03 – 26 – 2022
ኢዛና ኦስካር
11’ዱ HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሰነዶችን የምንደግፍባቸው 11 ምክንያቶች
1. ረቂቅ ሰነዶቹ በዋናነት ሰላምን; ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው;
1.1 ማንም ነውረኞችም ጭምር በማይክዱት መንገድ በግልጽ ኢትዮጵያ በሰላም እጦት; በሰብዓዊ መብቶች ዝቅጠት ውስጥና በዲሞክራሲ ቀውስ ውስጥ ያለች በመሆኑ;
2. ፋሺስቱ ስርአት በትግራይ ሕዝብ ላይ፡የዘር ማጥፋት; የጦር ወንጀል እና ወረራ የፈጸመና በመፈጸም ላይ ያለ የሰው አራዊት ስብስብ በመሆኑ በወንጀሎቹ ሁሉ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች; ቡድኖችና ተቋማቶችን ተጠያቂ ለማድረግ ስለሚያግዝ;
3. ረቂቅ ሰነዶቹ በቀጥታ ወንጀል ፈጻሚዎችን እንጂ ህዝብና ሃገርን በቀጥታ target ያላደረገ በመሆኑ;
4. ረቂቅ ሰነዶቹ በይዘትና በአፈጻጸም የፋሺስቱን ስርአት ቁንጮዎች ለመግራት እና መስመር ለማስያዝ የሚያግዝ መሳሪያ በመሆኑ;
5. ረቂቅ ሰነዶቹ በትግራይ ሕዝብ እና መሰል ሕዝቦች ላይ ከተፈጸመው እጅግ ዘግናኝ በደልና መከራ አንጻር እንዲያውም የዘገዮ በመሆናቸው;
6. የትግራይ ሕዝብና መሰል ሕዝቦች እያደረጉ ላሉት ህዝባዊ ትግል አጋዥ ነው:: ለትግላችን ደጋፊና ወሳኝ በመሆኑ::
7. ረቂቅ ሰነዶቹ በይዘት; በአፈጻጸም እና በአካሄድ የሃገሪቱን ምሁራን; institutions, associations – – – ታርጌድ ያላደረጉና የማያደርጉ ናቸው::
8. ረቂቅ ሰነዶቹ አለምአቀፍ ህግጋትና መርሆችን የተከተሉ በመሆናቸው::
9. ፋሺስቱ ስርአት ለሰላም ጠንቅ; ለሰብዓዊነት ጠላት እና ለዲሞክራሲ ፈጽሞ የማይመች ስለሆነ;
9.1 ፋሺስቱ ስርአት የሰራው ስራ ባያስፈራው? ተጠያቂነቱ ባያስጨንቀው? መጽደቁ ባያስደነበርነው? ስለምን ንጹህ ቢሆን ቢጸድቅ ባይጸድቅ ምን አስጨነቀው? ጉዳዮ ከወንጀለኛነቱ በላይ ተጠያቂነት ስለሚያስፈራው አይደለምን?
10. ረቂቅ ሰነዶቹ ለሌላው አስተማሪና መማሪያ ለመሆን አቅም ስለሚፈጥር;
11. ፋሺስቱ ስርአት በሰላምም ሆነ በጦርነት እድሜው ስለማይቀጥል – ወደና ወደዚ እያለ በነውረኛነት አለማቀፍ ማሕበረሰብን ለማጭበርበር ከሄደበትና እየሄደበት ካለው መስመር ለማገድና ሚናውን ለይቶ: ወይ ሰላም አልያም ጦርነት? ብቻ ምርጫው እንዲሆን enforce የማድረጊ መሳሪያ ሊሆን የሚችል በመሆኑ ነው::
ፋሺስቱ ስርአትና ደጋፊዎቹ ስለሰላም; ስለሰብዓዊ መብትና ስለዲሞክራሲ ሲጠየቁ እነሱ የሰላም ጸር; የሰብዓዊ መብት ጣሽና ገዳቢ; ጸረ ዲሞክራት በመሆናቸው ገመናቸውን ለመደበቅና የተለመደ ሸፍጣቸውን ለመደበቅ “ሉዓላዊነት” እና “የሀገር ክብር” የሚል ነጥብ ያነሳሉ:: ይህም ፈጽሞ የማይገናኝ ምክንያታቸው ነው:: ም/ቱም:-
I. ሰላም; ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ አለም አቀፍ – ድንበር አልባ የሰው ልጅ በሙሉ የሚያስፈልገውና የሚፈልገው ነጥብ ነው::
2. የኤርትራ ጦርን; የሱማሊያ ጦርን; የUAE Drones & high level military expert; የchina የጦር መሳሪያ; የቱርክ drones & military machines; የAzerbaijan military equipments – – – ወዘተ ተጠቅሞ በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት; የጦር ወንጀል እና ወረራ የፈጸመና በመፈጸም ላይ ያለ ስርአት በየትኛውም መለኪያዎች ስለሉኣላዊነት እና ስለሀገር ክብር ለመናገር ሞራላዊ ብቃት የለውም:: ፈጽሞም አይኖረውም::
በአለም የዲፕሎማሲ መድረክ የወረደና የዘቀጠ ፋሺስት ስርአት በሰብዓዊነት ላይ ላደረሰውና በማድረስ ላይ ላለው ግፍ; ስቃይና በደል HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሰነዶች ጥሩ ማሳያዎችና ጥሩ በትሮች ናቸው::
ትግራይ ትስዕር!
ትግራይ ትዕወት!