ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: [email protected]

ቅምሻ፥ እንደው ግን ምን ይሻላል? በኦርቶዶክስ እምነት የሚሸቅጡ የኦርቶዶክስ እምነት “ተከታዮች” የአገሪቱን የዘመን እኩሌታ በፈላጭ ቆራጭነት ሲቀመጡ፥ ድህነት ጸጋ፣ ስልጣናችን ከሰማይ ነው/መለኮታዊ ነው፣ ንጉስ አይከሰስም ሰማይ አይታረም! እያሉ በእግዚአብሔር ስም የእግዚአብሔር ቤት ሳይቀር እየዘረፉ፣ ከድሃ ከህዝብ አፍ እየመነተፉ ራሳቸውን ከማደለብ ያለፈ ምንም የፈየዱት ነገር ሳይኖር እንዲሁ እሸልባል። የቆጡን አወርድ ብላ የብብትዋን ጣለች እንደሚባለው ኮሚኒስቱም ቢመጣ በተውሶ እውቀት አገር ምድሩን ደም ከማቃባት ያለፈ የፈየደው ነገር የለም። መጽሐፍ፥ “ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ዘለፋ ይበልጣል” እንደሚለው ሰዉ የወደደውን እምነት እንዲከተል ፈቅደው እኛ እንደሆን ግን ከሁሉም የለንም! ያሉን በገዙን ዘመን በዝርዝር ሊቀመጥ የሚችል መንግስታዊ ድክመቶቹና ግድፈቶቹ እንዳሉ ሆነው የአገሪቱን ሰላምና የህዝቦችዋን ደህንነት በተመለከተ ግን አንጻራዊ ሰላም የሰፈነበት ዘመን እንደ ነበር ሁላችን የሚያስማማ ሐቅ ነው። ይህም አለፈ። ባለፈው ዘመን የተገኘ የእምነት ነጻነት የበቀለና ያበበ፣ ነባሩን ሲወቅሱና ሲያንካስሱ የመጡ ክፉኛ የማንነት ቀውስ የጸናባቸው፣ በጌታ ስም የሚሸቃቅጡ፣ ጌታ ይባረክ ጌታ ይመስገን! ከአንደበታቸው የማይጠፋ የምላስ አርበኛች የሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት “ተከታዮች” ስልጣን ላይ ሲወጡ ደግሞ እንደ ሌሎቹ እንኳ ትንሽ ሳይሰነብቱ ይባስ ብሎ ያልላቡበት የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት የሚያግበሰብሱ፣ አፋቸው ሲከፍቱና ሲዋሹ ሰይጣን ራሱ የሚያስቀኑ፣ የእግዚአብሔር ስም በአደባባይ ያሰደቡ፣ ከዚህም አልፎም ድፍን ዓለም እጁን በአፉ እስኪጭን ድረስ ይሄው ምድሪቱን የግፍና የበደል በየዓይነቱ የደም ምድርም አደረጓት።


በሌላው በኩል፥ አገሪቱ የመምራት መለኮታዊ ስልጣን ያለን እኛ ብቻ ነን በማለት የሚታወቁ፣ ለአንዱ ጋላ ለሌላ ጥንቁር ሻንቅላ ሲሉ ዛሬ ላይ የደረሱ፣ ለአንዱ መጤ ለሌላው ሰማይ አምድ የለውም እስላም አገር የለውም እያሉ ለሰው ሁሉ ታርጋ እየለጠፉ ከማሸማቀቅና ከማሳጣት ያለፈ ስራ መሰርተው መለወጥን ያልፈጠረባቸው ምዋርተኞችና ተራጋሚዎች ስልጣን ላይ ሲወጡም ሲገፈተሩም መከራ የሆኑብን ዙፋን ላይ ሲመጡ በአገሪቱ የሰሩትና ያደረሱት ኪሳራ ይሄው እስከ ዛሬ ዕለት ድረስ አገሪቱና ህዝቦችዋ እንደ አዳኝ እያደነ ይገኛል። ሌላው ወደ ስልጣን ሲመጣ ደግሞ እንዴት እነስተኛ ህዝብ ይገዛናል ተባለና ገፈተርነው፤ ከእነዚህ ራቅ ያሉ ከዚህም ከዚያም ተፈልገው ሲመጡ ደግሞ ገሚሱ በራሱ እምነት የሌለው፣ ስራውን ከመስራት ይልቅ አቧራ ያልነካው ወንበር እየወለወለ ሌሎች በማስደሰት ቀኑን ማሳለፍ የሚሻና የሰው ታላላኪ ብቻ ሆኖ መኖር የሚያምርበት ሆኖ አገኘናቸው፤ ከፊሉ ደግሞ ሲያስጮኸው የኖረ ሀገራዊነትና ህዝባዊነት ሳይሆን የስልጣን ጥም ስለ ነበር ከተራረፈው ፍርፋሬ በጥቂቱ ሲወረወርለት እንደ ቡችላ የበላውን በልቶ ልቡን አጥፍቶ የሚተኛ ምንደኛ ሆኖ አየነው፤ እስከ መቼ ተገፍቼና ተገለልዬ እኖራለሁ እስቲ ባይ (ያልቀመሰ ወገን ይቅመስ ሲባል) ደግሞ፥ የቸኮለ ጅብ ቀንድ ይነክሳል እንደሚባለው በጸሐይ ፍጥነት ሊባል በሚችል ሰዎቹ፥ ቀዋሚም ተንቀሻቃሽም ህይወት ያለውም የሌለውም ከነነፍሱ የሚውጡ፣ ስጋን በልተው ዓጥንት የሚቆረጥሙ በሙስና የመረቀኑ ጆቢራዎች ሆነው አየናቸው። ጥያቄው፥ ምን ይሻልሃል? የሚል ነው።


የቀረው፥ ማለትም በዚህ ደረጃ ያልሞከረ ባለ ሙሉ ባለስልጣን የሆነ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነው። ይህስ ቢሆን ዕድሉን ቢያገኝ አገሪቱን ከድጡ ወደ ማጡ ይጨምራት ይሆን ወይስ ሰላምና ዕረፍት ያመጣ ይሆን? የሚለውን ጥያቄ አሁን በሙላትና በእግርጠኝነት ምላሽ ያለው ጥያቄ አይደለም። አገሪቱ፥ የድህነት፣ የምቀኝነት፣ የበሽታ፣ የሃለቀርነት፣ የጦርነትና የእልቂት ቤተ ሙከራ መሆንዋ አይቀር ዘንዳ፤ አንድም፥ ስለሚመጣው አዲስ ጉልበት በክፉም በደጉም ለመጻፍም ለመናገርም ያመች ዘንድ ይሞከር/ስፍራውን ይረከብና እንየው። ደግሞም አይቀርም። ይዞብን የሚመጣ በተመለከተ ግን አሁንም እንደ ጎረቤት ህዝብ አብረን አናየዋለን።

የጽሑፉ ዓላማ፥ በተለይ በውጭ ዓለም ለምትገኙ በትግራይ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ስር ለተሰባሰባችሁ ወንድሞችና እህቶች መሰባሰባችን በእውነተኛ መንፈሳዊ እውቀትና ምክር ለማበረታት፣ ለማጎልበትና ለማጠናከር፤ ለሚጠይቁንም ሁሉ መልስ ለመስጠት ይቻለን ዘንድ በመንፈሳዊ እውቀት ለማስታጠቅ፤ ላልቆረጣላቸውም ይቆርጥላቸው ዘንድ ለማሳሰብ ተጻፈ።

መሪ ቃል፥ “እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ
ይሆናል። ደግሞ እላችኋለሁ፥ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና” (ማቴ 18፥ 18-20)።

መንደርደሪያ፥ በመሪ ቃላችን እንዳነበብነው፥ በእግዚአብሔር ልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ ዘልአለማዊ ህይወት ወይም የክርስትና እምነት ማለት ሃይል ያለው ሃይል የሚያወርድ የተገለጠ የአማኞች ህይወት እንጅ የተጣለለ ህንጻ ወይንም የቁጥር ብዛት ማለት እንዳይደለ በግልጽ ከቃሉ እንረዳለን። በተጨማሪም፥ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና እንዲል ቃለ ወንጌሉ እንደ ማግኔት የእግዚእብሔር መገኘት በአማኞች ህይወት/መካከላችን የሚያመጣ፥ ጥንታዊት፣ ብሔራዊት፣ ታሪካዊት ወዘተ እየተባለ በሚለፈፈው እንጀባና በሚደለቀው ዳንኬራ ሳይሆን በልጁ በማመን በሚገኝ ጽድቅ በመላበስ የሚገኝ የልብ ንጽህናና ቅንነት መሆኑ ነው። ይህን መሰረታዊ የክርስትና እምነትና እውቀት ገንዘባችን ከደረግን ዘንዳ መንፈሳዊ መሰባሰባችን ሆነ ህይወታችን በተመለከተ የሌሎች ይሁንታና ፈቃድ የሚሻው ሳይሆን ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ መንፈሳዊ ስልጣንና በረከት እንደሆነ ተረድተናል ማለት ነው።

የትግራይ ቤተ ክርስትያን ማለት ምን ማለት እንደሆነና እንዳይደለ ከዚህ ቀደም ለህትመት በበቁ ጽሑፎቼ በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጌለሁ። ከብዙ በጥቂቱ ለማስታወስ ያህል ግን፥ የትግራይ ቤተ ክርስትያን ማለት በሓዋ ሥራ 2፥ 5-8 “ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፤ ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?” እንዲል የጌታ ወንጌል ዓላማና ተልዕኮ ከሰማይ በታች የሚገኙ ህዝቦች ሁሉ በቋንቋ የምስራቹን ቃል እንዲሰሙና ሁሉም በራሳቸው ቋንቋ የምስጋና አምልኮ እንዲያቀርቡ ነው። የትግራይ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ዓላማና ተልዕኮ በተመሳሳይ ከዚህ አምላካዊ ቃል የሚመነጭና የሚቀዳ ሲሆን የትግራይ ህዝብ በራሱ ቋንቋ ፈጣሪውን እንዲያመልክና እንዲያመሰግን ዕድል ከመስጠት ባሻገር “ሰይጣን ይሻለናል!” ብላ ከምታምን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ህብረት ሊኖራት ስለማይችል ነው። ይህ መልዕክት በአማርኛ የተዘጋጀበት ዓላማ ታድያ “አማርኛ የሰማይ ቋንቋ ነው” ብለው የሚምኑ፣ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የራሳቸውን ቋንቋ ጥለው በአማርኛ እንዲጠቀሙ የሚያስገድዱ ዘመን ያለፈባቸው ነፈዞች የበከተ እምነታቸው ከቅዥት ያለፈ ውሃ የማይቋጥር ለመሆኑና ቁርጣቸውን ያውቁ ዘንድ ታስቦ ነው። በተረፈ፥ የትግራይ ቤተ ክርስትያን ሲባል ሰምተህ ለምትበረግገውና አጉል መመጻደቅ ለሚስተዋልብህ ወገን፥ የትግራይ ቤተ ክርስትያን የሚለው ስያሜ በአማርኛ የተረጎምነው እንደሆነ ትርጋሜው፡ “ሰይጣን ይሻለናል” ከምትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንና አምልኮተ ሰይጣን ከሚሰብክ አጋንንታዊ ሲኖዶስዋ ክፍልም ህብረትም የለንም! ነው።

ሌላው፥ የትግራይ ቤተ ክርስትያን ማለት ምን ማለት እንዳይደለ የሚመለከት ነው። የትግራይ ቤተ ክርስትያን ሲባል እርግማንና
ማጉረምረም የለመዳቸው የኢትዮጵያ ሰዎች ሐሰተኛ ምላስ እንደሚያራግበው፥ የክርስትና እምነት በነገድ መነጽር ወይም በብሔር ማዕቀፍ መገደብ፣ ማየትና ማጠር ማለት ሳይሆን ሓዋሪያው ጳውሎስ፥ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር አልፎአል እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል” ሲል፤ ሓዋሪያው ጴጥሮስ በተመሳሳይ፥ “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ” እንዲል የትግራይ ቤተ ክርስትያን ሲባል እንደሌሎች አገራትና አብያተ ክርስትያናት መጠሪያ የህብረቱ ጉባኤ ስያሜ እንጅ ክርስትናን በነገድና በብሔር ማጠር አይደለም። የትግራይ ቤተ ክርስትያን ለምትሰጠው እውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎትና አምልኮ ለመካፈል የሚፈልግ ማንም ይሁን ማን በሮችዋ ክፍት ነው። በትግራይ ቤተ ክርስትያን የክርስቶስ ናትና ግሪኩም ቢመጣ ቻይናዊ አድሎና መገለል የለባትም። በነገራችን ላይ፥ “ኢትዮጵያዊነት ሰዎች ወደ መንግስተ ሰማይ የሚገቡበት ሰማያዊ የዘግነት ካርድ ነው” የሚል የልሃጫሞቹ የአማራ ልሒቃን የበከተ እምነትና ዘፈን እንዳለ ሆኖ የትግራይ ቤተ ክርስትያን ማለት እነሱ እንደሚሉት “ክርስትናን በብሔር ማንነት መገደብ” ከሆነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ማለትስ ምን ማለት ነው? ተብሎ ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ምላሽ የላቸውም። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ማለትማ “ክርስትናን በዘግነት ማንነት መገደብ ማለት ነው” እንደማይሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ለመደንደርደሪያ ይህን ያህል ካልኩ ዘንዳ በመቀጠል ደግሞ ሁለት አካላት ላይ በማተኮር ሁለት ዓበይት ርዕሰ ጉዳዮችን ለማሳትና ለመዳሰስ እሻለሁ። ይኸውም በቀዳሚነት፥ በአንድነት፣ በፍቅርና በኢትዮጵያዊነት ስም ለዘመናት የተሰበከው ሐሰተኛ ማንነትና በላዩ ላይ የተደገመበት የአውሊያ፣ የምዋርተኞችና የአስማተኞች ድግምት መተት የተነሳ ዛሬም ከእውነት ጋር መታረቅ ተስኖት እንዳነከሰ የሚገኝ የሚመለከት ሲሆን፤ በአንጻሩ ለዘመናት ሐሰተኛ ትምህርትና ማንነት ቢሰበክም እውነት ሲገለጥ ሳያመነታ ለእውነት ተሸንፎ የቀድሞ እሮጌ አስተሳሰብና አሰራር አሽቀንጥሮ የጣለ በትግራይ ቤተ ክርስትያን የተጠለለው ህዝብ የሚመለከት ይሆናል።

ዛሬም መንታ መንገድ ላይ ቆመህ ለምታመነታ ሁሉ፥

  • የእግዚእብሔር መንግስት ቀርባለችና ንስሃ ግቡ ተብሎ በሚነገርበትና በሚሰበክበት ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው፥ “ሰይጣን
    ይሻለናል!” ከሚሉ ውልደ በርባን፤
  • ጽድቁንና መንግስቱን ከመስበክና ከመመስከር ይልቅ የአንድ ለፌ ወለፌ ወስላታ ግለሰብ ዘፋን መስበክ ከሚቀናቸው፤ ለኢትዮጵያ መሞት ለተዋህዶ መሞት! ነው እያሉ የነውራቸው አራፋ እየፈቁ ህዝቡን ለጦርነት ለሞትና ለእልቂት ከሚማግዱ፤
  • በሐሰተኛ ስብከት ህዝብና አገር ለጥፋት የሚማግዱ እውነት የማይገኝባቸው በነፋስ የተወሰዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎችና
    ሁለት ጊዜ ከሞቱ ፍሬ አልባ በለሶች፤
  • በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ከሚዘብቱ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም ከሚጠብቃቸው ከወደቁ ተንከራታች
    ከዋክብትና ህዝብ ከህዝብ የሚለያዩ ሥጋውያን ከሆኑ መንፈስም ከሌላቸው ሰዎች፤
  • የትግራይ ካህናትና ዲያቆናት በግፍ ሲታረዱና በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ ገዳዮች ከምትሸልም፤
  • የትግራይ አብያተ ክርስትያናት አድባራትና ገዳማት በታንክና በዓረቦች ድሮን ሲወድሙና ሲፈራርሱ ደስታዋን የምትገልጽ አዲስ አበባ መናገሻዋ ያደረገች ጋለሞታይቱ የኢትዮጵያ ሲኖዶስና ቤተ ክርስትያን ጋር መተሻሸት ሳይሆን የሚረባህ አርቀህ መሸሽ ነው።

በፖለቲካ አመራር የተቀመጡ ፖለቲከኞች ሲዋደዱ ሻምፓኝ መራጨት ሲጠሉ ደግሞ እምነት የጣለባቸው ህዝብ ደም ማቃባት፤ ይህን አድርገው ሲበቁ ደግሞ እንደገና ተመልሰው እርቅና ሰላም አውርደናል ብለው ምንም እንዳልተፈጠረ አንድ መዓድ ላይ ተቀምጠው መተሻሸትና መሳሳቅ የምንኖርባት ዓለም ነባራዊ ባህሪይ ነው። ይህ ዓይነቱ ልማድ ትናንት የነበረ ነው ዛሬም ያለ ነው ለወደፊትም መቀጠሉ የማይቀር ነው ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር እውቃለን፣ የጌታ አገልጋዮች ነን፣ መንፈሳዊ አባትና መሪዎች ነን፣ ጳጳሳት ነን፣ ነቢያት ነን ወዘተ የሚሉ በእግዚአብሔር ስምና ክብር ሲመጻደቁና ሲማማሉ ጸሐይ የምትጠልቅባቸው ሰዎች የእግዚአብሔር መንግስትና ጽድቅ መስበክና መመስከር ትተው ህዝብ እርስበርሱ እንዲተላለቅና ደም እንዲቃባ ፊተዋራሪዎች ሆነው መዝመታዘው ይቅር ለእግዚአብሔር ተብሎ በምህረትና በይቅርታ ሊታለፍ ይችላል ይሆናል። “ሰይጣን ይሻለናል!” በማለት ምርጫቸው በይፋ በአደባባይ ግልጽ ያደረጉ የሃይማኖት መሪዎች የሚመራ ሰይጣዊ ሲኖዶስ በተመለከተ ግን “ሰይጣን ይሻለናል!” ሲል በተናገረበት ማይክራፎን በአደባባይ የእግዚአብሔር ምህረት ካለመነና ከአገልግሎት ካልታገደ ተናጋሪው ሆነ ሰይጣን ይሻለናል ባይዋ ቤተ ክርስትያን እርጉም ሆኖው የእርግማንና የርኩሰት ምንጭም እንደሆኑ ይኖራሉ። እንግዲህ አሁንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን የምትል ሰው ያለህ እንደሆነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንና ሲኖዶስ እያጠጠህና እያጋተህ ያለ የአጋንንት ትምህርትና የምዋርተኞች ሽንት ለበረከት ሳይሆን የዘልአለም ሞት ያለበት ርኩሰት መሆኑን ልታውቅ ይገባል።

ጆሮ ያለው ሁሉ ያድምጥ፥ የያዕቆብ ወንድም ሓዋሪያው ይሁዳ በጻፈው መልዕክት ቁ. 20 ላይ “እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ” እንዲል ሰውን በሰውነቱ መቀበል ተስናቸው በጥላቻ ሰክረው ለጥፋት ከተሰለፉ የኢትዮጵያ ሰይጣናዊ ሲኖዶስ ተደምረህ/ሽ ላለመጥፋት ራስህን/ሽን ልትለይ/ዪ ይገባል። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክት ላይ “ወዳጆች ሆይ ጣኦትን ከማምለክ ሽሹ” እንዲል ህይወት ይሻልሃልና ከጋለሞታይቱ ኢትዮጵያ ሽሽ። ለምን? (ቁ. 20) “ነገር ግን አህዛብ የሚሰዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲሰዉ እላለሁ ከአጋንንትም ጋር ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም። የጌታን ጽዋና የአጋንንት ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም” እንዲል (1ኛ ቆሮ. 10፡14) አሁንም የሚሻልህ “ሰይጣን ይሻለናል!” ከምትል ቤተ ክርስትያንና ሰይጣናዊ ሲኖዶስ አርቀህ መሸሽ ነው።


መጽሐፍ፥ “መንፈስ ሁሉ መርምሩ” ሲል በሌላ ቤት ያለ ማዶ የሰፈረውን መጠቆሙ ሳይሆን እጠገብህ ያለ፥ ዘማሪ ነኝ፣ ሰባኪ ነኝ፣
መምህር ነኝ፣ አጥማቂ ነኝ፣ ፈዋሽ ነኝ፣ ባህታዊ ነኝ፣ ጳጳስ ነኝ፣ ሊቀ ጳጳስ ነኝ እያለ ቢዝነስ የሚሰራብህና የሚያወናብድህ፣ ሰውና
እግዚእብሔር የማይፈራ ወመኔ የሚመለከት ነው። እነዚህ የተለያዩ ቀሚሶችና መጠሪያ ስሞች ከስማቸው ፊት ለፊት በማስቀደም
ንግዳቸውን የሚያጣጥፉ ግለሰቦች በሙሉ መገኛቸውና አድራሻቸው የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስምሪታቸው ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው። ሲነማ ቤትቶችና መሸታ ቤቶች ቁጭ ብሎ ጳጳስ ነኝ መምህር ነኝ የሚል ወረበላ የለም። ስጋ ለበስ አጽራረ ጽድቅ ያለው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው። ለጸሎትም ብትሄድ ለቀብር በቀንም በምሽትም ጥላ እያዞረ “ከሚቀበሉ ይልቅ የሚሰጡ ብጽአን ናቸው” እያለ ኪስህን ገልብጦ የሚዘርፍህ ያለ ባለ መስቀል ቁማርተኛ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ቁጭ ብሎ ነው። ከመርካቶ በሸመተው ማለፊያ ጨርቅ ቀሚስና ቆብ አሰፍቶ መስቀል በእጁና በአንገቱ አንጠልጥሎና ጨብጦ ስራውን ይሰራ ዘንድ የተሰማራ ነፍሱን ቀቅሎ የበላ ካድሬም መገኛው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ነውና ለራስህ ስትል ከጋለሞታይቱ አገር፣ የመተተኞችና የጠንቋዮች የአስማተኞችና የምዋርተኞች ስብስብ ከሆነው ሰይጣናዊ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ሽሽ።

መቆማችን ያለ ግብዝነትና ያለ ሽንገላ ይሁን

ሰው በባህሪይው በሃጢአት የወደቀ ማንነት ተሸካሚ በመሆኑ ራሱንና ባለ እንጀራውን ማታላል ስለተቻለው ብቻ ፈጣሪውን ጭምር ሊያታልልና ሊሸነግል የሚችል/እንደሚችል ሆኖ የሚሰማው ደፋር ፍጥረት ነው። በመሆኑም ዳዊት “የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ” በማለት ጌታ አምላኩን ሲለምንና ሲማጸን የምናነበው። እዚህም እዚያም መሄድና መርገጥ ሳይሻን፣ የቅርብም የሩቅም ይሁንታና ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልገን፥ እርስበርሳችን ተሰባስበን በቋንቋችን በፍቅርና በነጻነት ጌታ አምላካችን የምናመልክባት የትግራይ ቤተ ክርስትያን የምናቋቁምበት በርካታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያት አለን።

ጥያቄው፥ ምን ይህዘህ? ማንን ተማምነህ? ነው የትግራይ ቤተ ክርስትያን! እያልክ ያለኸው? የሚል ነው።

መጽሐፍ “እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” ያለ፥
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ ሙሽራዋ ክርስቶስ ኢየሱስን በመተማመን ከሆነ በእውነት ምስጉን ነህ፤ ደግሞም ትጸናለህ፤ የሚያናውጥህ አንዳች ሃይልም አይኖርም። እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ አንደበት “በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው” እንዲል ደግሞ ይህ ሁሉ ጩኸት ደብረጽዮን የሚመራው የትግራይ ፖለቲከኛ በመታመን (ፖለቲካውን ለማመላከት እንጅ ስለሌላ አይደለም) የሆነ እንደሆነ ግን ውጤቱ የጊዜ ጉዳይ ነው የሚሆነው። መልእክቴ ግልጽ ነው፥ እግዚአብሔር ዳርቻችን ሊያሰፋና ሊባርከን ከሆነ እንደ ጥላ ከሚያልፈው ጊዜያዊ አጀንዳና ጩኸት ራሳችን ልንለይና ልናርቅ ይገባል። እንደ ስያሜያችን በሰማያዊ በረከት ልንባረክና ልንበዛ፣ ደስም ሊለንና በመሰባሰባችን ሃሴት ልናደርግ የምንችለው በትግራይ የምትገኘው ቤተ ክርስትያን የትግራይ ናት! ብለን መቆማችን ሌላ ህቡእ ተልዕኮ ሳይኖረን በመንፈሳዊ ቅናት፣ በእውነትና በጽድቅ፣ ትክክል ስለሆነና ስለሚገባን፣ “ሰይጣን ይሻለናል!” ብላ የአብርሃም፣ የይሕሳቅ፣ የእስራኤልን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔርን ከምትሳደብ ቤተ ክርስትያንና ነፍሰ ገዳይ ከሆነ ሰይጣናዊ ሲዶኖስ ህብረት የለንም ሊኖረንም አይችልም ብለን አምነንበት፣ ያለ ግብዝነትና ሽንገላ ውግንናችን የእውነት ጸሐፊ ከሆነው ከእግዚአብሔር ብቻ ያደርግን እንደሆነ አሁንም፥ መጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” እንዲል በእውነት አናፍርም። አንድም፥ ያለ መንፈስ ቅዱስ መገኘት የእግዚአብሔር ስራ መስራት፣ ሀገርና ህዝብ የሚባርክ መንፈሳዊ ተግባራት ማከናወን ስለማይቻል የትግራይ ቤተ ክርስትያን ብለን እርስበርሳችን ስንሰባሰብ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ይዘንና ታምነን ሊሆን ይገባል። ከዚህ ውጭ ያለው ና ሊኖር የሚችል ምክንያት ሁሉ ታድያ ወንዝ የማያሻግር ሸክምም ነው።

ሌላው፥ የአማኞች ጉባኤና ህብረት የሆነችው ቤተ ክርስትያን ለመምራት ሆነ የክርስትኖች መሰባሰብ ለማስተባበር ቀደም ሲል እንደ
ተጠቀሰው ለቤተ ክርስትያን የተሰጠ መንፈሳዊ ስልጣንና ሰማያዊ ጸጋ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የሰው አእምሮ የሚያልፍ መንፈሳዊ ስልጣናችን በሚገባ መጠቀምና መገለጥ መቻል አለብን የሚል ነው። አለዚያ ትርፉ መላላጥ ነው የሚሆነው። ይህን እንወቅ፥ የትግራይ ቤተ ክርስትያን፥ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆኖ ቀጠለች አልቀጠለች የትግራይ ህዝብ ፈጣሪው በቋንቋው የማምለክና የማመስገን መብት ያለው ህዝብ ነው። ፖለቲከኞቻን ፌዴራል ሲሉ ፌዴራል፣ ትግራይ ሲሉን ትግራይ! ማለት ለእናንተ አእይንተ እግዚአብሔር ለሆናችሁ ለእግዚአብሔር ካህናት የተገባ አይደለም፤ ነውርም ነው። የፖለቲከኞቹ በሽታ በእናንተ ላይ አይሰልጥን። እንደዚህ ዓይነት የዥዋዥዊ ፖለቲካም እግዚአብሔር ከእናንተ ከቅዱሳኖቹ ያርቀው። አንድም፥ ቤተ ክርስትያን ፖለቲከኞች ሲሰበሰቡ የምትሰበሰብ እርስበራሳቸው ሲናቆሩና ሲለያዩ ደግሞ እንዲሁ የምትናቆርና የምትለያይ ጉባኤ አይደለችምና።

መጽሐፍ፥ “ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋልም ይጋርድሃል” እንዲል በትግራይ ቤተክርስትያንና በፖለቲከኞቻችን መካከል ያለውና ሊኖር የሚገባ ግኙንነት በተመለከተም አንዱ በሌላው ላይ ጥላውን እንዳያሳርፍ፣ ተገዢና መጠቀሚያ እንዳይሆን አሁንም ጥንቃቄ ማድረግና በንቃት ሃላፊነታችን መወጣት ይገባል። በተለይ እናንተ መንፈሳውያን መሪዎች መጽሐፍ “በዋጋ ተገዝታችኋል፤ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ” እንዲል አካሄዳችን ሁሉ በእውነትና በጽድቅ ይሆን ዘንድ እመክራለሁ። ሐቁ፥ በሰላም ጊዜ ሆነ በጦርነት ጊዜ ሁለቱም አካላት ከተሰመረላቸው መስመር አልፈው የሚፈጽሙት ማንኛውም ዓይነት ግኙንነት ለማንም የማይጠቅም ይልቁም የጥፋት መንገድ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ለቤተ ክርስትያንም ለፖለቲከኞቻችንም የሚበጅ ታድያ ሁለቱም የየራሳቸው ስራ ሲሰሩና የተጣለባቸው ሃላፊነትና ግዴታ በአግባቡ መወጣት ሲችሉ ብቻ ነው። አገርም ህዝብም ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው አሁንም ሁሉም የየራሱ ስራ ሲሰራና ሃላፊነቱን በትጋት ሲወጣ ነው። ፖለቲከኞቹም ቢሆኑ ተጠቃሚዎች የሚሆኑ ቤተ ክርስትያን – የቤተ ክርስትያን ስራ (መንፈሳዊ ሃላፊነትዋን) ስትሰራና ስትወጣ ብቻ ነው። በነገራችን ላይ፥ የመንግስታትና የፖለቲከኞች ውድቀትና ድቀት የሚጀምረው ባለስልጣናት የወደዱትና ያሹትን ማድረግ እንደሚችሉ በማመን ከተሰጣቸው የስልጣን ገደብ አልፈው ጉልበታቸውና ስልጣናቸው መከታ በማድረግ በነገር ሁሉ ፈላጭ ቆራጭ መሆን ሲቃጣቸውና በእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ሳይቀር እጆቻቸው ስያስረዝሙ ነው። አገርና ህዝብም በዚህ ልክና መጠን የሚከስሙ መንፈሳውያን መንፈሳዊ ሃላፊነታቸውን ጥለው የካድሬ ስራ በመስራት ላይ ሲጠመዱ ነው። አግኝተው ያጡ ሰዎች ምን እያልኩ እንደሆነ በትክክል ይገባቸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በሁሉም ዘንድ ሊታውቀ የሚገባ ሌላው ሐቅ የእውነተኛ ካህንና እውነተኛይቱ ቤተክርስትያን የስልጣን ምንጭ
በሚመለከት ይሆናል። የቤተክርስትያን/የካህን የስልጣን ምንጭ የሰው ሃሳብ አይደለም። የአንድ መንግስት ስልጣን የሚመነጨው የሰው ሃሳብ ከሆነው እንደየ አስፈላጊነቱ የሚሻርና የሚሻሻል ህገ መንግስት ነው። የቤተክርስትያንና የካህን የስልጣን ምንጭ በአንጻሩ ለብዙዎች ሞኝነት ከሚመስለው ከላይ ከሰማይ ነው። የቤተክርስትያንና የካህን ስልጣን የሚመነጨው፥ የመኳንንትና የስልጣናት ሁሉ ባለስልጣን ከሆነው፣ ብቻውን ፈጥሮ ከሚገዛ፣ በምድር ክበብ ላይ የተቀመጠ፣ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድር የእግሬ መረገጫ ናት ያለ ከእግዚአብሔር የሚመነጭ ነው። አሁንም ለሁሉም ግልጽ ሊሆን የሚገባ ሐቅ ቢኖር፥ ቤተ ክርስትያን ማለት የፌደራል ተቋም እንዳይደለች ሊገባን ይገባል። ቀለል ባለ አማርኛ፥ በትግራይ የምትገኘው አለም አቀፋዊት የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን የትግራይ ናት። ከዚህ አልፋ የሌላ የማንም ልትሆን አትችልም። መንፈሳዊ እንቅስቃሴዋ በተመለከተም አሰራርዋ ሊገመግም፣ ሊፈትሽና ሊወስን የሚችለው አካል ቅድሳት መጻሕፍት መሰረት አድርጎ የተቋቋመው የካህናት ጉባኤ አንድም የትግራይ ሲኖዶስ ብቻ ይሆናል። የትግራይ ፖለቲካዊ መጻኢ በተመለከተ የትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ ስፍራውና ቦታው ራሱ ይወስናል፤ ቤተ ክርስትያን በተመለከተ ግን አሁንም ደግሜ እላለሁ በትግራይ የምትገኝ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የትግራይ ናት!
ተወደደም ተጠላ፣ ተስማማን አልተስማን፣ ይመቸን አይመቸን፣ ይክፋን ይድላን፡ በድምጽ ብልጫ የሚወሰን የቤተ ክርስትያን ህልውናና መንፈሳዊ ጉዳይ እንደሌለ ግልጽ ሊሆንል ይገባል። እውነት ነው፥ ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፋዊት ናት። ይህ ማለት፥ ቻይናም ደቡብ አፍሪካም ህንድም አሜሪካም ያለው በእምነት የሚመስለን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ወንድሞታችንና እህቶቻችን ናቸው። እንደ አማኞችም አይደለም በእምነት የሚመስለን ግለሰብና ቡድን/ህዝብ ቀርቶ ሌላውም ቢሆን ደስ እያለን የመውደድና የመቀበል ግዴታ አለብን። ሰውን በሰውነቱ መቀበል ክርስትያናዊ ግዴታችን ነውና። ከማንነታችን የተነሳ የሚያገሉን፣ ሲያዩን ሆነ ስማችን ሲጠራ ደም የሚያስቀምጣቸው፣ ቅናትና ምቀኝነት የቀን እረፍት የሌሊት እንቅልፍ የሚያሳጣቸው፣ ሞት የሚመኙልን እምነት አልባ ሃይማኖተኞች ምቀኞችና ምዋርተኖች ግን የመቀበል ሆነ ከእነርሱ ጋር ህብረት የማድረግ ገዴታ የለብንም። ለምን? እንደዚህ ያሉ የበግ ለምድ የለበሱ፣ አብ ያልተከላቸውና ጠላት የዘራቸው ሰዎች ለመንፈሳዊ ህይወታችን ደህንነት ጠንቅና አደጋ ስለሆኑ ነው። በመሆኑም፥ ለራሳችን መንፈሳዊ ደህንነት ሲባል ትግራዋይ ሁሉ ከጋለሞታይቱ ኢትዮጵያና ሰይጣናዊ ሲኖዶስዋ አጠገብ ልንርቅና ልንሸሽ ይገባል።

ከዚህ ሁሉ ግፍና በደል በኋላም ቢሆን ዛሬም ድረስ ከአሮጌ አስተሳሰብና የበከተ እምነት ተሰፍተህ ለቀረሃኸው፣ ዛሬም መንታ መንገድ ላይ ቆመህ ለምታመነታ ደግሜ እላለሁ፥ ዛሬ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የምትለው ሃለኸው በእውነቱ ነገር እውነት ስለ ያዝክና ስላለህ ሳይሆን እንዳንድህ ስግብግብነትና ራስ ወዳድነት ስለጸናብህ፣ ገሚስህ በመንፈሳዊ የእውቀት ድርቀት ስለ ተመታህና ቅድሳት መጻህፍት የሚያስተምሩን ትምህርት ባለማወቅህ እንደሆነ ስጽፍልህ በታላቅ በአክብሮት ነው። ሰው ከእግዚአብሔር የተሻለ ሃሳብ የለውም ሊኖረውም ስለማይችል መጽሐፍ መፍትሔው መሸሽ ነው ብሎ ሽሽ ሲልህ ጨርቂ ማቂ ሳትል ልትሸሽ በተጋባ ነበር ዳሩ ግን ክፉ አመል አልቆረጥ ብሎህ ይሄው ዛሬም መንታ መንገድ ላይ ቆመህ ታመነታለህ። በተረፈ፥ ትግራዋይ ሆኖ ከእግዚአብሔር እውነት ይልቅ የጋለሞታይቱ የኢትዮጵያ የመተትና የድግምት ሐሰተኛ ፍቅር አስምጦት ዛሬም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚል ባለአውሊያ ሊቀጳጳስ ይሁን ቄሰ-ገበዝ በማሃከላችሁ የተገኘ እንደሆነ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቆጥራችሁ አውጣችሁ ጣሉት። እንደዚህ ያለ ከእግዚአብሔር የጽድቅ መንግስት ይልቅ ተላላ ለሆነ ሰው መንግስትነት የቆመ፣ ስለ እውነት ለመቆም አቅምና ጉልበት ያጣ፣ በመንፈስ ቅዱስ ያልተጠመቀና ነፍሱን የሸጠ ምንደኛ ከሚበጀው ይልቅ የሚፈጀው ስለሚበዛ ቆርጣችሁ ልትጥሉት ይገባል።

ማሳረጊያ

በልጁ በማመን የሚገኝ የዘልአለም ህይወት ተካፋይ የሆንክ የእግዚእብሔር ካህንና ህዝብ ሆይ ስማ፥ መጽሐፍ፥ “እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው። እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ” እንዲል (1ኛ የጴጥ 2፥ 7-9) በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እውነተኛ እምነታቸን ለዓለም ሁሉ ይገለጥ ዘንድ የምንገለጥበት ሰዓት አሁን ነው። ስለ ህዝባችንና ከተሞታችንም ቢሆን፥ ትግራይ ሰው የደረሰበት ደረጃ ደርሳ ለህዝቦችዋ የእረፍት ምንጭ ለትሆን የምትችልበት ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ሊኖር አይችልምና ከእንቅልፍህ ንቃ።

በላያችን ስለ ተፈጸመብን፣ ስለ ሆነብንና ስለ ደረሰብን ሞትና እልቂት ሁሉ ወደኋላ ተመልሰን የምንመልሰው ህይወት፣ ሀብትና ንብረት የለም። የሆነብን ሁሉ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ሆናል። እንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ሆነብንና ስለ ተፈጸመብን ነገር እያነሳን ደጋግመን ብናወራና ብንዘፍን ደግሞ ጊዜያችን በከንቱ ከመፍጀትና ከማባከን ያለፈ ምንም ትርጉም ያለው ነገር አይደለምና ለኛ የሚሻለውንና የሚረባንን ለማድረግ ልንበረታ ይገባል። አሁን ያለፈውን ሁሉ ከኋላችን ትተን ወደ ፊት መሄድና መገስገስ ይገባናል። አንድም፥ የወንድሞቻችንና የእህቶቻችን ሞትና መስዋእትነት በከንቱ እንዳይቀር፣ ስለ ህልውናችንና ደህንነታችን ስለ ክብራችንና ማንነታችን ህይወታቸውን የገበሩ የትግራይ ወንዶችና ሴቶች ደምና አጥንት መታሰቢያ ይኖረው ዘንድ፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራትና መንግስታት በዝግ በር መክራና ዘክራ ስታበቃ በሐሰተኛ ትርክና ውንጀላ በላያችን ላይ የፈጸመውች ወራራና ከዚህ የተነሳም በህዝባችን ላይ ለፈጸመችው በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም የጦርና የዘር ማጥፋት ወንጀል በታሪክ መዝገብ ይጻፍና ይታወስ
ዘንድ ትግራይዋይ ሁሉ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም መጽሐፍም፥ “ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?”
እንዲል (ገላትያ 4፥8)፤ “ሰይጣን ይሻለናል!” እያሉ እንደበታቸው በእግዚአብሔር ከሚያላቅቁ ውልደ በርባንና ዘርአ-ያዕቆብ ከሆኑ
መተተኞችና ምዋርተኞች ራሳችንን ፈጽመን በመለየትና በማራቅና ትግራዋይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው የሞትለት እውነተኛ የትግራይ የክርስትና እምነት በመመለስ ለህዝባችን መንፈሳዊ መነቃቃት፣ መለወጥና መፈታት ምክንያት ልንሆን ይገባል በማለት ጽሑፌን እዚህ እቋጫለሁ።

“ዓሰርተ ትእዛዛት ዳግመ ህንፀት ትግራይ” በሚል በትግርኛ የተዘጋጀ መጽሐፍ አማዞን ላይ የመጽሐፉን ርዕስ በመጻፍ ማግኘት ይችላሉ።

By aiga