ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

የትግራይ ህዝብ በአማራ ህዝብ ያለው እይታና አመለካከት እውነት ስለሆነ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት አሁንም ደግሜ እላለልሁ። ይኸውም፥ ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ብትል የትግራይ ህዝብ፥ የአማራ ህዝብ ጠላቴ ነው ብሎ አያምንም። ትግራዋይ፥ አማራ እንደ ህዝብ ጠላቴ ነው ብሎ አያምንም። ከየትኛውም ወገን ይሁን እንደዚህ ዓይነት እምነትና አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሰውም ቢሆን እምነቱም ሆነ አስተሳሰቡ የጤና ሊሆን አይችልም። የትግራይ ህዝብ፥ ለአስራ ሰባት ዓመታት ባደረገው ትግልና በከፈለው የህይወት መስዋእትነት የአማራ ህዝብ ባለውለታ እንጅ ሌላ ሊሆን አይችልም። ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋ፣ ወሎ ተብለው በተናጠል የሚታወቀውና አንተ ጎጃም ነህ አንተ ጎንደር ነህ እየተባለ ሲናከስና ሲባላ የሚታወቀው ማህበረሰብ እንዲሁም ቅማንትና አገር ተብለው የሚታወቁ ብሔር ብሔረሰቦች በመላ አማራ የሚባል ካርታ ሰጥቶ አገርና ህዝብ ያደርገው ትግራዋይ እንጅ ኦሮሞ ወይም ጋምቤላ አይደለም። ከትጥቅ ትግሉ በሃኋም ቢሆን (በዘመነ ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ)፥ ትግራይ ለራስዋ እዚህ ግባ የሚባል መሰረተ ልማት ሳይኖራት፥ የአማራ ህዝብ በልማት በማቋቋም ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክታለች።

ዛሬ እንደዚህ ከሻዕቢያ ከሶማሊያና ከኢምሬትስ አገራትና መንግስታት ሰራዊት ተሰልፈው፥ ግባ በለው! እያሉ ሊወጉን፣ ሊጨፈጭፉንና ሊያስጨፈጭፉን በአገሪቱ አሉ የሚባሉ ባለሀብቶችና ሚልዮኔሮች የአማራ ክልል ተወላጆች ናቸው። እነዚህ ሚልዮኔሮች የፈጠረ ታድያ ሌላ ማንም ሳይሆን ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለእኩልነት የተዋደቀው የትግራይ ታጋይ በከፈለው የህይወት መስዋዕትነት ነው። በመሆኑም፥ የትግራይ ህዝብ ትናንትም ዛሬም የአማራ ህዝብ በክፉ የሚመለከት ህዝብ አይደለም፤ ይህን የሚያደግበት አንዳች ምክንያትም የለውም። ተራው የአማራ ሰው በየትኛው ዓለም እንደሚገኝ ማንኛው ሰው ኑሮውን የሚኖር ሰው ነው። የአማራ ህዝብ እንደ ማንኛውም ህዝብ ፍላጎቱም ሆነ መሻቱ በሰላም መኖር ነው። እንግዲያውስ፥ ትግራዋይ (በግልም በቡድንም) ከተራው የአማራ ህዝብ ጋር ምንም ዓይነት ቅሬታ ሆነ ጥላቻ የለውም፤ ሊኖሮውም አይችልም ሲባል ጭብጥ ላይ የተመሰረተ ሐቅ ለመሆኑ የሚጠራጠር ሊኖር አይገባም። በርግጥ ይህ መሬት ላይ ያለው እውነታ ጤናማ አእምሮ ያለው የአማራ ክልል ተወላጅ የሆነ ሰው ሁሉ የሚመሰክረው ሐቅ ነው።

የአማራ ከተሞች፥ ሰዎች በማንነታቸው ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ (ከጦርነቱ በፊትም በኋላም) በተጋሩ ላይ የፈጸሟቸው ግፎችና ሰቆቃዎች እንዲሁም ግዲያዎች በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው። ትግራዋይ ግን አማራ ይህን አደረገብኝ፣ አሳደደኝ፣ ገደለኝ ብሎ በማንነታቸው የአማራ ተወላጆች በሆኑ ንጹሐን ዜጎች ላይ እጁን ሊያነሳ ቀርቶ በሃሳብ ደረጃም በክፉ የተመለከተው አንድ ሰው ለምስክርነት አይገኝም። ትግራይ ውስጥ አንድ ሰው በማንነቱ አማራ ስለሆነ አይደለም ግፍ ሊፈጽምበት ቀርቶ ዘውር ብሎም በክፉ ዓይን የተመለከተው አንድ የአማራ ሰው የለም። ሌላው ሁሉ ቢቀር በዚህ ወቅት እንኳን ቢሆን፥ ትግራይ ውስጥ የሚገኝ በማንነቱ አማራ የሆነ የአማራ ክልል ተወላጅ ሁሉ መብቱ ተጠብቆለት እኩል በሰላም እየኖረ የሚገኝ ህዝብ ነው። “የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው!” ብሎ የተነሳና የዘመተ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ለሰሚ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ግፍና በደል የፈፀመ፣ ምንሊካዊ አስተሳሰብ የተጸናው የአማራ ልሒቅ ታድያ ትናንትም ዛሬም የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው።

የዐቢይ አህመድ ዓሊ ወደ ስልጣን መምጣት ጀምሮ ወረራው እስከ ተፈፀመበት የነበረውን ጊዜ የአማራ ልሒቃን ከትግራይ ጋር ያላቸው ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ችግራቸውን እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥረትና ሞክራዎች ሲደረግ አሻፈረኝ ብለው በአንፃሩ የአዳማ ፖለቲከኞች ተላላኪና አስፈፃሚዎች በመሆን ትግራይን አብሮው ወሯል፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍና በደል ፈፀመዋል፣ ሃብትና ንብረቱንም ወረዋል። የአማራ ልሒቃን ተሰጣቸው ተደጋጋሚ የሰላም ዕድል ሁሉ በማባከን ጦርነትን መምረጣቸውንም ይታወቃል። አሁን መፍትሔው፥ ጠቢቡ “አለንጋ ለፈረስ፥ ልጓም ለአህያ፥ በትርም ለሰነፍ ጀርባ ነው” እንዳለው (ምሳ.26፥3) የአማራ ልሒቃን በመረጡትና በሚገባቸው መንገድ ማስተናገድና ድጋሜ ፊታቸው ወደ ትግራይ እንዳያዞሩ መስበር ብቻ ነው። ይህ ማንም ያልሰለጠነ፣ መቼም ቢሆን የማይሰለጥን፣ ደንቃራና ኋላቀር የአማራ ልሒቅ ስፍራውን አውቆ እንዲኖር ከተፈለገ፣ በልኩ እንዲመላለስ ማድረግ የሚቻለው በሌላ በምንም ዓይነት መንገድ ሳይሆን በሚገባው መንገድ በማስተናገድ ብቻ ነው። ቀለል ባለ አማርኛ፥ ትግራይ ከአማራ ልሒቃን ጋር ያላት ችግር የምትፈታው በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍና በደል የፈጸመና ያስፈጸመ ወንጀለኛ ሁሉ ወደ ፍትህ በማቅረብ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።

አሁን በዚህ ሰዓት ከዚህም ከዚያም ሳይሆኑ አየር ላይ ተንሳፈው የቀሩ ለቅላቂዎችና ሸለፈታሞቹ የአማራ ልሒቃን ዛሬ መሄጃና አማራጭ ሲያጡ፣ ነፍሳቸው ለማትረፍ አልሞው ስለ ጦርነት አስከፊነት እየደሰኮሩ የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ/ወገን ነው! እያሉ የሚያስተጋቡት ያለ ሐሰተኛ አባባል እንደ ማያተርፋቸውና በዚህ ዋሾና የሸፈጥ ምላስ የሚደለል ትግራዋይ እንደሌለም ቁርጣቸው ያውቁ ዘንድ ይገባል። የአንድ አባት ልጆች ነን፣ ደማችን አንድ ነው፣ አንድ ህዝብ ነን ያለከው የአዳማ ፖለቲከኛ ቂጥህን ገልብጦ ሲገርፍህ ሌላ ማምለጫ ስለሌለህ “የትግራይ ህዝብ ወገን ህዝብ ነው! በሰሜን እየተካሄደ ያለ ጦርነት የፖለቲካ ሴራ ነው” ወዘተ እያልክ የምትቀባጥረውና የምታሰማው ያለ ጩኸት ሰሚ የለውም። ይህ ሁሉ መዓት ከመከሰቱና ከመምጣቱ በፊት አይንህን እንድትከፍት፣ መንገድህን እንድትሰልል፣ አካሄድህ ድጋሜ እንድትመረምርና ያለ ትግራይ ክብር እንደሌለህና ሊኖርህም እንደማይችል ሲነገርህ አሻፈረኝ ብለህ ያባከንከው ዕድል ዕዳው በራስህ ላይ እንጅ ትግራዋይ ያንተ ዕዳ ተካፋይ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለውም። በነገራችን ላይ፥ የአማራ ልሒቃን ከዚህ በከፋ መልኩ ሳይገረፉና ሳይላላጡ ከትግራይ ጋር ሰላም የማውረድ ፍላጎት ካላቸውና የሚሹም እንደሆነ አሁን በዚህ ሰዓት ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ያውቃሉ። ይሄ፥ እኛ ከሁሉም በላይ ነን፣ ሁሉንም የመግዛት መለኮታዊ ስልጣን የተሰጠን ለእኛ ነው፣ አንድ ባህል አንድ ቋንቋ አንድ ህዝብ የሚለው ልሃጫም እምነትና አስተሳሰብ ግን ዳግም ላያንሰራራና ላያውከን ዋጋውን ያገኛል። የአማራ ልሒቅ የሻዕቢያና የዐቢይ አህመድ ዓሊ አሻንጉሊት ሆኖ ለመቀጠል ከመረጠ አሁንም ይጮሃል የሚሰማውም አይኖርም።

በተረፈ፥ የአማራ ልሒቃን “የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው” ብለው የሚያምኑ ሰዎች ቢሆኑ ኖሮው፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊና ኢሳይያስ አፈወርቂ እየተፈራረቁ እንደ ውሻ ጃስ እያሉ በትግራይ ህዝብ ላይ ባስነሱት ጊዜ፥ ተዉ፣ በትክክል ችግር አለብን ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ ደግሞ አሁን እየሄዳችሁ ያለ መንገድ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፣ እርስበርሳችን ብንወያያና ብንመካከር ነው የሚሻለው፣ የሚያብለጨልጭ ሁሉ ወርቅ አይደለምና ይህ የሞቅታ ፖለቲካ አዳልጦ ይጥላችኋል፣ ያለ ትግራይ እዚች አገር ላይ አትከብርም፣ ከትግራይ ጋር መተናኮስ ይፈጃችሁ እንደሆነ እንጅ አይበጃችሁምና ልብ ግዙ ተብለው ድፍን ሦስት ዓመት ሙሉ ሲለመኑ በሰሙን ነበር። ዳሩ ግን፥ የአማራ ልሒቅ ሲባል በተፈጥሮው፥ ቅሌታም፣ ተላላኪ፣ ሃፍረት የሌለውና የማያውቅ ሰልቃጭና ወስላታ ቢራቢሮ፣ ቀረርቶና ሽለላ ከማሰማት ያለፈ ቁም-ነገር የማይገኝበት ተራጋሚ፣ ለመልካም ነገር የማይበቃ ምዋርተኛ፣ ባጭባጭና ሁከተኛ የሆነ ባዶ ፍጥረት በመሆኑ ከትግራይ በኩል የቀረቡለት የሰላም ሃሳብና አማራጭ ሁሉ በመንፈግ፥ መሬቱን ለሱዳን አስረክቦ፣ ከጎረቤት አገራትና መንግስታት ጋርም ግንባር በመፍጠር ትግራይን ወሯል የትግራይን ህዝብ አበሳብሰዋል። አጠምቀከ በስመ አብ አጠምቀከ በስመ ወልድ አጠምቀከ በስመ መንፈስ ቅዱስ ይኩን ስምከ/ኪ ብላ ስም ሰጥታ ክርስትና ያጠመቀችው ትግራይ ታሪካዊ ጠላት ብሎ ከሚጠራው የኤርትራ ሰራዊት ጋር መክሮና ጎን ተሰልፎ ትግራይን ወግቷል። የአማራ ልሒቃን ለሰሚ ጆሮ የሚሰቀጥጥ ግፍና በደል በትግራይ ህዝብ ላይ ፈጽመው ሲያበቁ ነው እንግዲህ ዛሬ ደግሞ ተመልሰው “የትግራይ ህዝብ ወንድም ህዝብ ነው” እያሉን ጥላ ከለላ፣ ታዳጊ ፍለጋ ሲማጸኑ እየሰማን ያለን። ጥጉ፥ ትግራዋይ የሚያውቀው የአማራ ልሒቅ ሌላ ምንም ሳይሆን ፍርድ የሚጠብቀው፥ ሌባና ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ነው። መፍትሔው? ቀደም ሲል እንደ ጠቀስኩት ፍትህና ፍርድ ማድረግ ነው።

በነጻ ብሎ ምሳ የለም!

By aiga

One thought on “ትግራይ ከአማራ ልሒቃን ጋር ያላት ችግር የምትፈታበት መንገድ አጭርና ግልጽ ነው”
1. እዞም ጥቕመ-ፈሊጣውያን አምሓራ እቲ አቐሚጥካዮ ዘለኻ አውሒድካሎም አለኽ ስለምታይሲ ኩሉ ናቶም ረብሓ አብ ሕሰም ትግራዎት ዝምስረት ኢዩ።ታሪኻዊ ጸላእቲ እዮም።ቕድሚ መግዛእትን ድሕሪ መግዛእትን ንትግራዋይ አብ ክልተ ዝመቐሉ ታሪኹ ዝሰረቑ ዳርጋ ቓንቘኡ ዘጥፈኡ መሪቱ ዝወረሱ ጸላእቲ ህዝቢናዮም።ሓንቲ ምስላ ናይ ትግረ አላ ‘ክፉእካ እልርአ ሰኒካ ኢየአምር’ ማለት ሕማቕካ ዘይረአየስ ጽቡቕካ አይፈልጥን !!

Comments are closed.