እንርሳው ወይ … አረሜናዊ ግፉን
በትግራይ ምድር ላይ …
በወራሪ አራዊቶች … የወረደውን ሀጢያት
የደረሰውን ጭካኔ … የዘነበውን መዐት
ደረሰ ወይ በናንተ … ደረሰ እንጂ በኔ
            እኔ ማለት ? …
… ሚሊዮኖች እኔ  … አለን በትግራይ ላይ

እንባችን የደረቀ … ልሳናችን የተዘጋ … ሆዳችን የቆሰለ
ልባችን የተሰበረ … እንቅልፍ የተሳነን .. መራመድ ያቃተን
የስነ አእምሮ በሽተኞች … የስነ ልቦና ተጠቂዎች
ተንቃሻቃሽ ሬሳዎች … ያልሞትን ግን የሞትንው
የግፍ ረገጥ ተምሳሊዎች  … የታሪክ ዝክርቶች
እናቶች፣ እህቶች ፣ አባቶች ፣ ወንድሞች ፣
ምስኪን ህጻናቶች … ስጋ ለበስ ፍጥሮች …
እንሳቅ ወይ የውሸት ሳቅ …
እናጨብጭብ ወይ ባንድ እጃችን
… ተጋሩ እኔዎች
            አዎ 
እኔዎች … እኔዎች … ፍትህ ፈላጊዎች
… እንርሳው ወይ ግፉን … እንርሳው ወይ ጥቅሱን 
ከመተማ እስከ ባህርዳር … ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ
ኤርትራ ወዳጄ … ኢሱ ቀኝ እጄ … ተብሎም እንደ ነበር
እንሰርዘው ወይ … ይሄን ከአእምሯችን … ፀረ-ሰላም እንዳንባል
ደብቀን ቁስላችንን … ሁሉን እንርሳውና …
… ሰላም ብለን … ሰላምን እንቀበል? 

መታሰቢያነቱ … በባዕድና በአገር ውስጥ ወራሪ አራዊቶች – ግፍ ለደረሰባቸው የትግራይ ህዝብ ይሁን 

በ እየብ ግደይ

By aiga