በፍርድ ቤት ውሳኔ ወደ ሰራቸው ከተመለሱት መካከል 10 ጋዜጠኞች ፣ 7 የቴክኒክ ባለሙያዎች ፣ 2 የፕሮሞሽን ክፍል ሰራተኞች ባጠቃላይ 19 እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።

የፍርድ ቤት ወሳኔ ተከትሎ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም በትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሻለ በቀለ ተፅፎ ማህተም ያረፈበት ደብዳቤ ፦

” ለስቪል ስርቪስ ኮሚሽን ፍርድ ቤት ባቀረባችሁት አቤቱታ መሰረት በቀን 03/12/2015 ዓ.ም በደብዳቤ ይ/ፍ/መ ቁጥር 001650/2015 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ወደ ስራ ምድባችሁ እንድትመለሱ ተወስኗል። ” ይላል።

ጉዳዩ መቼና ? እንዴት እንደተጀመረ ?

የቀድሞው የትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አስተያየቱ አጋርተዋል።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ህዳር 19/2013 ዓ.ም የፌደራል መንግስት መቐለን ሲቆጣጠር በክልሉ ከነበሩ ድምፂ ወያነ ትግራይና የትግራይ ቴሌቪዥን ጣብያዎች መሃል ድምፂ ወያነ ባጋጠመው ውድመት እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም ሰርጭት ሲያቆም ከ8 ወራት ጦርነት በኃላ ሰኔ 21 /2013  ዓ.ም የትግራይ ሃይሎች መቐለን መልሰው ሲቆጣጠሩ ስራ አስኪያጁ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ጨምሮ 46 ባለሙያዎችና ደጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ‘ ከጠላት ተባብራቹሃል ‘ የሚል ግምገማና ክስ ቀርቦባቸው ታስረዋል፣ ከስራ ተባረዋል ፣ ትግራይ ለቀው የወጡም አሉ።

‘ ከጠላት ተባብራቹሃል ‘ የሚል ክስ ቀርቦባቸው ከታሰሩና ከስራ ከተባረሩት  መካከል 19 ጋዜጠኛችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ለሁለት አመታት ሲከላከሉና ሲከራከሩ ቆይተው ፍርድ ቤት አዘግይቶም ቢሆን ወደ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ መወሰኑ የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ‘ሕጊ ስዒሩ ‘ ‘ህግ አሸንፈዋል ‘ ሲል ገልፆታል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ፣ ከመቐለ ከሚገኙ ቤተሰቡ ተለያይቶ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ካሕሳይ ብሩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ወደ ስራው ይመለስ እንደሆነ ላቀረብንለት ጥያቄ ‘ ከነበርኩበት የሃላፊነት እርከን ሁለት ደረጃ ወደ ታች ወርደህ ስራ በመባሌ እና አሁን በተቋሙ ካለው ማኔጅመንት ለመስራት ፍላጎት ስለሌለኝ አልመልስም ‘ ብሏል።

በፍርድ ቤት ትእዛዝ ወደ ስራ ምድባቸው እንዲመለሱ ከተወሰነላቸው 19 ጋዜጠኞችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በተጨማሪ በ2013 ዓ.ም በቀጥታ  (በሃንቲንግ) የተቀጠሩ 8 ጋዜጠኞች ወደ ስራ መደባቸው እንዲመለሱ ወደ ክልሉ እንባ ጠባቂና ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አመልክተው መልስ በመጠበቅ ላይ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ለማወቅ ችሏል።

  TIKVAH ETHIOPIA

By aiga