ኣብርሃም ብርሃነ

የዳዊት ፍሬው ኃይሉ እናት ወ/ሮ ዘነበች ዛሬ ጥዋት ከአንጀታቸው ስያለቅሱ የተናገሩት እሮሮ ነው።

 ሙዚቀኛ በቅርቡ ለሥራ ወደ ጣሊያን ሀገር የተጓዘው የተለያዩ የሙዚቃ መሣርያዎች ተጫዋች ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በተኛበት ክፍል ሞቶ ተገኝቷል። 

የታዋቂው የኪነት ሰው ፍሬው ኃይሉ ልጅ እና ዝነኛው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው መስከረም 7 ቀን 1971 ዓ.ም በአዲስ አበባ መዲና ልዩ ስሙ ደጃች ውቤ ሠፈር (አሁን ጊዜ በፈረሰውና ከአዲስ አበባ ምግብ አዳራሽ ፊት ለፊት አስፓልቱን ተሻግሮ) ነው የተወለደው፡፡

ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በራስ አበበ አረጋይ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ ደግሞ በእንጠጦ አጠቃላይ ትምህርት ቤት ከአጠናቀቀ በኋላ ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ ይመኘው የነበረውን፡የልጅነት ሕልሙን እውን ለማድረግ፡ የሙዚቃ ትምህርት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን አጠናቆ ተመርቋል፡፡ 

ፍሬው ከወለዳቸው ልጆች ብቸኛው አባቱን የተካ ትልቅ የሙዚቃ ሰው ነበር።

ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በዋነኛነት ከሚታወቅበት የክላርነቴ የሙዚቃ መሳሪያ በተጨማሪም አልቶ ሳክስፎን፣ክራር፣መሰንቆ ወዘተ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወታል፡፡በኪነት ዓለም ስሙ ያስጠራ ወጣት ነበር።

 ዳዊት ፍሬው ኃይሉ የአባቱ ሥራዎች ጭምር ያሉባቸው አራት የሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበሩ የሙዚቃ አልበም ለህዝብ በየለያዩ ጊዜ አቅርቧል፡፡ 

በታዋቂው እና አንጋፋው የብሔራዊ ትያትር ላይ ለ10 ዓመት በሞያው አገልግለዋል።

 ዳዊት በሙያው በመላው ኢትዮጵያ ተዟዙሮ ስራዎችን ከማቅረቡ በላይ ከሀገር ውጪ በፈረንሳይ፣ጀርመን ዴንማርክ፣ስዊድን፣ሆላንድ፣ኳታር፣ ለንደን፣ጅቡቲ ተዘዋውሮ ስራዎቹን አቅርቧል።

ዳዊት ፍሬው በኢትዮጵያ ቀደምትና የመጀመሪያ ከነበሩ ድምፃዊያን መካከል የታዋቂው ድምፃዊና ሙዚቀኛ የፍሬው ኃይሉ ልጅ ሲሆን ወደ ሙያው ለመምጣት የአባቱ ተፅእኖ ቀላል እንዳልሆ ይናገራል፡፡

ዳዊት የአባቱን ሥራዎች ለማስተዋወቅ በእጅጉ ጥሯል።

 ዳዊት በተኛበት ሙቶ ብመገኘቱ፡የአሟሟቱን ጉዳይ የጣልያን መንግስት እያጣራ እንደሆነ ተገልጿል።

ዳዊት እንደ አባቱ ብዙ በሚሰራበት ዕድሜ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። 

”አንተ የእኔን ሞት ማየት ሲገባህ እኔ ያንተን ሞት አየሁ!”

የዳዊት ወላጅ እናት ወ/ሮ ዘነበች።

ዓይጋ ለ ሟች ወዳጅ ቤተሰብ መፅናናት ትመኛለች!

By aiga