ሙሉጌታ በሪሁን
አንድ ሃገር እንደ ሃገር የሚያስቆሙት ባህል፣ታሪክ፣ቋንቋና፣ጆኦግራፊያዊ መልከአ ምድርን ያጠቃለለ ሲሆን፣ የነዚህ እሴቶቹ ጥምር ውጤትና፣በውስጡ ያሉትን የብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ድምር ውጤት፣የአገርነትን ክብር እና ይዘት ይኖሩታል።ከዚህ አኳያ ኢትዮዺያም “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ” እንዳሉት አባይ አባይ የሚያደርጉት የተለያዩ ጅረቶችና፣ወንዞች ወደ ውስጡ ተቀላቅለው አባይ ወንዝ እንደሚያደርጉት ሁሉ።በተለይ ከድህረ ንጉስ ሚኒሊክ የተፈጠረችው ኢትዮዺያም በውስጧ ያካተተቻቸው የብሄር ብሄረሰቦች ድምር ውጤት ነች።
እነዚህ ሕዝቦች እንደየ አከባቢያቸው የየራሳቸው ባህል፣ቋንቋ፣ታሪክና ማንነት ያላቸው እስከ ሆኑ ድረስ፣ ሃገሪቱ በውስጧ አጭቃ የያዘቻቸውን ሕዝቦች፣ፖለታካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ስነልቦናዊና፣ዜግነታዊ ክብራቸውን የመጠበቅ አለም አቀፍ መብትና ግዴታም አለባት።እርግጥ ነው የሰው ልጆች እንደመሆናችን መጠን፣አንዱ በአንዱ ጫንቃና፣ትከሻ ተቆናጦ ሌላዉን ረግጦ የመግዛት አባዜ፣አሁንም ቢሆን በ21ኛው ክፍለዘመን እጅግ በተራቀቀ መንገድ ይፈጸማል።
በጣም የሚገርመው ግን እኛ ኢትዮዺያዊያን ስለራሳችን ስንናገር፣ከሰው ዘሮች በፊት የተፈጠርን።ከ4ሺ ዓመት በፊት ስልጣኔ የነበረን።በአለም ውስጥ አሉ ከሚባሉ 4 ሃያላን ሕዝቦች ነበረን። የአክሱም ስልጣኔ ባለቤቶች ነበረን፣ የራሳችን ፊደልና፣ቁጥሮች ያሉን። የመጀመሪያዎቹ የመገባበያ ሳንቲሞች የፈጠርን እያልን።”ማሞ ሌላ፤መታወቅያው ሌላን” የሚለውን ስነምግባር መለየት አቅቶን ያልሆነውን፣የማይመለከተንን ”ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እየሄድን፣ ትክክለኛው ማንነታችን ሳናውቅ፣ በነገሩን የበሬ ወለደ ታሪክ እየተነዳን። አንዱ አንዱን አጥፍቶ የራሱ ያልሆነውን ማንነት ለመውረስ እየተላለቅን፣የአለም መሳቅያ መሳለቅያ የሆንን ሕዝቦች ነን።
እስኪ የዛሬዋ ኢትዮዺያ በተለይ ከውድቀተ ዘመነ አክሱምና፣ ከድህረ የአገዎች ስልጣኔ በኃላ እያቆጠቆጠ የመጣው የአማራይቱ ኢትዮዺያ አመሰራረትና የጭካኔ አገዛዝ፣በመጠኑ እንመልከት።እርግጥ ነው ገዢዎች የሚሰንዱት ታሪክ ለራሳቸው በሚያመች መንገድ ፣የፈለጉትን ጨምረውና ቀንሰው ቢሆንም፣የታሪኮቻቸውና፣ትርክቶቻቸው እውነተኝነት የሚረጋገጠው ግን መሬት ላይ በሚገኙ፣በሚታዩ፣በሚዳሰሱ ማስረጃዎች ይሆናል።
የአክሱማዊያን ስልጣኔ፣ታሪክ፣ባህል፣ተውፊትና፣ጀግንነት በተለያዩ ማስረጃዎች መሬት ላይ የሚገኙ ስለሆኑ እንደ ቀደምት የስልጣኔ ፈር ቀዳጆች መሆናቸውን ያስረግጥልናል።ዳንኤል ክብረት የፈለገውን ቢዘርፍ፣የፈለገውን ቢሰብክ፣ ዮዲት ጉዲት ያፈረሰችውን ሃወልት ተሸክማው እንዳልሄደች ሁሉ፣በትግራይ ውስጥ ያሉት ቅርሶች ቢወድሙ እንኳን ታሪካቸውን ልትሰርዘው አትችልም። የሰው ወርቅ አያደንቅ ቢሆንባቸው መሰለኝ “ጣልያኖቹም” የሰረቁትን ሃወልት ተሸክመው አምጥተው በቦታው የተከሉት።የትናንት ሆነ የዛሬ ታሪክ የኛ የሆነውን ለጊዜው ቢመስላቸም፣ የኛ የኛ ነው። አባይና የህዳሴ ግድብ ሲነሳ፣ ጁንታው መለስ ዜናዊ፣ ጁንታው የትግራይ ሕዝብ ፈርቀዳጅነቱ ማንም አይነጥቀውም።አስከነአባባሉ “አባይን የደፈረ”
ከብዙ የታሪክ መፃህፍት እንደምንረዳው ከዘመነ አክሱማዊያን በመቀጠል፣በንጉስ ላሊበላው የአገው ስርወ መንግስት የቀጠለው የአገዎች ስልጣኔና ታሪክ የሚገባውን የቀደምትነት እውቅና ባይሰጠውም፣በተስፋፊዎቹ የአማራ ነገስታት፣እንደ ቅማንትና፣ ስናሻዎች፣ አገዎችም በአማራ እየተዋጡ እስከመጥፋት ደርሰው ነበር። ነገር ግን መሬት ላይ ባሉት የቀደምት አያቶቻቸው
ተገምብተው እንደ እንቁ ፈርጥ ደምቀው የአለምን ዓይን የሚማርኩት በየላሊበላዎቹ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣የታሪክ ባለቤትነታቸው ተረጋግጧል።ከውድቀተ ላሊበላ በኃላ እያቆጠቆጠ የመጣው፣ የሽዋውያን መሳፍንት ፍላጎት ደግሞ፣ እንደ አክሱማዊያንና፣አገዋውያን ሰርቶ፣ገምብቶ የታሪክ ባለቤትነትን መጎናጸፍ ሳይሆን፣የሌሎችን ታሪክ፣ባህልና፣ቅርስን በመበረዝ፣በመዝረፍ፣ ሰርቆ የበላይነትን መጎናጸፍን እንደ አላማ አድርገውት መጥቷል።
ለምሳሌ ከንግስና ዐፄ ይስሃቅ በ1407 ዓ/ም ጀምሮ እየተጋጋለ የመጣው የሰሜኖቹና፣የሽዋውያኑ ግጭት ብቅ ጥልቅ እያለ ቢቆይም፣በተለይ ደግሞ ከዘመነ ንጉስ ዘርአያቆብ ከ1426 እስከ 1460 ዓ/ም ለ34 አመት ግልጽ የሆነ ከፍተኛ የሃይማኖትና የቅርሶች ብረዛና ዝርፍያ በትግራይ ላይ ተካሂደዋል። ለምሳሌ በዘመኑ የነበሩትን “ሃይማኖታዊያን ተጋሩ” እንደነ “አባ እስጢፋኖስ” የመሳሰሉትን የሃይማኖት ሊቃውንት መጥቀስ ይቻላል።ደቂቀ እስጢፋኖስ በመባል የሚታወቁት የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት መምህራን ከ1400-1500 ዓ/ም የነበሩ የሃይማኖት ፈላስፎች ናቸው። እነዚህ የሃይማኖት አባቶች ግን በንጉስ ዘርአያቆብ ፍርድ ቤት ቀርበው ካለ ጥፋታቸው፣ ለንጉስ አልሰገዳችሁም በሚል ክስ ተከሰዋል።እነሱም እኛ የምንሰግደው ለአንድ ፈጣሪያችን እንጂ፣ ለሰው ልጅ አንሰግድም።በማለት ሲመልሱለት፣ንጉስ ዘርአያቆብ እንዴት እኔን አንተ ትለኛለህ ? እኔኮ ንጉስ ነኝ ? ቢለው አባ እስጢፋኖስ፣ሲመልስለት አይደለም አንተን፣ ለአምላካችንኮ አንተ እያልን “አምላካችን ሆይ በደላችንን ይቅር በለን” ምህረትህን ስጠን እያልን ነው የምንማጸነው። ላንተ ደግሞ እንጸልይልሃለን እንጂ፣ አንሰግድልህም። በማለት መልሶለታል።ከዛም መልሱ እንደ ድፍረት ተቆጥሮበት ከ7 ወር እስራት በኃላ፣ በንጉስ ዘርአያቆብ እስር ቤት እያለ ሂወቱ አልፏል።ከዛ በኃላ ንጉሱ፣ የደቂቀ እስጢፋኖስን ተከታዮች የሆኑ ካህናትና ቀሳውስት፣ ቁጥራቸው እስከ 6000ሺ የሚደርሱ ካህናት ከአንገት በታች ሰውነታቸው መሬት ላይ ቀብሮ፣ በፈረስ እንደሄደባቸውና፣ እንደገድሏቸው የቤተክህነት ታሪክ ይነግረናል። ምክንያቱም በወቅቱ ይሰጥ የነበረው ሃይማኖታዊ አስተምሮ፣ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ትክክለኛ ሃይማኖታዊ አስተምሮ ስለነበር፣ከዛ በኃላ ግን ዘርአያቆብ በነበረው እውቀትና የስነጽሁፍ ልዩ ችሎታ በሚፈልገዉ እየቀየረና፣ እየበረዘ ንግስናዊ ስልጣኑ፣ መለኮታዊ መልክ በማስያዝ ይሰብክና ያስተምርበት ጀመር። ለዚህ ሰነምግባሩም እጅግ ብዛት ያላቸው ካህናት አሰልጥኖና፣አስተምሮ ወደ ሰሜኑ የትግራይ ግዛት በማሰማራት የሃይማኖታዊ ብረዛ ስራውን አከናውነዋል።እንሆ ዛሬ በየ እምነት ቤቶቹ ተሰግስገው፣የፈጣሪን ትእዛዝ፣ለበደሉን ይቅር እንደምንል ሁሉ በደላችንን ይቅር በለን የሚለውን የፈጣሪ ቃል፣ጁንታ ከሚገዛን፣ሰይጣን ቢገዛን ይሻላል የሚሉ የአማራ ዻዻሳትና፣ካህናት እንደ አሸን ፈልተው።ሃይማኖቱን እንዳይኖሩት፣እየሰበኩ የገቢ ምንጭ ሆኖ ለማየት በቅተናል።
ዛሬ በኢትዮዺያ ምድር ከሽዋ አንኮበር፣ደብረብርሃን፣ደብረ ታቡር፣ጎንደርና ጎጃም የተስፋፋው የመጠቅለልና የማስገበር አባዜ፣በወቅቱ መገታት ስላልቻለ ብቻ ሳይሆን፣ከሰሜኑ የትግራይ ሕዝብ እምብርት የወጡትም ጭምር ሳይቀር ”የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ይሰራል እንጂ፣ታሪክ አይጽፍም” በሚል የተሳሳተ እምነትና አስተምሮ፣ ላለፉት 600 አመታት እየተደራረበ የመጣውን ችግር፣እራሱ የትግራይ ሕዝብና፣የትግራይ የሃይማኖት መሪዎች የተከተሉት የተሳሳተ መንገድ፣አካሄድም ጭምር ለዘመናት እየተከታተለ፣የሽዋ መሳፍንትም ሳይታክቱ፣የትግራይን ሕዝብ እያደከዩና፣በጋብቻ እያስተሳሰሩ፣ገዢዎችን በማስቀመጥ እስከ ዛሬ በተዛባ ሃገራዊ ማንነት፣በተበረዘ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ እዚህ ደርሰናል።
ለምሳሌ በ1770 ዓም በጎንደር ዘመነ መንግስት፣ስርአተ አልበኝነትና፣ኢሃይማኖታዊ ስነምግባር በመስፋፋቱ በወቅቱ የነበረው የጎንደር ንጉስ “ንጉስ እዮአስ”ስርአተ መንግስቱን ማስቀጠል ስላልቻለ፣ በወቅቱ የሰሜኑን ክፍል ሲያስተዳድር የነበረውን “ራስ ስሑል ሚካኤል” እርዳታውን ሲጠይቅ ራስ ስሑል ሚካኤል 20ሺ ወታደሮቹን አስከትሎ ወደ ጎንደር በመሄድ፣ ስርአተ መንግስቱን ቢያስተካክልለትም ቅሉ፣ንጉስ ኢዮአስ ቤተመንግስት ውስጥ የነበሩት የኦሮሞና፣የአማራ ተወላጆች በጠነሰሱት ሴራ፣ ራስ ስሑል ሚካኤል እንዲገደል ወስነው፣የንጉሱን ወንድም ከቻለ በሂወት፣ካልሆነ ደግሞ ሬሳውን ይዞለት እንዲመጣ አዘውት ከተንቀሳቀሰ በኃላ።የእዮአስ ስራዊት ከኃላ እንዲወጋው ተወስኖ ውግያው ቢጀመርም፣የንጉሱ ሚስት “ተዋበች” በሴራው ተበሳጭተው ራስ ስሑል ሚካኤልን ስላስጠነቀቛቸው፣እቅዳቸው ከሽፎ መጨረሻው የንጉስ እዮአስን ሂወት በስቅላት ቀጥፎታል።
ከዛም ራስ ስሑል ሚካኤል ጎንደርን ለ7ዓመታት ካስተዳደሩ በኃላ፣ ወደ ቀያቸው ወደ ትግራይ ተመልሰው እስከ ህልፈተ ሂወታቸው ኖሯል።
እንዲህ እያለ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ኢትዮዺያዊነት፣እንደ አንድ ሕዝብ ወይም አገር ሳይሆን፣ አንዱ አንዱን አጥፍቶ፣የአንዱን ታሪክና ቅርስ ወርሶና ዘርፎ፣ የራሱ የሆነ ማንነት ለመገንባት በሚመኝ ህልመኛና፣የለም የራሴንማ አሳልፌ አልሰጥም በሚል ሕዝብ፣ ፍጥጫ ውስጥ የተመሰረተች፣የተገነባች ኢትዮዺያ እንሆ ዛሬ በኔ፣ባንተ፣ባንቺ የሂወት ዘመን ደርሰን አሁን ለምንገኝበት የኢትዮዺያ ይዞታና፣ፖለቲካዊ ስርአተ አልበኝነት፣የካንጋሩ ፍርደ ገምድልነት የሰፈነባት። የሰራ የሚከሰስባት፣የዘረፈና፣የቀጠፈ የሚመሰገንባት፣የእንቆቅልሽ አገር እያየን ነው። ጀግኖች ስለሃገር የተዋደቁ የሚሰቀሉባት፣የሚረሸኑባት፣እንደነ በላይ ዘለቀ፣ጽሃፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተ ወልድ፣እንደነ አምባሳደር ስዩም መስፍን የሚገደሉባት። እንደነ ብርሃኑ ነጋ፣አንዳርጋቸው ጽጌ ትናንትና ኢትዮዺያን ከነግብጽና፣ ከነሻዕብያ ጋር ሆነው ሲሸጥዋት የነበሩት ደግሞ የሚሾሙባት የእንቆቅልሽ አገር ላይ ደርሰናል።
ለምን ? እንዴት ? እዚህ ደረጃ ላይ ደረስን ለሚለው ጥያቄ፣ በአንድ ቀን ወይም በአንድ አመት፣ ዘጭ ብለን እዚህ አለመድረሳችን የሚታወቅ ቢሆንም፣ ከላይ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት ከንጉስ ዘርአያቆብ እስከ የደርግ ውድቀት ያሉትን የሽዋ ባላባቶችና፣ መሳፍንት ከሰሜኑ ሕዝብ በተለይ “ከትግራይና ከዛሬዋ ኤርትራ፣የቀድሞዋ ባሕረ ነጋሽ” ጋር ያካሄዱትን ያልተቋረጠ የታሪክና የስልጣኔ ዝርፍያ፣እንደየ ነገስታቱና፣መሳፍንቱ ፍላጎት ኢትዮዺያና የሕዝቦቿ ቁጥሯና፣የቆዳ ስፋትዋ አንዴ ሲቀንስ፣አንዴ ሲጨምር፣የእንደኛው ሕዝቧና፣መሬቷ ሲሸጥ፣ሌላኛው ሕዝብና መሬት ሲጨመር፣ የሕዝቦች ፍላጎት ሳይካተትበት ገሚሱን በጉልበት፣ገሚሱን በማትሬዛ እየተሸጠች፣ እየተለዋወጠች አሁን ያለችውን ኢትዮዺያ ላይ ደርሰናል።
በጣም የሚገርመው ግን ኢትዮዺያዊያን፣ለወሬ ዳገት የለውም ሆኖ እንጂ ! ኢትዮዺያ ከዛሬ 4ሺ አመት ትጠቀምበት የነበረው ዘዴ በበሬ ማረስ ሲሆን ዛሬም በ21ኛው ክፍለዘመን ያው በበሬ ማረስነው አልተቀየረም። ዛሬ ኢትዮዺያ ከ44 ዩኒቨርሲቲዎች በላይ ቢኖሩዋትም፣አብዛኛው የገጠሩ ሕዝቧ ውሃ የሚቀዳው ከኩሬ ነው። አብዛኛ ሕዝቧ የመብራት አገልግሎት የለውም። የኢትዮዺያና፣የኢትዮዺያዊያን ስንክሳር በዚህ አያበቃም።ሃገሪቱ በዘመነ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ በአቶ መለስ ዜናዊ መሪነት፣ እጅግ በጣም ተስፋ ሰጪ የልማት ፕሮግራሞችና፣ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የታዩ ቢሆኑም፣በዲሞክራሲያዊ ስርአታዊ አስተዳደርና አመራር ከፊተኞቹ መሪዎች የተሻለ ለውጥ ቢታይም፣ድርጅታዊ የእዝ ሰንሰለት የተከተለ የከፋፍለህ ግዛ ስርአት በመሆኑ፣ ተመልሶ ኢ.ሕ.አ.ዲ.ግ
ከውስጡ በፈለቁ በራሱ አባላትና፣በውጭ ሃያላን መንግስታት በተለይ በአሜሪካ መሪነት ብትንትኑ ሊወጣ ችሏል።
የዚህ የመፈረካከስ ውጤት ደግሞ “የኦሮማራን” ጥምረት ፈጥረው የነበረውን የሕ.ወ.ሓ.ት የበላይነት ገርስሰው በመጣል፣ሕ.ወ.ሓ.ት ባንክና ታንካቸውን በሰላም አስረክበው ወደ መቐለ እንዲከትም አድርገዉታል።
ውድ አንባብያን ሆይ እዚህ ላይ እኔ የማቀርበው ጽሁፍ፣የምተርከው ታሪክ፣ብትግራዋይነቴ በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የዘር ማጽዳት፣ወንጀል በተመለከተ፣ እኔ ኢትዮዺያዊ ለመሆን የሚያስገድደኝ፣ወይም የምመኘው፣ዜግነት ባለመሆኑ፣ በሕዝቤ ላይ በደረሰው የጀኖሳይድ ወንጀል “ኢትዮዺያና፣ኤርትራ” እንደ ሃገር።አብይ አህመድና፣የብልጽግና ፓርቲ፣ከኢሳያስ አፈወርቒና፣የህግደፍ (ሻዕብያ) እንደ ፓርቲ ለአለም ፍርድ ቤት ቀርበው ብሰብአዊ መብት ጥሰትና፣በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው እስኪ ቀርቡ ትግሌን እየቀጠልኩኝ።ኢትዮዺያ የሚባል ስም ከማልሰማበትና ከማፍርበት ደረጃ ላይ ስለደረስኩኝ፣የኢትዮዺያዊነት ሽፋን በማጋለጥ የተሰራውን አስነዋሪና አሳፋሪ የኢትዮዺያ እንደ አገር፣ ኢትዮዺያዊያን እንደ ዜጎች ማድረግ የነበረባቸውን ሳያደርጉ በመቅረታቸውና፣ለዘር ጭፍጨፋውም የበኩላቸውን ድጋፍና፣የመዋጮ አስተዋጽኦ ያደረጉ ስለሆኑ የወጋ ቢረሳም የተወጋ አይረሳምና።ላንረሳው በስነጽሁፍና፣በዶክመንተሪ ዘግበንና፣ሰንደን ለትውልድ እንደምናስተላልፈው መታወቅ አለበት። በመጨረሻም እኛየትግራይ ሕዝቦች እንዴት ብለን ከነዚህ ሕዝቦች ጋር አብረን ኖርን ? ለሚለው ጥያቄ የሆነ ሊያሳምነኝ የሚችል መልስ በለማግኘቴ፣ አለመቃወም የድርጊቶቹ ደጋፊነት የሚያሳይ ምልክት ነው ሲባል ብሰማም፣የኢትዮዺያ ሕዝብ ግን በሚወክሉት ፖለቲከኞች፣በሚያምናቸው የሃይማኖቱ አባቶች፣በማያደንቃቸው አዝማሪዎችና፣ተዋንያን፣በሚመካባቸው ፕሮፌሰሮችና፣የሚዲያ ባለሙያዎች እንዲሁም እሱን በሚወክሉ የፓርላማ አባላት የትግራይን ሕዝብ ከገጸ ምድር ለማጥፋት፣ ከመከላከያችን ጎን ነን በማለት በአደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ሰጥቷል።
አብይ አሕመድ አሊ ወደ ስልጣን ከመጣበት ቀን ጀምሮ፣ያልተቛረጠ የድጋፍና የሰልፍ ትዕይንቶች
ተካሂደዋል።ይህ አልበቃ ብሎ፣ የትግራይ ሕዝብ ባልበላ አንጀቱ፣ባልሰረቀው እጁ፣እሱ ተሰውቶ፣ቆስሎ ያመጣውን ለውጥ፣ በኦሮሞና በአማሮች ጥምረት፣ከቀንደኛው የትግራይ ሕዝብ ጠላት፣ ከሻዕብያው መሪ ከኢሳያስ አፈወርቒ ጋር በመተባበር፣ ከመንገድ፣እስከ ባጀት፣ከኮሮና ማስክ እስከ የአምበጣ መከላከያ መድሃኒት ተነፍጏል።
ትግራዋይ ትናንትና እና ከትናንትና ወድያ በነ “ደጃች ውቤ” ፣በነ ንጉስ ሚኒሊክ፣ በነ አፄ ሃይለስላሴና፣ በነ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም የደረሰበትን ግፍና ስቆቃ፣ዜሬ የእነሱን ጭካኔና አረሜኔነት በሚያስንቅ መልኩ፣ በጥቅምት 24/2013ዓም (Nov04/2020) የአሜሪካኖች ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዕለት ተጠንቶ፣አለም አይኗንና ጆሮዋን ወደ ምርጫው ስታደርግ፣የኢትዮዺያና የኤርትራ፣የሶማሌ የጦር ጥምር ፈጥረው፣ የአማራ ፋኖ፣ የአማራና የ፰ቱ ክልሎች ልዩ ሃይል በማሰለፍ፣ የትግራይ ሕዝብ ከገጸምድር ለማጥፋት ተንቀሳቀሱ።
ታሪክ እራሱን ይደግማል።የቅርብ አመታት የታሪክ መዛግብት እንደሚነግሩን፣ንጉስ ተክለሃይማኖት 60ሺ ሰራዊታቸው ይዘው ከአፄ ዮውሃንስ 12ሺ ወታደሮች ጋር ገጥመው የውሃ ሽታ እንደሆኑት፣ሚሊሊክ በተለያዩ ወቅት ሃፍረቱን እንደተከናነበው።ሃይለስላሴ የእንግሊዞች የጦር አውሮፕላኖች መጥተው እስኪያግዙት እንደተዋረደዉ። የደርግ ሰራዊት ከሽሬ በመሸሽ ትግራይን ለቆ
እንደፈረጠጠው ሁሉ፣ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመንም የአብይ፣የኢሳያስ፣የፎርማጆ፣የአማራ ተስፋፊዎች፣የ8ቱ ክልል ወታደሮች የተቀበሩት ተቀብረው፣የቆሰሉት ቆስለው፣ የተማረኩት ተማርከው፣ ከተምቤን ዓብይ ዓዲ የጀመሩትን ሩጫ፣መቐለን ትተው፣ ወልድያን አልፈው፣ ደሴን አስረክበው፣ ደብረብርሃን በራፍ ላይ እየተቀጠቀጡ እንደከብት እየተነዱ ሸሽቷል። ይህ ታሪክ በዘመኑ ቴክኖሎጂ ተደግፎ በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈ የዘመናችን የኢትዮዺያና፣የኢትዮዺያዊያን የከፋ ውርደት ነው።
እኔን የገረመኝ ግን በዚህች አገር ውስጥ ያልተደረገ ምን አለ ? ከአህያ ቄራ፣ እስከ የሰው ልጅ እንደፍዬል ዘቅዝቆ መግደል፣ ለዛው ብሺዎች የሚገኙበት በሻሸመኔ በአደባባይ ስው ተዘቅዝቆ ሲገደል አይተናል። ይህ እንደ ኢትዮዺያዊ ዜጋ ከባህላችንና ከእምነቶቻችን ያፈነገጠ፣ ከሰው ልጅ ባህርይ ውጭ የሆነ ድርጊት ሲፈጸም፣የ4ሺ ዘመን ስልጣኔ፣የሃይማኖታዊያን ነን የሚሉትን የወሬ ፕሮፓጋንዳ፣ ትክክለኛውን የኢትዮዺያዊያን ስነልቦና ቁልጭ አድርጎ ለመጀመርያ ግዜ ያየንበት ወቅት ነው።
አብይ አሕመድ አሊ የንግስና ምኞቱን ለማሳካት ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱና የመጀመርያው ደግሞ ሞትን እንድትለማመዱት አደረጋቹህ፣ከዛማ ግድያውን አጧጧፈው፣ሕዝቡንም ሾርት ሚሞሪ ብሎ አንቛሸሸው።ናቀው። በመቀጠል፣ ኢንጅነር ስመኘው በአብዮት አደባባይ በጠራራ ጽሃይ ገደለው።በመቀጠል ጀነራል ሳዓረ መኮነን፣ ጀነራል ገዛኢ አበራ፣ዶር አምባቸውና የስራ ባልደረቦቹ ቢሮአቸው ውስጥ ረሸናቸው። ሕዝቡ አንዲት ቃልም አልተነፈሰም። እስኪ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከሚደርሰው የቦምብና የድሮውን ድብደባ ባሻገር በማስረጃና በተንቀሳቃሽ ምስል በሚዲያ የተላለፉትን የተጋሩ ሰቆቃ ላስቀምጥ። ኢትዮዺያና፣ኢዮዺያዊነት እንደሚወራውና እንደሚተረከው የታሪክና ምሳሌ ድርሰት ሳይሆን፣ መሬት ላይ ኢትዮዺያዊያን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ባለሃብቶችና አዝማሪዎች ጋዜጠኞችና፣ቅልብ አክቲቪስቶች ሲገለጹ፣ ስነ ምግባራቸው ይህንን ይመስላል።
ይህ ከዚህ በታች የምዘረዝረው ማስረጃ በቪድዮ ተንቀሳቃሽ ምስል ተቀርጾ በሚዲያ ለአለም የተዘረጋ ማስረጃ ከመሆኑ ባሻገር፣ከዚህ በኃላ የትግራይን ሕዝብ ኢትዮዺያዊ ነው። ብሎ የሚከራከር ካለ የጤንነቱ ሁኔታ መፈተሽ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁኝ። በትግራይ ሕዝብ በኩል ደግሞ፣ የዚህ ክፉ ስነምግባር ተሳታፊዎች በህግ ፊት ቀርበው፣አስፈላጊውን ሕጋዊ ፍርድ እስኪያገኙ፣ ያለማቋረጥ መታገል አለብን በማለት ለማሳሰብ እወዳለሁኝ።
፨በኢሳት ሚዲያ አንድን አሳ ለመያዝ ባህሩን ማድረቅ። ተብሎ 5ሚሊዮን ለ90ሚሊዮን ተብሎ በመሳይ መኮነን ተሰብኳል።
፨እስክንድር ነጋ እነዚህን ሕዝቦች እንደ ኮክራች ማቃጠል፣ እንደ ጁዎች ማቃጠል ነው። ብሎ በመሰበኩ ዘብጥያ ወርዷል።
፨ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ የዛሬው የአብይ አማካሪ፣የትናንትና ምርኮኛ፣መቐለ ድረስ ተኪዶ ብእቅድና በፕላን ተጠንቶ መቀጥቀጥ አለባቸው።
፨አንዳርጋቸው ጽጌ ለነዚህ ሕዝቦች መጨከንና ማጥፋት አለብን። በማለት ለአብይ አሕመድ ፍኖተ ካርታ ስጥተነዋል በማለት ጥላቻው ገልፇል።
፨አገኘሁ ተሻገር የአማራ ርእ/መ፣ይህ ሕዝብ (የትግራይ)ማለቱ ነው የአማራ፣የኦሮሞ፣የሶማሊያው፣በአጠቃላይ የኢትዮዺያ ሕዝብ ጠላት ስለሆነ መጥፋትአለበት።
፨ወርቁ አይተነው፣ይህ ሰው የአማራ ሃይሎች ምዕራብ ትግራይን በወረራ ከያዙ በኃላ፣ዋነኛው የፋይናንስ አቅራቢ ከመሆን አልፎ፣ በየግምባሩ እየሄደ የአማራ ወራሪዎችን በመቀስቀስና፣በማበረታታት፣እስከ የጦርነት እቅድ እየነደፈ ገለፃ ሲያደርግ ተመልክተናል።ከዛም አለፍ ብሎ በመሄድ፣የትግራይ ሕዝብን ገድሎ ስጋችንን እንደ ፍዬል ስጋ ጠብሰው እንዲበሉ ያነሳሳ ጨካኝ አረመኔ ባለሃብትለራሱ የሰሊጥ ንግ ሲል በየቦታው የዜጎችን ግድያ የሚያቀነባብ ወንጀለኛ ነው። ።
፨ዳንኤል ክብረት ይህ ሰው ደግሞ፣ ዋናው የአብይ አሕመድ አሊ አማካሪ ሲሆን፣በሚኒስተርነት ማአረግም የባህል ሚኒስተርና፣የፓርላማ ተመራጭም ነው።እርግጥ ነው ባለው ሃላፊነትና ባለው ወደ ሚዲያ የመቅረብ እድል፣ የሃገሪቱን ገጽታ ለጥሩ ውጤት ሊጠቀምበት ይችል ነበር። ሆኖም ግን ባገኘው አጋጣሚ ለተጀመረው የተጋሩ የዘር ማጥፋት ዘመቻ፣ ቤንዚን ሲያርከፈክፍበት አይተናል።ሰምተናል።
ወያኔዎች ከገጸ ምድር ማጥፋት ብቻ ሳይሆን፣ነበሩ ተብለው እንዳይዘከሩ ከታሪክ መዛግብት ሁሉ መፋቅ አለባቸው። እነሱ የሰሩትንና እነሱ የሚያስታዉሱንን ማፍረስ አለብን። ለልጆቻችን የማስፈራሪያ ምሳሌዎች በማድረግ አንድን ሕፃን ጭራቅ መጣብህ ስንለው እንደሚፈራ ሁሉ፣ወያኔ የሚባለውን ስም ሲሰማ እንዲፈራ አድርገን ልጆቻችን ማሳደግ አለብን። እያለ በሚዲያ ሲሰብክ አጨብጫቢው ሕዝብ ደግሞ፣ ሞቅ ደመቅ አያደረገ ሲያጋግሉት የሚውል መንፈሰ እርኩስ ነው።
፨ምዕራብ ትግራይ በአማራ ተስፋፊዎች ከተወረረ በኃላ ምንም የማያውቁ ንጹሃን ተጋሩ፣ተጋሩ በመሆናቸው ብቻ የኃሊት የፊጥኝ ታስረውተ፣ ገድለው፣ወደ ተከዜ ወንዝ ተወርውረው፣ብሱዳን የተከዜ ዳርቻ ላይ ብዛት ያለው የተጋሩ አስከሬኖች ተገኝቷል።
፨በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተጋሩ ካለ ምንም ጥፋት ታስረው፣ከዛም ምንም ጥፋት እንደሌላቸው ከተረጋገጠ በኃላ ወዳ አገራቹህ ሂዱ ብሎ ፍርድ ቤት ነጻ ለቋቸው፣ወዳ ሃገራቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ፣በአማራ ታጣቂዎች ታግተው፣ ትግራዎት ስለሆኑ ብቻ ከተሳፈሩበት መኪና አውርደው፣የሰው ክቡር ሂወት ሆኖ አይኑ እያየ በእሳት ሲያቃጥሉት በቪድዮ አሳይተዉናል። ያ አልበቃ ብሎ የወርቁ አይተነው ምክር ሰምተው ሳይሆን አይቀርም፣ስጋውን በእንጀራ ወይስ ? በዳቦ እንብላው ? ሲሉ ሰምተናል።የሰው ልጅ ክቡር ሂወት ሲቃጠልና፣ሲማጸናቸው ሰምተናል።በምስል ተቀርፆ አይተናል።
፨በቻግኒ ከተማ አንድን የቤንሻንጉል ተወላጅ ከባጃጅ አውርደው ሕዝብ እያየ በአደባባይ በድንጋይ እየተመላለሱ ደብድበው ሲገድሉት በቪድዮ አይተናል።
፨በምዕራብ ትግራይ ሰላማዊያን የትግራይ ተወላጆች የወያኔ ሰላዮች ናቸው ተብለው፣ወጣቶቹ ይገደልልን እያሉ ሲጮሁ፣ፋኖዎቹም ወጣቱን ሲገድሉት በቪድዮ አይተናል።
፨ጸሊሞይ የኢትዮዺያ ወታደሮችና፣የአማራ ፋኖዎች ተከዜን ተሻግረው ወደ “ጸሊሞይ” በገቡበት ወቅት፣ሕዝቡ ቄዉን ለቆ ስለሄደ፣መሄድ ያልቻሉት አረጋዊያን በተኙበት ከረሸንዋቸው በኃላ, የአንድ አዛውንት አባት አንገት ቆርጠው ከጣራው ጫፍ ሰቅለዉት ሄደዋል።
፨ማህበረ ዴጔ የኢትዮዺያ ወታደሮች አክሱምን ከተቆጣጠሩ በኃላ፣ በአከባቢው ወደ አለው ገጠር በመሄድ ወጣቶቹን ሰብስበው እናንተ ጁንታዎች ናቹህ። በማለት ወጣቶቹን ረሽነው ወደ ገደል ሲወረውርዋቸው በተንቀሳቃሽ ቪድዮ አይተናል።
፨ የአብይ አሕመድ አሊ ስርአት የትግራይ ተወላጆች ከያሉበት በተለያየ መንገድ እያሰረ፣ከስራ ገበታቸው እያፈናቀለ፣ሃብታቸውን እየወረሰ ማሰቃየቱ አልበቃ ሲለው፣አገራችን ብለው ወጣትነታቸውን የገበሩላት፣ ሂወታቸውን ሊከፍሉላት በውትድርናው አለም ኢትዮዺያን ሲያገለግሉ የነበሩትን ቁጥራቸው ከ17000 በላይ የሰራዊቱ አባላት ለቃቅሞ በየካምፑ ካሰራቸው በኃላ፣ እስከ ዛሬዋ ቀን ቁጥራቸው 83 የሆነ መኮንኖችን ገድሏቸዋል።
፨የአብይ አሕመድ ስርአት፣ሌሎችን ባንዳዎች እያለ ሲከስ ቢውልም፣ሃቁ ግን ኢትዮዺያን ሊያፈርስ በውጭ ሃይሎች የተላከ። የአገር ክህደትን በግልጽና፣በሚስጢር የፈጸመ ባንዳ እሱ ነው።የኤርትራ ሰራዊት ጋብዞ ያኩሩ የኢትዮዺያ ምሶሶ የሆነውን የትግራይ ሕዝብን የጨፈጨፈ።
የሻዕብያ ሰራዊትን ጋብዞ ቅድስት ከተማችንን አክሱምን ያስደፈረ፣ከ800መቶ በላይ የአክሱም ከተማ ነዋሪዎችን ያስገደለ።
፨አባቱ ደርግ በሓውዜን የገበያ ቀን እንዳደረገው፣በቶጎጋ ሕዝብ ላይ ለገበያ በወጣ ሕዝብ ላይ በጀት የቦምብ ናዳ ያወረደ ጨካኝ አረመኔ።
፨የአማራ ፋኖዎች ምዕራብ ትግራይን ከወረሩ በኃላ፣ቁጥራቸው ከ1000ሺ በላይ የማይ ካድራ ሰላማዊያን ሕዝቦች በገጀራና በመጥረብያ ጨፍጭፈው ገድለው፣ጭራሽ ተበደልን ብለው የሰው ሃዘንና፣ለቅሶ ሳይቀር የሚቀሙ ቀማኞችን አይተናል።
ግን ለምን ?
ምንን ለማግኘት ? ለሚለው ጥያቄ እኛ የትግራይ ሕዝቦች ሳንሆን መመለስ ያለብን፣የአብይ አህመድ የኦሮሞ ብልጽግና፣ የነ ገዱ አንዳርጋቸውና፣የነ ደመቀ መኮንን ብልጽግና፣ የነ ብርሃኑ ነጋና፣የነ ታማኝ በየነ ፈንታ ይሆናል። እኛ የትግራይ ሕዝቦች፣ሊያጠፉን የመጡትን ወራሪዎች በተለይ በ፫ተኛው ዙር የወረራ ሙከራቸው የኢትዮዺያ መከላከያ ወታደሮች ከ270,000ሺ በላይ. የአማራ ተስፋፊዎችና ፋኖዎች ከ60,000 በላይ፣የሻዕብያው ወራሪ ሃይል ቅጥረኛ ወታደሮች ከ20,000 ሺ በላይ ግብአተ መሬታቸውን ያከናወን ስንሆን። በመጀመርያውና በሁለተኛው ወረራ ደግሞ ከ500 ሺ በላይ የትግራይ መሬት መቀበርያቸው ሆኗል።
“ትግራይ የወራሪዎች መቀበርያ ናት” ስራ ለሰሪው፤እሾህ ላጣሪው ሲባል ከጥንት ጊዜ ጀምሮ፣ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የአያት ቅድመ አያቶቻችን የክብራችን፣የማንነታችን መገለጫችን ለክብራችንና፣ ለመሬታችን፣ ለሃገራችን ለዚህች ቅድስት መሬት “ሃገረ ትግራይ”ተጋሩ የትም ቦታ፣የትም ዓለም እንኑር የሂወት፣የዲፕሎማሲ፣የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅርቦታችን እስከ እለተ ሞታችን ይቀጥላል።
“ትግራይ” አለም ሊያጠፋት በ360 ዲግሪ ከበዋት፣በአየር፣በምድር፣ከአለም ነጥለው ካለ ወሬ ነጋሪ ሊያጠፉን ሞክረው ነበር። ያ ህልማቸው፣ ምኞታቸው፣ በጀግናው “የትግራይ መከላከያ ሃይልና” በጀግናው የትግራይ ሕዝብ ተመክቶል። ፍላጎታቸውና ምኞታቸው በኖ፣ተኖ ቀርቷል። ትናንትና
ከአሸባሪ ጋር አንነጋገርም። ጁንታው ወያኔ እንደ ዱቄት ስለበታተነው ከእንግዲህ ደብረፄን የታለ ? ጌታቸው ረዳ የታለ ? እያልን እየፈላለግን ነው እንዳላሉ ? ዱቄቱ “ድፎ ዳቦ” ሆኖ ገዝፎና ጎልብቶ፣ በመምጣት ጉሮሮዋቸው ይዞ፣ ደቡብ አፍሪቃና ኬንያ ድረስ ወስዶ አስፈርሟቸዋል። “ክልተ ግዜ ክነዛርቦ ኢና” ማለት ይሄ ነው።
የትግራይ ሕዝብ ለህልውናው ተዋግቶ፣ የመኖር መብቱን አስጠብቛል። ኢትዮዺያ የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ያላትን ሃብት አሟጣ ከተጠቀመች በኃላ፣ ትግራይን ሳሆን እራሷን አጥፍታለች። በአለም አደባባይ የኢትዮዺያና፣ የኢትዮዺያዊነት ምሶሶው” የትግራይ ሕዝብ” መሆኑ አለም በአይኗ ብሌን አይቷለች።
ትግራይ ለጠላቶቿ መቀበርያ ነች።
ዘልአለማዊ ክብር በዚህ የጀኖሳይድ ጦርነት ሂወታቸው ላጡት ሰማእታት። ክብር ለነዛ ሳይበድሉ፣ካለ ጥፋታቸው ለተደፈሩት ከ120 ሺ በላይ የትግራይ ሴት እህቶቻችንና፣እናቶቻችን።
ትግራይ ትስዕር አመሰግናለሁኝ 11/27/2022 ሙሉጌታ በሪሁን [email protected]
Mulugeat, sorry I did not installed the Amharic font! I read your note and I found it the usual tplf diaspora bravado we were this we are that. please take responsibility when you miserably fail due to your own miscalculation and over estimating your selves.. Yes, it is easy for you in the diaspora to create all the blunder and see the fighting from a distance while the poor people of Tigray pay the heavy price. what more distraction and death do you people want just to prove your wrapped ego ? when are you people take responsibility for the mess you created? you always look for an excuse and blame this blame that. you blame the world but not your self who is the architect of all the conflict in Ethiopia. when your army capture a town, you claim your selves tplf is the best army in the world when you loose you blame the us, eu, turkey etc. By doing so you are prolonging the suffering of the people of tigray and Ethiopia in large. what is the essence of your article? are you telling us there is another round of war ? or you lost the war because the world did not supported you?