ እስከ ምስራቅ በአንድ ድምጽና፣ በአንድ ስሜት ነበር የተቀበለው።በተለይ ደግሞ የትግራይ ሕዝብ መቀለ ሄዶ ካደረገው ንግግር በመነሳት ትልቅ ተስፋ ጥሎበት ነበር ? የኃላ ኃላ ግን ትኽክለኛ ማንነቱ ለማወቅ ግዜ አልፈጀበትም።

ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ማለት የዛሬ አያርገውና እንደምናየውና፣እንደምንሰማው ሳይሆን በአለም ተፈጥረው ካለፉ ስመጥር ግለሰቦች ውስጥ የሚመደብ ትግራይ፣ኢትዮጲያ፣ከዛም አልፎ አፍሪቃ ካፈራቻቸው ምርጥ ልጆቿ አንዱ ነው።

አለም እነ አልበርት አንስታይን፣እነ ዊልያም ሸክስፒር፣እነ ሞዛርት፣እነ ማንዴላና፣ማዘር ተሬሳ፣እነ መለስ ዜናዊ እንዲሁም ሌሎች ስመጥር መሪዎች፣ሳይንቲስቶች፣ፖለቲከኞችና ኢኮኖሚስቶች ስታፈራ ? እነዚህ ግለሰቦች ከስህተት ነጻ ነበሩ ማለት ባይቻልም፣ በሰሩት ድንቅ ስራ ዓለም ታስታውሰቸዋለች።

      አለመታደል ሆኖ ግን እኛ ሃበሾች፣ኢትዮጲያዊያኖች፣ተጋሩዎች የራሳችን እያጣጣልን ነጮች ከኛው ወስደው፣የኛው በራሳቸው ቃላት ተርጉመው፣ የኛን እንደራሳቸው አስመስለው ሲሰብኩን አፋችን ከፍተን የምናዳምጥና ? የምናስተጋባ አሳፋሪ ፍጡራን መሆናችን ለሚረዳ ሙሁር ነኝ ? ፖለቲከኛ ነኝ ? ባይ ኢትዮጲያዊ ሆነ ትግራዋይ እንደማየት የመሰለ የውድቀት ውድቀት የት ይገኝ ይሆን ? እረ ለመሆኑ የራሳችንን እያራከስን ? የሌሎችን ስናዳምቅ ምን ያክል የእውቀት ድህነት ላይ እንደገባን ለመረዳት እንችል ይሆን ?

እኔን የሚገርመኝ ክቡር ጠ/ሚ መለስ ዜናዊኮ ? አለም ካፈራቻቸው ብልህ መሪዎች ተርታ የሚሰለፍ ባለ ምጡቅ አይእምሮ መሆኑ የአለም መሪዎች፣የአለም ኢኮኖሚስቶችና፣የአለም ዩኒቨርሲቲዎች የመሰከሩለት፣እነ “አምባሳደር ሱዛን ራይዝ” ሂ ኢዝ ኤ ዎርልድ ክላስ ማይንድ ነው(He is world class mind) ብለው በአደባባይ የመሰከሩለት ግለሰብ መሆኑን ረሳን ? ጠ/ም መለስ ዜናዊ ማለትኮ እነ “ጎርደን ብራውንና፣ቶኒይ ብሌርን” የመሳሰሉትን የእንግሊዝ መሪዎችን አስከትሎ፣በነ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች እየተጋበዘ የራሳቸው “የኒዮ ሊብራሊዝም” ፍልስፍና የመጨረሻ ውድቀትና፣የራሱን ልማታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍና፣ በእውቀትና በኩራት ተሟግቶ የሚያሳምን ብልህ ታዋቂ ሳይሆን “አዋቂ ግለሰብ”እኮ ነው።

ጠ/ም መለስዜናዊ ማለትኮ በአለም የአየር ጸባይ፣በአፍሪቃዊያን የወደፊት እጣ የሚሞግት፣ ከበለጸጉት ጂ፰ (G8)ሃገራትና ከ(G20)ጂ፳ ሃገራት፣ የአፍሪቃ አህጉርን ወክሎ፣ ለዛውም ተመርጦ፣አንተ የኛ የአፍሪቃዊያን ወኪል ነህ ! ተብሎ የተመረጠ ብቁ መሪኮ ነው።ጠ/ሚ መለስ ተተኪዎች አላፈራም ስንል ? ደ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት መሪ፣ዶር ማሃሪ ታደለ ማሩ፣ሳይንቲስት ዘቢባ የኑስ፣ኮሎኔል ዶክተር ቢንያም ተወልደ፣እነ ኢንጅነር ታደስ የማነ ኮሎኔል ዶክተር ቢንያም ተወልደ የመለስየስራ ውጤቶች አይደሉምንዴ ? መለስ ባቋቋመው ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው አሁን ላሉበት የላቀ አለም አቀፋዊና፣ ሃገራዊ ሃላፊነት የበቁ ሙሁራን አይደሉምን ?

  ይህን የትግራይ፣የኢትዮጲያ፣የአፍሪቃ አለኝታን ነው እንግዲህ ? ማንም የሱን የእግር እጣቢ ያክል እውቀትም ሆነ አስተዋጽኦ የሌለው ?  መሪ፣ካድሬ፣አክቲቪስት፣ፖለቲከኛ እየተነሳ ሊወቅሰዉ የሚዳዳው ያለዉ ? እረ ለመሆኑ የኢትዮጲያ ሙሁራኖች ይሁን የትግራይ ሙሁራኖች ሆይ ? ለሁሉም ልክ አለው።ክቡር ጠቅላይ ምኒስትሩ በሂወት ዘመኑ ታግሎ፣መርቶ የሚታይ፣ የሚነካ፣የሚቆጠር፣ የሚመነዘር የስራ ውጤት አሳይቶ፣ አስረክቦን አልፏል።

     አብይ አህመድኳን ዕድሉ ገጥሞት እንሆ ላለፉት ፮ ዓመታት እሱ የተከላቸው፣ እሱ የጀመራቸው፣በሱ የስልጣን ዘመን የተከማቸን የሃገር ሃብት እየተጠቀመ  እዚህ ደርሳል። የሚያሳዝነው መለስ የገነባውን ቴሌኮም፣አየር መንገድ፣ ባንክ፣ የኤሌክትሪክ ሃይል፣ አንድ በአንድ እየሸጠ ? በተቃራኒው ከኢትዮጲያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተባብሮ ሃገሪቱ የኃሊት እንድታሽቆለቁል የበኩሉን እያደረገ ነው።  መገንባት ያቃታችሁን ኢኮኖሚና እድገት?  በመሸጥ የግል ስልጣናችሁን ለመጠበቅ ስትሉ ሃገሪቷ አይታው የማታውቀውን ጦርነት ቀሰቅሳቹህ አደለም ብችሎታቹህ ልትገነቡ፣የተገነባውንም ማስቀጠል አልቻላችሁም።ታድያ በየ ጎራዉ የተሰገሰጋቹህ የሌቦች ጥርቅም፣ በስመ መለስ ቅጥፈታቹህ ምናልባት ውድቀታቹህ ለመሸፋፈን የማታቀርቡት ምክንያት አይኖርም። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የሚለካው እሱ በነበረበት የመሪነት ግዜ፣ባሰራቸው ጥሩ ስራዎች ሲመሰገን፣የተሳሳታቸው ስህተቶች ደግሞ እናንተ ከሱ በኃላ ሃላፊነቱን የተረከባቹህ ሙሁራን፤ ፖለቲከኞች ነን ባዮች (ካላቹህ ? ማለቴ ነው)የሱን ስህተት አርማቹህ ሃገሪቷን ወደተሻለ ልማትና እድገት ማድረስ ሲገባቹህ?  “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል” እንዳሉት “ትግራይም ሆነ ኢትዮጲያ” ከድጡ ወደ ማጡ ነክራቹህ ? እናንተ ስልጣናቹህን ለማስጠበቅ ሲባል፣ ደስ ሲላቹህ ሶማልያ፣ደስ ሲላቹህ ወለጋ፣ደስ ሲላቹህ ትግራይ፣ደስ ሲላቹህ አማራ፣ደስ ሲላቹህ ሱዳን፣አንዴ ከግብጽ እያላቹህ ይህን ምስኪን ሕዝብ አንዴ በስመ ሰላም ? አንዴ በስመ ሕግ ማክበር ? እያገላበጣቹህ ትቆሉታላቹህ ? የሚያሳዝነው ደግሞ የትምህርትን ትርጉም መቀመቅ የከተቱት የሙሁራን ሆድ አደሮች፣ ይጦሩኛል ? ይጠቅሙኛል ? ብሎ አፉን ትቶ ያስተማራቸውን ድሃውና፣ ገበሬውን ማሕበረሰብ፣ የከዳ የወረቀት ሙሁር፣ የእውቀት ድሃ፣ የሆነው ሙሁር ተብዬ ? እናንተ የዘመኑ አሳፋሪ ፖለቲከኞችን መሞገት እየቻለ ? ለሆነውም ላልሆነውም እያጎበደደና፣ የመጣው እንደ “ጆከር የካርታ” መጫወቻ የሚያገላብጠው የዘመኑ ሙሁር ማየትን የመሰለ የመጨረሻ ዝቅጠት ? በመለስ ግዜ አልነበረም።አልታዬምም።ታድያ ይህንን እውነታና ሃቅ ዛሬ የናንተው ሚዲያዎች ለጋዜጠኝነት ስነምግባር ሳይሆን ? ለገቢ ምንጭነትና፣ ለሃብት መሰብሰቢያ፣ በሚጠቀሙበት ሚዲያ መለስን ለመውቀስ ከየጥጋቹህ ብቅ ጥልቅ ብትሉም ? የክቡር ጠቅላይ ምኒስተር መለስ ዜናዊ ታሪክ እናንተ ባገኛችሁት አጋጣሚ ብትተቹት? ብታጣጥሉት ? መለስም ሆነ፣ እናንተ የዘመኑ እንደ “ነጭ ወረቀት ባዶና፣ንጹሃን” ግዜው ጠብቆ ታሪክ ይፈርዳል።ስራዎቻቹህ ህያው ናቸውና። 

ክቡር ጠቅላይ ምኒስተር መለስ ዜናዊ ህያው ነው። መለስ የህዳሴው ግድብ ነው።መለስ የአዳማው የፍጥነት መንገድ ነው።መለስ የአዲስ አበባው ጅቡቲ ባቡር ሃዲድ ነው።መለስ ግልገል ግቤ ፪ና ፣ ፫ ነው፣ መለስ ከ፵ በላይ ዩኒቨርስቲዎች ነው፣መለስ የኢትዮጲያ አር መንገድ ነው።መለስ የነዛ ዘመናዊ ሆስፒታሎች፣ የገበሬውን ሂወት የቀየሩት ጤና ጣቢዎች፣ ባለቤት ነው። እረ ስንቱ ??? የረሳሗቸውን ጨምሩበት።እናንተ የዚህ ዘመን ጉዶች በምን እናድንቃቹህ ? እናስታውሳቹህ ካልንም ? ጠ/ሚ መለስ የገነባውን ኢኮኖሚ “በማፍረስ” እንዘክራቹሃለን፣ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በማውደም እንዘክራቹሃለን። የዘመናችን ትልቁ የእርስ በርስ ጦርነት በመቀሰቀስና በማዋለድ እንዘክራቹሃለን። ይሄው ነው እናንተ ከህልፈተ ሂወት ክቡር ጠቅላይ ምኒስተር በኃላ የመጣቹህ የፖለቲካ መሪዎች የምትዘከሩበት ታሪክ።

 ኢትዮጲያና፣ትግራይ በመለስ ግዜ የገነቡትን ኢኮኖሚ በማውደም “የህወሓትና፣የብልጽግና” ካድሬዎች በስልጣን ሽኩቻ የሕዝብን ደህንነትና፣የሃገሪቱን ሰላምና እድገት ችላ በማለት ? ለግል የፖለቲካ ስልጣናቸው ተብሎ ከ፳፪ ቢልዮን( $22 ቢልዮን ብር) በላይ ዶግ አመድ ያደረጉ የደናቁርት ፣የውሽታሞች፣ የእውቀት አልቦ ስብስቦች፣ በመባል ታሪክ ይዘክራቹሃል። ይሄዉ ነው የናንተ ታሪክ። ያ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ? ሌት ተቀን፣በግል ፍላጎት ሳይታለል፣የገዛ ልጆቹን፣ውዷ በለቤቱን የሚገባቸው የአባትነትና፣የባልነት ግዴታዉን ወደ ጎን ትቶ ? ሃገሬ፣ ሕዝቤ፣ እያለ በግዜ የለም የሩጫ ሂወት ! እንደ ሻማ ቀልጦ፣ ስራው በተግባር አሳይቶ፣ ያለፈው ጀግናው ጠ/ሚ መለ ዜናዊ ግን ክቡር ነው።ህያውም ነው።

በአንድ ወቅት “አቶ በረከት ስሞኦን” ሲናገሩ በቤተመንግስት በግ ታርዶ፣ ሁሉሙ እየበሉና እየጠጡ፣ ሲዝናኑ አቶ በረከት መለስን ሊያየው ስላልቻለ፣ ተነስቶ ወደ ቢሮው ይሄዳል። መለስም ተደፍቶ መጽሃፍ ሲያነብ ያገኘዋል።እንዴ ምን ታደርጋለህ  ናና ከኛ ጋር ተጫወት እንጂ ቢለው ? መለስ እምባ እየተናነቀው፣ “በረከት የዚህች ሃገር ችግር ከምንገምተው በላይ ነው”። እኔ ደግሞ ፈራሁኝ።ሃገሪቷ እጄ ላይ እንዳትሰበርብኝ ፈራሁኝ ? አለኝ ብሎ መስክሯል። ሌሊትና ቀን ሰርተን ይህች ሃገር ከወደቀችበት ማንሳት አለብን ! አለኝ። ብለው የሰጡትን ቃል ስንሰማ፣ጠ/ሚ መለስ ቃሉን በተግባር ያሳዬ፣ያስመሰከረ ብልህ፣በሳል፣አዋቂ መሪ ነበር።ዛሬ ማንም የእንግዴ ልጅ እየተነሳ ? መለስን ሊተች ወይም ሊያርም ሞራሉም፣ብቃቱም ያለው ኢትዮጲያዊ ይሁን ትግራዋይየለም ! ለወደፊትም አይኖርም !

በእግር ኳስ አለም “ፔሌ” የእግር ኳስ ንጉስ ይባላል ።ከፔሌ በኃላ እነ ማራዶና፣ሮናልዲኖ፣ሜሲ ፣ክርሲቲያኖ የመሳሰሉት ስመ ጥር እግር ኳስ ተጫዋቾች ተፈጥሯል።አንዳቸውም ግን የፔሌን ቦታ መውሰድ አልቻሉም። ምክያቱም ፔሌ የግዜው እንጂ የዛሬው ንጉስ አይደለም።የጠ/ሚ መለስም ክቡር እውቀትና የስራ ውጤትም ? በነበረበት ግዜ የተለካ፣ የአለም ምርጥ ጭንቅላት ከነበራቸው ሰዎች መካከል ለዘልአለም ተሰቅሏል። መለስዬ ሳንረዳህ፣ አስተሳሰብህና ራእይህ ሳይገባን፣ ሳንጠቀምብህ፣ ላጠፋነው ጥፋትና፣ የራሳችን የአይእምሮ መቀንጨር ለላማመን፣ መለስ መሪዎች ሊፈጥርልን አልቻለም ? ብለን አንተን ስህተተኛ አድርገን በመሳል፣እኛ ትኽለኞች መስለን ለመታየት እያደረግነው ያለው ደባን ይቅር በለን ????

እስኪ ለሰከንድ ቆም ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፣ከመለስ በኃላ የመጡትን ተላላኪ ካድሬዎችን እንይ ? የሃገሪቱን የቁልቁለት ጉዞ እናስተውል ? የሌብነቱ፣የሙሰኝነቱ፣የዝርፊያው፣የስራ አጥነቱ፣የኑሮ ውድነቱ፣የሰላም እጦቱ፣የሃገሪቱ ዳርድምበር መደፈሩ፣የሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ውድቀትና፣በአጠቃላይ የማህበራዊ ቀውሱን እንመልከት ? እነዚህ ሁሉ የቁልቁለት ጉዞ ያስጀመሩን ሙሁራንና ፖለቲከኞች ናቸው እንግዲህ መለስን ተተኪዎች አላፈራም እያሉን ያሉት ?

ሕዝቤ ሆይ መለስ በአለም ዉስጥ አሉ ከሚባሉት ሕገ መንግስቶች ጨምቆ የሃገሪቱ ሕገ መንግስት አጽድቆልሃል።እንደ ሕዝብ፣ እንደ ሙሁር፣እንደ ፖለቲከኛ በአጠቃላይ እንደዜጋ፣ ለመብትህና ለልጅ ልጆችህ ስትል ? ሕገ መንግስቱ ወደ መሬት ወርዶ በሕዝባዊ ተቋማት እንዲጠናከር እስከ መስዋእትነትም ቢሆን ከፍለህ መብትህን አስጠብቅ።ይህ ዋናውና አማራጭ የሌለው ግዴታህ ነው።አይ ካልክ ደግሞ ጣቶችህን ወደሌሎች እየቀሰርክ ? የመጣው አፈጮሌ እያታለለህ መኖር ትችላለህ። ኢትዮጲያዊም ሆንክ ትግራዋይ ? ለደቂቃ ሰከን ብለህ እራስክን ፈትሽ ? የወላጆችህ ስራ ጀግንነት፣ክብር የነሱ ታሪክ እንጂ ያንተ የስራ ውጤት አይደለም። አሁን ያለው ያንተ ታሪክ ጦርነት፣ርሃብ፣በሽታ፣ስራአጥነት፣ስደት እና ሌብነት የወረራት ሃገር መገለጫዋ የሆነች” ኢትዮጲያ፣ትግራይ” ናቸው።ይህ ነው ተጨባጩ ታሪክህ። ምርጫው በዚሁ ቀጥለህ ሃገሪቷ ድምጥማጧ እንድትጠፋና የእርስ በርስ ጦርነት የሰፈነባት የዘመነ መሳፍንቷ ኢትዮጲያ መመለስ ?  ወይስ ተሞኩሮ፣ የብርሃን ጭላንጭል የታየበትን ትክክለኛ ፌደራሊዝምና ሕዝቦች በመረጡት ስርአት የምትተዳደር ሃገር መመስረት ? ምርጫው የሕዝቡ ነው መልካም ቀን ! መለስዬ አንተም ሂወትህን በሰላም፣ገነት ውስጥ ያኑሩልን ! አሜን

ሙሉጌታ በሪሁን

By aiga

One thought on “           “ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው””
  1. Dear writer, I read your note about the former president prim minister Meles, I have a mixed filling about your story of Meles, yes he did some good while in power like many pm or Presidents in the past. The problem I found in your writing is you only focused on the good part of Meles and you deliberately avoid all the bad policy he and his cadres created in the country. The problem we are facing now in the country is created by him and his party called eprdf. I will mention few of the problems he created for the country, one is to make the country a land locked country, second to create an administrative region based on ethnicity the third mega sin he did is to carve out land from Gonder and Wello places like welkayet and raya and incorporate in to the tegrai I can go on and on, so please open your mind you fox in tegrai are now a victim of this policy

Comments are closed.