ቀኑን ያለቀበት
ኣውራ ዶሮ
ቁንጩን ሺቅብ ገትሮ
ኣቦራ ሲረጭ ጭሮ ጭሮ:
እንደ ቢራቢሮ:
ቀይ ብጫ ኣረንጓዴ ክንፍን ገትሮ:
ፈክሮ ፈክሮ:
በስማይ ከንፎ በሮ
ጏሮ ለጏሮ ተሽከርጅሮ
ማን ኣለ ከኔ ሌላ ዘንድሮ
ሄደ ሊዋጋ ከቀበሮ
ለምን ቅምጢትዋን በላህብኝ ብሎ::
መስሎት እንደኣመሉ እንደወትሮ:
ቀንዝሮ ቀንዝሮ
ሲደፈጥጥ እንስትዋ ደሮ
ጫጭቶችዋን ኣባሮ::
እየተዝመገመገ ቀበሮ ጉድጋድ ጥልቅ
የጭን ገረዲቱን ሊነቅ::
ታድያ ቢጠብቅ: ቢጠበቅ
እግረኛ ሠራዊት እርሱን የሚያደንቅ
ኣሸናፊ ኣለቃ ከጉድጏድ ሊል ብቅ:
ቢጠብቁ ቢጠብቁ
እንካን ኣውራ ደሮ
ክንፍም አልወጣም ተስፈንጥሮ:
ለካስ የኖሩት እድሜ ልክ
በቅዠት መቀምቅ
ነገር ዓለሙ ጠንቀ ቅ
ብለው ሳያውቁ:
ኣውራ ደሮው ትልቁ
እዝያው ከጉድጏድ ድብን ብሎ ማለቁ:
እውኑን ካረጋ ገጡ
እግሬ ኣውጪን ብለው ፈረጠጡ
ለረዥም ሲያላግጡ ሲሸላምጡ
ሳያስቡት ለካስ ሞትም ኣለ ብለው ደነገጡ::
ያሬድ ሕሉፍ
Yared,
what is your point? please elaborate the contents of your poem.