W. Yilma

በአቢይ መንግስትና በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መካከል November 2/ 2022 በፕሪቶሪያ ጦርነትን በዘለቄታ የማስቅም ስምምነት ከተደረሰ በኳሏ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውሉ እንደጠፋበት አቅጣጫ እያዘመመ መሆኑ ፖለቲካን ለሚከታተል ለው አደጋች አይደለም። ይህስ ለምን ሆነብሎ ለሚጠይቅ መለሱ የጦርነቱን መቆም አዲስ ጥምረት ለመሠረቱት የኤርትራው ሻዕቢያና የአማራ ክልል ፖለቲከኞች ምቾት የማይሰጣቸው ሆኖ ስለተገኘ ነው። በጥባጭ ካለ ማን ንፁህ ውሃ ይጠጣል? እጅግ የሚያሰጎርመው ነኀር በመላ ኢትዮጵያ ወደ 30 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የሚላሰ የሚቀመስ ባጣበትና ይህም ሁኔታ ያተቀረው የአለም ህዝብ ያመነጋጎሪያ አጀንደ በሆነበት በኢትዮጵያውያን ፖለቲካ አውርቶ አደሮች መንደር ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ሃገሪቷ በመንደር ወጠምሻ እየታመለች ትገኛለች። ሁሉም አጥፊ እንጂ ትንሽ እንኳን አዋቂ በጠፋበት ሃገር ህሊና ላለው ኢትዮጵያዊ ይህን
ክስተት ሲመለከት ከማፈርም አልፎ አንገት በማስደፋት “ኢትዮጵያዊ” አይደለሁም የሚያስብል ደረጃ የሚያስደርስ ነው። አሁን በኢትዮጵያ ምን የማያጣላ ነገር አለ? በፖለቲካ አመለካከት ፣ በማንነት ፣ በመሬት ፣ በድንበር ፣ በሃይማኖት እና በታሪክ ወ.ዘ.ተ ጠብ-ያለሽ በዳቦ!
መነሻዬ ስለተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ለማውራት ስይሆን አሁን ትግራይ ስላለችበት የፖለቲካ ሁኔታ ሆኖ ወደዚያው ላምራ። ባጭሩ ወደ ፍሬ ነገሩ ስገባ ሕሊና ላለውና እንደሰው ለሚያስብ ፍጡር በትግራይ የሚታየው የፖለቲካ አካሄድ አዝማሚያው በእጅጉ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ልብንም የሚያደማ ነው። እንድያው አሁን ማንይሙት ምን ያለ ሰው ነው ትግራይ ውስጥ ሥልጣን የሚፈለገው? ሁሉም በወደመበት ምን ሰርቶ ምንስ መቼ ሊያሳካነው? ማንን አብልቶ ማንን ሊያጠግብ? ለየትኛው ሥራፈለጊ ሥራ አስገኝቶለት ኑሮውን እንዲመራ ሊያደርግ? ስንቱን ትምህርት ፈላጊ ወደትምህርት ቤት አስገብቶ የእውቀት ጥማቱን ሊያረካለት? ስንቱን የአካልና የሠነልቦና ታማሚ ሃኪም ቤትና ክሊኒክ አስገብቶ ከበሽታቸው ሊፈወስ? ስንቱን የተራቆተ ልብስ አልብሶ ሰውነቱን ሊሸፍን? ስንቱን የተፈናቀለ ወደቀድሞው ቀየው መልሶ በዘለቀታ ሊያቋቁም? ለስንቱ ነፍሰጡር እናትና ህፃናት
ክትባት ሊሰጥ? ስንቱን አካለ ስንኩል በቋሚነት ሲረዳ? ኸረ ስንቱ ተዘርዝሮ ስንቱ የነገራል? እንዲያው ብቻ አሳቢ እና አዛኝ ላጣው ምስኪኑ ለትግራይ ህዝብ ፈጣሪ ይድረስለት እና ጠላቶቹን አሰገዝቶለት ከመከራ ያውጣው ከማለት በስተቀር ከሰው ብዙ ይጠበቃል የሚል እምነት የለኝም።
ኣብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ለራሱ በብዙ መከራ ተሸብቦም ያለ ቢሆንም አሁን በትግራይ ያጊዜአዊ አስተዳድር ለመመስረት ያሚደረገውን ሂደት በአትኩሮት ይከታተላል ፣ እነዚህንም በሁለት ጉራ ከፍሎ ማየት ይቻላል። ጨካኞች እና ፋሺስቶች የሆኑ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የማቋቋመው የጊዜአዊ አስተዳደር ሂደቱ ተስናክሎ የትግራይ ህዝብን እነሱ ከመጨፍጨፍ እራስ በራስ ኣባልተው የበለጠ ጉዳት በማድረስ ርኩስ አላማቸውን ማሳካት የሚፈልጉ።

ሰላም ፈላጊዎች ፣ የትግራይ ህዝብ ትግል ደጋፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ቶሎ ተመስርቶ የትግራይ ህዝብ አሁን ካሉበት ችግር በአፋጣኝ ወጥቶ ወደ ተረጋጋና ሰላማዊ ሕይወቱ እንዲመለስ ፍላጎት ያላቸው ናቸው። ቀምነገሩ ግን ከላይ ከተጠቀሱት በላይ መላው የትግራይ ህዝብ የሰላምን ሂደት ተሳክቶ አሁን ከአቅሙ በላይ የሆነውን ባለብዙ ዘርፍ ችግር እና ስቃይ በቶሎ ሊያስወግዱለት ወደሚችል ሁኔታ እንዲደርስለት እንጂ ልጆቹ አንድሰው በምትይዝ የሥልጣን ወንበር እርስ በርስ ተጣልተው መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት እንዲያጋዮ አይደለም።
ደግሞስ ምን የሚቃጠል ቤት እና ንብረት ከጠላት ተርፎ ! እንዲያውም ይህ ቀርቶ በይበልጥም ሻዕቢያ እንደ “ቁራሌ” ምን ለቃቅሞ ያልወሰደው አለና? በግልፅ ለመናገር በተለይ በትግራይ በአሁኑ ጊዜ ዲሞክራሲ እና ግልፅ የሆነ አሰራርን የሚጠላ ካለ ጤነኛ አዕምሮ የሌለው ሠው መሆን ኣለበት። የዚያኑ ያህል ዙሪያውን በእብዶች ፣ ለውበላ አምባገኖችና ሽፍቶች በበዙበትና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የትግራይ ህዝብ ህልውናው በሰው እጅ ምፅዋት ላይ በተመሠረተበት ትግራይን የዲምክራኪ ደሴት እናደርጋታለን በሚል ምናባሚ እሳቤ በመቋቋም ላይ ያለውን ጊዜአዊ አስተደደር በረባ ባልረባ አቃቂር እያወጡ መሰናክል መፍጠር ለህዝብ ማሰብ ነው የሚል ግምት የለኝም። ሀሳቤን በሚገባ ለመግለፅ አሁን ትግራይ ያለችበት አጠቃላይ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እጅግ የረቀቀና የቅርብ ግብን ሳይሆን የረዥሙን ጊዜ ጥቅም ባገናዘበ መልክ በጥንቃቄ መከናወን አለበት ማለት ዲሞክራሲን መቃወም አይደለም። ይህ ግምት ውስጥ ሳይገባ እንዲያው በዲሞክራሲ ስም የአካዳሚክ ትንታኔን በመስጠት የድንቁርና ፣ የመዴ አካሄድን ማበረታታት ከጥቅም ይልቅ ጉዳቱ የከፋ ነው የሚሆነው። መታወቅ ያለበት የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት አሁንም እድል ይሰጠን ከአሁን በፊት የፈፀምናቸው የዘር ማጥፋትና ሌሎች ከባባድ ወንጀሎች አይጣሩብን እያሉ በመማፀን ላይ ባሉበት ሰዓት ሌላ ተጨማሪ የፖለቲካ ብስለት የሌለው እሳቤ ከትግራይ ምድር ከተጨመረበት የትግራይ ህዝብ ጨርሶ እንደ ሀዝብ የሚጠፋበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። እንዴት ሰው ካለፈው ታሪኩ አይማርም? በይበልጥም የትግራይ ተወላጆች!
ለመስዋዕተንት ሳትጣሉ እንዴት ለስልጣን ትጣላላችሁ? በዚህ ሳቢያ በሚከሰተው ችግር ተጎጂ የሚሆነው ማነው? ተጠቃሚውስ? ምነው ማምለጫ እንዳጣች አይጥ በተጠመደላችሁ ወጥመድ ለመያዝ ተሽቀዳደማችሁ? በጣት ለሚቆጠሩ ኢሊቶች ፍላጎት ከ 5 አስክ 6 ሚሊዮን የሚገመተው የትግራይ ህዝብ በችግር ውስጥ ይኑር? የአብይ መንግስት እኮ የሚፈልገው በሰላም ስም አሁንም የትግራይን ህዝብ ማዳከምና ማሰቃየት ነው።
እዚህ ላይ በደንብ መታወቅ የሚያስፈልገው የፕሪቶሪያው ስምምነት በግልጽ አንዳስቀመጠው ድርድሩ የተካሄደው ትግራይን ይመራ በነበረው ህውሃትና የአብይ መንግስት መካከል ነው። በጣት ለሚቆጠሩ ወራቶች ይህ የፖለቲካ ድርጅት በግዚያዊ አስተዳደር ውስጥ የበላይነት ቢኖረው እንደከባድ ነገር መታየት የለበትም። ቁም ነገሩ ትግራይ በአንድ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ አንዳትገባ መስራቱ ላይ ነው። ትኩረት ማግኘት ያለበት ዲሞክራሲ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ለማስፈን ተከታታይነትና ሀቀኝነት ያለው የረዥም ግዜ ትግልን ይጠይቃል። የትግራይ ሁኔታ ክዚህ የተለየ አይደላም። ዲሞክራሲ ከሰላምና ከኢኮኖሚ እድገት በፊት አንዴት ቀድሞ ሊመጣ ይችላል? ፖለቲካ ጊዜና ቦታን አንዲሁም አቅምን ብሎም የአካባቢ ሁኔታዎችን ማገናዘብ ካልቻለ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዛኝ ሆኖ መገኝቱ መታወቅ አለበት። የአሁኑ የትግራይ ህዝብ ያለብት ሁኔታ ስለፖለቲካ ድርጅቶች ስልጣን የሚያስጨንቅ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ያለበትን ሁኔታ ተረድተን እንዴት ካለበት ባለብዙ ዘርፍ ችግሮች መንጥቀን እናውጣው።
ለዚህስ አፈጻጸም የሚረዳ አደረጃጀት እንዴት እንመስርት የሚል መሆን አለበት እንጂ እገሌ ይህን አገኘ አገሌ ያንን አጣ ወይም አነሰው ወደሚል አታካራ ውስጥ መግባት የትግራይን ህዝብ ችግር ከማባባስ አልፎ የጠላት መጫውቻም መሆን ነው። እናት ሀገሬ የምንላት ከድታን ምንም አንድነትና የተቀራረበ ፍላጎትና አላማ የሌላቸው የውጭና የውስጥ ስብስብ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው አኛን ለማጥፋት ሲተባበሩ እኛ ከዚህ ሁሉ መዓትና መከራ ለመዳን የነበረንን ትብብርና አንድነት እንዴት እናላላ? ህዝባችን አሁንም ተፈናቅሎ በከፍተኛ ችግር ላይ ነው፡
ገሚሱ የትግራይ መሬት በሻቢያና በተስፋፊዎቹ በህገወጥ መንገድ ተይዟል፡ በስቃይ የሞቱትን ትተን በአስር ሺዎች አስካሁን በእስር ላይ ያሉ አሉ። የባንክ አገልግሎት በቅጡ አልጀመረም ፣ አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ የነበረ ከደሞዝ ከተለየ ሁለት አመት አልፎታል። አነዚህንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ነገሮችን የማስፈጸም ላይ ትኩረት ሰጥቶት ሊሰራ ይገባል፡ የትግራይ ህዝብ ማንም ህዝብ ሊቋቋመውና ሊሸከመው የማይችለውን መከራ በመስዋእትነቱና በአንድነቱ አዚህ ደረጃ ላይ አድርሷል። ወደታሰበው ዘላቂ ሰላምና የዲሞክራሲ ስርዓት ለመድረስና ለመመስረት የአመለካከትና የባህሪ ለውጥ ከሁሉም ይፈለጋል።
በመጨረሻም ጦርነቱ ቆሞ ሰላም አንዲሰፍን ፍላጎታችን ከፍ ያለ ስለነበር የሰላም ሂደቱን ውስብስብነትና ግልጽ አለመሆን ልብ አላልነውም ነበር፡ አሁን ግን ግልጽ አየሆነ መጥቷል። ከሚታዩት ነገሮች የስምምነቱን ውሳኔዎች በመፈጸም ላይ ያለው ትግራይ ውስጥ ያለው ኃይል ነው። ከወዲያ ወገን ግን አዝጋሚነት ብቻ ሳይሆን ሆን ተብሎ ነገሮችን ወደማወሳሰብ የገባ ይመስላል፡ እኔ የምጠረጥረው የፈለገውን ዓይነት ጊዚያው አስተዳደር ይመስረት አብይ የእርሱ ፍላጎት አስካላሟላ ድረስ የመቀበል ፍላጎት የለውም። ይህም ሆን ብሎ የትግራይን ህዝብ የበለጠ በሰላም ስም ለመጉዳት ያቀደው ነው፡ ስለሆነም የዚህን አደገኝነት ታውቆ ከአብይ ጋር ስምምነት ያደረገው የትግራይ ኃይል አደራዳሪዎቹ የተጣለባቸውን ሃላፊነት አንዲወጡ መወትወት ያስፈልጋል።
ሰላም ለሁሉም!

By aiga

2 thoughts on “ትግራይ – እሳትአቀጣጠይ፣አውርቶ፣አደርአትፈልግም”
  1. Why you do not give up about Ethiopia and worry about Tigray only? I think enough lessons have been learnt, but some Tegarus stuck in Ethiopia and still talking about Ethiopia? The other thing, we do not want this language called Amharic our medium, it is a colonial language and I suggest you learn how to use your own language and if it is hard to do, just keep on trying. Amharic is a colonial language, colonnialists do not have to be white only.

  2. pulsar, I would like to be blunt , can you tell me the kind of tegray you can envision or build without Ethiopia? talk is cheap it is easy for you to say focus on tegray only . tegray or any other region can not survive without Ethiopia that is for sure. Specially a place like tegray with almost no resource tegary will collapse in no time. Look at eritra with a much better resource than tegray but still a miserable place for one to live. so there is a say in English, be careful what you ask for, you may just get it that would be a disaster

Comments are closed.