ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የጽሑፉ ዓላማ፥ ጎበዝ፥ በዓለማችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ የጎረቤት አገራትና መንግስታት አስተባብራ መጥታ በግዛትዋ ውስጥ ይኖር በነበረ ህዝብ (በትግራይ ህዝብ) ላይ የፈፀመችው ወረራ ግቡ ቢመታ፣ እንዳቀዱትም ቢሳካላቸውና ቢያጸዱን ኖሮ ይህ አሁን ቀጥለን የምንመለከተው ሐታታ ሁሉ ሊጻፍ ቀርቶ አይታሰብም ነበር። ህልውናውና ደህንነቱንና ክብሩና ማንነቱ በደሙና በመስዋእትነቱ ያረጋገጠ ብርቱና ተዋጊ የትግራይ ህዝብ በመስዋእትነቱ ልክ የሚገባው ያገኝ ዘንድ ድጋሜ ለማሳሰብ የተዘጋጀ አጭር ጽሑፍ ነው።
ሐተታ፥ ትግራዋይ በነገሮች ማሰብና መጨነቅ ካለበት አሁን በዚህ ሰዓት ከምንም በላይ ሊያሳስበው፣ ሊያስጨንቀውና ምላሽ ሊሰጥበት የሚገባው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር እንደ ህዝብ ለእኛ ለተጋሩ በዘላቂነት የሚረባንና የሚጠቅመን ምንድ ነው? የሚል ሊሆን ይገባል። የትግራይ ህዝብ፥ በትግሉና በመስዋእትነቱ ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንባር ፈጥረው በአንድነት ከተደገሱለት እንደ ህዝብ ታሪክ የማድረግ ድግስ ተርፋዋል። ጥያቄው ከዚህ በኋላስ? የሚል ነው። ትግራዋይ፥ ህልውናውና ደህንነቱና ክብሩና ማንነቱ በመስዋእትነቱ ካረጋገጠ በኋላ ቀጣይ ጉዞው ወዴት ነው? ምንድ ነው የሚጠብቀው? ህይወት ለገበረለት ዓላማ ተመኑ/ዋጋውና መዳረሻው ምንድ ነው? ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ ግድ ነው።
እውነት ነው፥ ትግራዋይ፥ ከዚህ ቀደም በታሪክ ከኢትዮጵያ የተበደረውና ለወደፊቱም የሚበደረው መልካም ነገር ሊኖር ቀርቶ ትግራዋይ እንደ ህዝብ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰምጦ በመቅረቱ መሄድ የሚችለውን ያህል ሳይሄድ የቀረ፣ ወደኋላ የቀረና ለኢትዮጵያ ሲባል የተጎሳቀለ ህዝብ ነው። ሐቁ፥ ለውጥ፣ ልማትና ዕድገት ለሚፈልግና ለሚመኝ ትግራዋይ ኢትዮጵያ የምትባል የምዋርተኞችና የነፍሰ ገዳዮች አገር እንቅፋት ናት። በሁሉም መስክ ሊባል በሚችል ሁኔታ የኋላቀርነት ምሳሌና መገለጫ የሆችው ኢትዮጵያ ለእኛ ለውጥ ፈላጊዎች ተጋሩ ወጥመድ ናት። ኢትዮጵያ የሰው መጨረሻ ሆኖ ስታበቃና ምንም ሳይኖራት፣ እንዲሁ በውሸት ስትቀደድ በድህነት ውስጥ ከኖረችና በደም የጨቀየችው የነፍሰ ገዳዮችና የወስላቶች አገር ጋር መፋታት ለእኛ ለተጋሩ ጥቅማችን ነው። ህልውናውና ደህንነቱ ክብሩና ማንነቱ በደሙና በመስዋእትነቱ ያረጋገጠ የትግራይ ህዝብ ለጥፋትና ለውድመት ካልሆነ በቀር ለለውጥና ለዕድገት ከኢትዮጵያ የሚፈልገውና የሚሻው አንዳች ነገር የለውም። ይህች ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ የአመጸኞችና የግብዞች አገር ለውጥ ፈላጊ ለሆነው ትግራዋይ ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ አሽክላ በመሆን ወደኋላ ከመጎተት ያለፈ ለትግራይ ዕድገትና ለውጥ የምታበረክተው አውንታዊ አስተዋጽዖ የላትም።
ጥጉ፥ ዘመናችንና ትውልዳችን የሚመጥን የራሳችን የትምህርት፣ የጤና፣ የእርሻ፣ የንግድ፣ የፋይናንስ፣ የትራንስፖርት ወዘተ ፕሮግራሞችና ፖሊሲዎች ቀርጸንና ጽፈን የራሳችንና የቤተ ሰቦቻችን ህይወት መለወጥ እንዲሁም እንደ አገር ማደግ ለምንሻ ለእኛ ለተጋሩ ከዚች መዓትዋ ከማያልቀው፣ በሃይማኖት ስምና ሽፋን የፈጣሪ ስምና ክብር በአደባባይ ከምታዋርድ፣ የአስመሳዮች የአታላዮችና የምቀኞች አገር ከሆነችው ኢትዮጵያ ከመፋታት ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ የለንም። ኢትዮጵያ አሁን በዚህ ሰዓት፥ የስልጣኔ ባለቤት ለሆነው፣ አቦጊዳ ብሎ ፊደል – እዝል ግዕዝና አራራይ ብሎ ዜማ – አሃዱ ክልኤቱ ብሎ ቁጥር ሰርቶ የሰጠ፣ ምግባርና ሃይማኖት ያስተማረ፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር በእጁ ጠፍጥፎ ለሰራትና ለቆረቆራት፣ ብርቱና ተዋጊ ለሆነው ለትግራይ ህዝብ የምትመጥን አገር አይደለችም። ከሰው በላይ ታክስ ሲክፍል የመጣና የሚታወቀው ትግራዋይ ነው። እንግዲያውስ ኢትዮጵያ፥ ለትግራይ የምትሰጠውና የምታበረክትው ሰው የማያወቀው ምንድ ነው ያላት? የሞትና የደም ናፍቆት ያለው ሰው ካልሆነ በቀር ያለፈውን አልፎዋል ብሎ ወደ ፊት የመሄድ ፍላጎት ላለው ትግራዋይ ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲህ ቤቱ ልትሆን አትችልም። እየተባለ ያለ ቀለል ባለ አማርኛ ለማስቀመጥ ያህል፥ አንፈልጋትም አታስፈልገንም ነው።
ጎበዝ፥ የቆረቆርናት፣ እውቀታችንና ጎልበታችን ገብረን ሰው የሚኖርባት አገር ያደረግናት፣ ከምንም በላይ ደግሞ በዘመናት መካከል የህይወት መስዋእትነት እየከፈልን ያቆየናትና ያቆምናት አገር ዛሬ ጥለን መሄዳችን ምንም አይቀርብንም። ቢቀርብንም የሚቀርብን ነገር ቢኖር፥ ፈጣሪና ባለ አእምሮ ሰው የሚፀየፈው በቃላት የማይገለጽ የለየለት ውሸት፣ ግብዝነት፣ ትምክህተኝነት፣ አመጽ፣ አጉል ሰይጣናዊ ሃይማኖተኝነት፣ አመንዝራነትና ሌብነት ነው የሚቀርብን። ከኢትዮጵያ ማምለጥ ለእኛ ተጋሩ የሚኖረው ትርጉም፥ ከድህነት፣ ከድንቁርና፣ ከከንቱና አልባሌ ሞት ማምለጥ ነው። ጳጳሳት መስቀል ይዘው፥ በሃይማኖችት ስምና ሽፋን ተዋህዶ ማለት ኢትዮጵያ ናት ለኢትዮጵያ መሞት ደግሞ ለተዋህዶ መሞት ነው! ሰይጣን ቢገዛን ይሻለናል! ወዘተ እያሉ ነፍሰ ገዳዮች ከሚመለምሉባበት ከኢትዮጵያ መሸሽ፥ ከመዓትና ከእርግማን ማምለጥና ነጻ መውጣት ነው። በመሆኑም፥ ተጋሩ መለወጥና መንገዳችንን ለይተን መሄድ አለብን ሲባል አንዲሁ የአፍአ ሳይሆን እውነኛ መለወጥ፥ የትም የማያደርስ መናኛ የሆነውን ህይወት መጸየፍ፣ መተውና መጣል ነው ስለሆነ ነው። መለወጥ፥
- የበከተና ቆሻሻ ማለትም ሃይማኖታዊ ሆነ ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ እምነትና አስተሳሰብ ጋር መፋታት ነው፤
- መለወጥ፥ በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ ተስፋ በአዲስ ጎዳና መሄድና መመላለስ መቻል ነው፤
- መለወጥ፥ መነሻህና መዳረሻህ እየተመለከትክ የቆምክበትን በማስተዋል መጠየቅ መቻል ነው፤
- መለወጥ፥ ባልህበት ርገጥ ከሚለው ህይወት በመውጣት ወደፊት መገግስገስ መቻል ነው፤
- መለወጥ፥ ከታሪካዊ እስራትና ባርነት መፈታት ነው፤
- መለወጥ፥ መባነን፣ መንቃትና ዓይንህን ከፍተህ ማየት፣ መሄድና መራመድ መቻል ነው፤
- መለወጥ፥ አድርግና አታድርግ በሌለበት ሁኔታ ራስህን ችለህ መቆም ነው፤
- መለወጥ፥ ከማያባራ መላለጥና ደምነት በመምለጥ ሰላማዊ ህይወት መኖር መቻል ነው፤
ሰው በአስተሳሰቡ የተፈወሰና የተለወጠ ያመለጠና የበራለት እንደሆነ ከመልካም ነገር ሁሉ አይጎድልም። ይህ ማለት፥ በአስተሳሰቡ የተፈታ ሰው ሌላኛው ሰው አለኝ የሚለውና የሚኮራበት ቁሳቁስ ሁሉ ሳይፈልገው ሊያገኘው የሚችልና የሚከተለውም ነገር ነው። አንድም፥ ለውጥም ዕድገትም የሚጀምረው ሰው በአስተሳሰቡ የተፈወሰና የነቃ እንደሆነ ነው። በአንጻሩ፥ በልዩ ልዩ ጨለምተኛ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እምነቶችና አስተሳሰቦች የታሰረ፣ ልቡና አእምሮው የጨለመበት፣ ራሱን ችሎ መቆም የማይችል ሰው ደግሞ አይደለም በራሱ ሊለወጥና ለውጥ ሊያመጣ ቀርቶ በተለወጠ አገር ማኸል ቢቀመጥም እንዲሁ ጎስቋላ እንደሆነ ይኖራታል እንጅ ህይወትን አያጣጥማትም። አቃቢትዋም አበምኔቱም የጦርነትና የፖለቲካ ተኝታኝ የሆነባት አገር ጋር ተስተካክሎ ልማትና ዕድገት ስለ ማይታሰብ ለውጥ የሚሻ ትግራዋይ ሁሉ ከእንደዚህ ዓይነቱ ወራዳነትና የተምታታው ማህበረሰብና አገር ራሱን ሊለይ ይገባል።
እንደ ጎረቤት አገር ለሀገረ ሱዳን የምንመኘው መልካም ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያም እንመኛለን!