ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የጽሑፉ ዓላማ፥ ሊዘርፍ፣ ሊያወድም፣ ሊያጠፋና ሊገድል የመጣው የኢትዮጵያ ሠራዊትና የአማራ ኢንተርሃምዌ ሚኒሻና ታጣቂ በምርኮ ሲሰበሰብ፥ ሙርከኛውን እዛው በሰላም ግባ! እየተባለ ማሰናበት አሁን አሁን እንደ አንድ ትልቅ ዜና መናገና ማስነገር እየተለመደ የመጣ ይመስላል። በርግጥ፥ ይህ እያደረገ ያለ አካል ምንን እያሰበ እያደረገው እንዳለና በተለይ ለኢትዮጵያና ለምዕራቡ ዓለም ይህን በማደረግ ሊያስተላልፈው የሚፈልገው መልእክት ስቼው አይደለም። ሐቁ ግን፥ የድርጊቱ መንፈስ ሆነ ዓላማ ጤናማ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ድርጊቱ የሚታይ ውጤት ሊያስገኝ ያልቻለና የማይችል፣ ፍሬ አልባ ድርጊት መሆኑን ለመግለፅ፥ ውሳኔዉን ለመቃወምና በአስቸኳይ እንዲቆምም ለማሳሰብ ያለመ አጭር ጽሑፍ ነው።
ሐተታ፥ የተማረከ/የሚማረክ የጠላት ሰራዊት በምንም ዓይነት መልኩ ይሰለፍ በምን የመጣው፥ ሊገድል፣ ሊያጠፋና ሊያወድም ነው። በትግል ጥርሳቸው የነቀሉ የትግራይ የሰራዊት አመራር አባላት የጠላት ሰራዊት ሲማረክ/ሲማርኩ ከሞራልም ከህግም አንፃር ምን ማድረግ እንዳለባቸውና እንደሚገባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ባለሞያዎች ለመሆናቸውም የማያጠራጥር ነው። ሐቁ ይህ ከሆነ ዘንዳ፥ በጦርነት መሃል ሙርከኛን ማሰናበት ታድያ ምን አመጣው? ይህን እያደረገ ያለስ ማን ነው? ማለታችን ግን አይቀርም። አንድም፥ ጥያቄው ትክክለኛና ተገቢ በመሆኑ የሚመለከተው አካል እያደረገው ያለ ያደርግ ዘንድ ያስገደደበት ምክንያት አስመልክቶ ሊሰጠው የሚችል ምላሽ እንዳለ ሆኖ በዚህ ጽሑፍ ጉዳዩ ከትግራይ የፖለቲካ አመራር ባህሪይና ባህል በመነሳት እንመለከታለን። በማስቀደም ግን፥ ላለፉት 30 ዓመታት የትግራይ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ትግራይን ያለ ተቀናቃኝ በብቸኝነት ሲገዛ የመጣና የዘለቀ የህወሓት አመራር፥ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ሙርከኛ እየተሰበሰበ መንግስትነት የመሰረተ፣ ሰብስቦ ለወግ ለማዕረግ ባበቃቸው ሙርከኞች ለሞትና ለእልቂት የማገደን የህወሓት አመራር ዛሬም በ60ዎቹ ከማሰብ ስላልወጣ፥ ከሰላሳና ከአርባ ዓመታት በኋላም ተመሳሳይ ሂደትና መንገድ እየተከተለ ሲያበቃ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ መሆኑን ተረድተን ከድርጊቱ እንዲታቀብ የትግራይ የሰራዊት አመራር አባላትም ሃላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥርዬን አቀርባለሁ።
ቢቀናው፥ ሊያጠፋ፣ ሊያወድምና ሊገድል የመጣ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ከሞት ተርፎ በሙርኮ ከተሰበሰበ በኋላ በጦርነት መሃል ሙርከኛን በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት፥ ሃላፊነት የጎደለበት፣ የተፋለሰ፣ ግንዛቤ ማጣትና የእውቀት ድርቀት የሚፈጥረው፣ ዋጋ የሚያስከፈል ድርጊት መሆኑን ታውቆ በአስቸካይ ሊታረም ይገባል። በመሆኑም ይህ ዓይነቱ አጥፊ ድርጊት ሊወገዝ የሚገባው አጥፊ ተግባር እንጅ የሚያኮራና የስልጣኔ ምልክት ተደርጎ መወሰድም የለበትም። ሌላው ቢቀር ለሁለተኛ ጊዜ የተማረከ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ወታደር መኖሩንም እየሰማን ነው። ይህ ታድያ በትግራይ በኩል የሚታይ ነህዝላልነት እንጅ ጀብድ አይደለም። ተራው ሲቪል ማህበረሰብና ይህን እንደ ጀብድ የሚያስተጋቡ ዩቲበሮች የዚህ ዓይነቱ ፍሬ አልባ ድርጊት ጠንቅና መዘዝ ባይገባቸው ምንም አይፈረድባቸውም። ስቪል የፖለቲካ አመራር አባላትም በተመሳሳይ የጠላት ሰራዊት ከመማረክ ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ወደ ሚዘጋጅለት ስፍራ እስከማከማቸት ያለውን ሂደትና መስዋእትነት ምንኛ ፈታኝና አደገኛ እንደሆነ በተጨባጭ የማወቅ እድል ስለሌላውና ስለማይኖረው ይህን መሰል ጥፋት በጠራራ ፀሐይ ላይ ሲፈፅም አይደንቀኝም። በዚህ ጉዳይ ላይ በቀዳሚነት የሚመለከታቸው የሰራዊቱ አለቆች ግን፥ ሊያጠፋ፣ ሊያወድምና ሊገድል የመጣ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ከሞት ተርፎ በሙርኮ ከተሰበሰበ በኋላ በጦርነት መሃል ሙርከኛን በሰላም ግባ! ተብሎ ሲሰናበት ሲያዩና ሲሰሙ ቆመው መመልከት የለባቸውም፤ ድርጊቱም ሆነ ውሳኔው ትክክል አይደለም በማለት ሊያስቆሙት ይገባል።
አንድም፥ ይህን እያደረጉ ያሉ አፍቃሬ ኢትዮጵያ የህወሓት አመራር አባላት ለእነሱ ለብቻቸው ከሰማይ የተሰጠ፣ እነሱ ብቻቸው ከዓለም ተለይተው የተማሩትና የሚያውቁት ፖለቲካዊና ወታደራዊ እውቀት ባለቤት ካልሆኑ በቀር፥ በጦርነት መሃል ሙርከኛ በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት ለህልውናውና ለደህንነቱ ለክርብሩና ለማንነቱ እየተዋደቀ ያለ መንእሰይ ትግራይ በቀጣይነት እየከፈለው በሚገኝ የህይወት መስዋእትነት መቀለድ ብቻ ሊሆን ነው። በርግጥ፥ በታሪኩ ስህተቱን አምኖ መቀበል የማይሆንለትና ያልፈጠረበት፣ ከስህተት ሰፈር የማይታጣ፣ እኔ ብቻ ነው የማውቀው እያለ ሲመፃደቅ ለራሱ ገደል ገብቶ እኛንም ለዚህ ሁሉ ጦስ የማገደን፣ እየተሳሳትክ ነው ስህተትህን አስተካክል ሲባል ስህተት አያውቀኝም እያለ በስህተት ላይ ሲህተት ሲፈጽም ከአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ተንሳፎ ራሱን እንኳ ከእስርና ከሞት መታገድ የተሳነው የህወሓት አመራር ከዚህ ዓይነቱ ያልበሰለ፣ ተራ የሰፈር አተስተሳሰብና አስራር ጀርባ ለመሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። የትግራይ ህዝብም እንደ ህዝብ ለዚህ ሁሉ እልቂትና ሞት የማገደው የዚህ አመራር አቅመ ቢስነትና ራዕይ አልባነት ዛሬም ያሻውን እንዲያደርግ ከፈቀድንለት በእውነቱ ነገር ስህተቱ የእኛ ነው ሊሆን የሚችለው። ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ውሳኔ ሆነ ኦፕሬሽን በሚመለከት፥ ስራቸውም ኑሮአቸውም ለዚህ የተሰጡ፣ ሲነሱም ሲቀመጡም ጣቱ ለጦርነት እንደ ሰለጠነ ተዋጊ ጦረኛ ሰው የሚያስቡ፣ በልባቸውም በእምሮአቸውም እንደ ጦረኛ ተጋይ የሚመላለሱ የሰራዊት መሪዎች መተው አለበት። ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን የፖለቲከኞች ቢሆንም የሰራዊት አለቆቹ አስተያየታቸውን ተጠይቀው ይሁን የሚሉትን እንዲሆን አይሆንም የሚሉትን ደግሞ እንዲቀር ካልተደረገ አደጋ ላይ ነን። አንድም፥ አንድም ሲቪል የፖለቲካ ባለ ስልጣናት ሰራዊቱን ላልተገባ መንገድ ለፖለቲካዊ ዓላማ ሲያውሉትና መጠቀሚያ ሲያደርጉት ውጤቱ ግልጽ ነው፤ ከዚህ ቀደም ያደረሰብብን ኪሳራም የሚታወቅ ነው።
በጦርነት መሃል ሙርከኛን በሰላም ግባ! ብሎ በማሰናበት የምንለውጠው የኢትዮጵያውያን ጠማማና ምቀኛ ልብ የለም
የጠላት ሰራዊት አያያዝ በተመለከተ የሰለጠነ ዓለም የሚባለው የምዕራቡ ዓለም/ምዕራባውያንም ቢሆኑ አይደለም ድሮ ዛሬም ከ75 ዓመታት በኋላ፥ ፈርጣማ ወታደራዊና ቁጠባዊ ተከለ ሰውነታቸው ሁሉንም የማሳወርና ዝም የማሰኘት አቅም ፈጠረላቸው እንጅ የታሊባን ተዋጊ የያዝነው እንደሆነ አይደለም በሰላም ገባ! ተብሎ ሊሰናበት ቀርቶ ምን እንደሚደረገና እንደሚፈጽምበት ይታወቃል። ይህ ማለት ግን፥ እኛም ጓንታናሞ የሚመስል እስር ቤት ሰርተን አንድ በአንድ እናፅዳቸው እያልኩ እንዳልሆነ ግልጽ ለማድረግ እወዳለሁ። አንድን ሙርከኛ ተገቢ በሆነ ሁኔታ መያዝ፣ መንከባከብና መጠበቅ የህግም የሞራልም ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይም የትግራይ ህዝብና ሰራዊት የሚታሙ እንዳይዳሉ ወዳጅም ጠላትም የሚመሰክረው ሐቅ ነው። የእኔ ሃሳብ፥ ትግራይን ዳግም ለመውረር የዘመተ፣ የቀናው እንደሆነም፥ ሊዘርፍ፣ ሊያጠፋ፣ ሊያምፅ፣ ለያወድምና ሊገድለን የመጣ የኢትዮጵያ ይሁን የኤርትራ እንዲሁም ኢንተርሃምዌ የአማራ ሚኒሻና ታጣቂ ጦር ሜዳ ሲማረክ እንደ ሙርከኛ መብቱ ተጠብቆለት በልዩ ሁኔታ ወደ ሚዘጋጅለት ስፍራ እንዲገባ ተደርጎ የሆነ እስኪሆን ድረስ ማቆየት እንጅ ወጠምሻውን በጦርነት መሃል በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት ዕብደት የማይገልጸው ስህተት ነው ባይ ነኝ። የትግራይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር በጦርነት መሃል ሙርኮኞችን በሰላም ግቡ! ብሎ ማሰናበት ካለበትና ይህን የሚያድርግበት በቂ ምክንያትም ካለው፥ እየሸለለ የመጣ ወጠምሻውን ሳይሆን ድጋሜ ለጦርነትና ለወትድርና የማይበቁ ሰዎች ለይቶ በሰላም ግቡ ብሎ መላክና ማሰናበት ይችላል ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የሌሎቹን ተመክሮ ማየት ካለብን ራሽያን መመልከት እንችላለን። ራሽያ ከማረከቻቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው የዩክሬን ሰራዊት አባላት መካከል በጦርነቱ ክፉኛ የተጎዱና ዳግም ለጦርነት የማይበቁ በቁጥር አንድ መቶ የሚሆኑ ሙርከኞች በጦርነት መሃል በሰላም ግቡ! ብላ ማሰናበትዋን ይታወቃል። በጉዳዩ ጥልቀት ያላቸው በርካታ ባለ ሞያዎች እንደሚስማሙበት፥ ስድስት ወራት ያስቆጠረ የራሽያና የዩክሬይን ጦርነት ግጥምያው በዩክሬይን መሬት ይካሄድ እንጅ ራሽያ እያካሄደችው ያለ ጦርነት ከዩክሬን ጋር ነው የሚል እምነት የላቸውም። አንድም፥ እገሌስ እያደረግው አይደለም ወይ! እንዳይባል እንኳ በራሽያና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለ ጦርነት ኢትዮጵያ የጎረቤት አገራትና መንግስታት ጋብዛ በትግራይ ላይ የፈጸመችው ወረራና የከፈተችው ጦርነት ሁለቱም ጦርነት ከመሆናቸው በቀር በሌላ በምንም ዓይነት መልኩ የሚያመሳስል ነገር የለውም። በመሆኑም፥ በጦርነት መሃል ሙርከኛን በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት የትግራይ የፖለቲካ አመራር ስራው ሁሉ ግልጽነት የጎደለበት ከመሆኑ ባሻገር የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ የተሳሳተ ውሳኔና ድርጊት ነው። የኢትዮጵያ ሰራዊትና ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች በመላ ጳጵሱም ሼኩም ፓስተሩም ነቢዩም የትግራይ ህዝብ ጠላት ህዝብ ነው! ፈጽሞ መጥፋት አለበት ብሎ ትግራዋይ እንደ ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የነቀለ ህዝብና አገር ጋር ገጥመህ በጦርነት መሃል ወጠምሻ ሙርከኛ በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት ትክክል አይደለም።
ለአካለ መጠን ያልደረሱ፣ ጉልበታቸው የደከሙ ሽማግሌዎችና ንጹሐን እናቶቻችንና ሴት እህቶቻችን በማንነታቸው ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ ከገበያ ማኸል አይቀር ከቤተ ክርስትያን እየታፈሱና እህል ውሃ በሌለበት ስፍራም እንደ ዱቄትም እየተሰፈሩ በሚታጎሩባት አገር ላይ ቅጥረኛ ነፍሰ ገደይን ምክንያት እይደረደርክ በሰላም ግባ! ብሎ ማሰናበት የትግራይ ህዝብ ህመምና ሰቃይ ምኑ ያይደለ፣ ህሊና ቢስ ቁማርተኛ አመራር ብቻ ነው ሊውለውና ሊያደርገው የሚችለው። ምናልባትም ከዚህ ዓይነቱ የተሳሳተ ውሳኔ ጀርባ ሊኖር የሚችል ምክንያት በአገር ውስጥም በምዕራባውያን ፊት የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ያለመ ከሆነ ይህን በማድረግ የምንለውጠው የኢትዮጵያውያን በክፋት የጠቆረ፣ አመፀኛ፣ ጠማማና ምቀኛ ልብ እንደሌለ ቁርጣችን ልናውቅ ይገባል። ሐቁ፥ ግልጽና የማያወላዳ አቋም በመያዝ እንጅ እንደዚህ ዓይነት ፍሬ የሌለው ተግባር በመፈጸም የሚገኝ ፖለቲካዊ ሆነ ሌላ ትርፍ አሎ ብሎ የሚያምን አመራር ካለ ሌላ የከፋ ጥፋት ሳይፈጽም ከእንቅልፉ ቢነቃ ይሻለዋል።