የትግራይ ህዝብ አንድማንኛውም ህዝብ ለኢትዮጵያ ሃገረመንግስትና ግንባታ ከፍተኛውን ድርሻ አበርክቷል። ሆኖም ይህ ማህበረሰባዊ ተሳትፎ የነበረውን የዘመናት ትግል ለራሱ ማህበረስብ ዘለቄታ ያለው ሰላምን አላስገኝለትም። በዚህም ምክንያት የራሱን ሶሻል ካፒታል ተጠቅሞ ማህበረሰቡን ሊጠቅሙ የሚችሉ የኢኮኖሚ፡ የባህል፡ የስነጥበብ ቋንቋና የሥርዓተ ትምህርት እድገት ለማምጣት አላስቻሉትም። ይህም አልበቃ ብሎ ሌሎች አሱ በታሪክ ሰሪነቱ የሚግባውን ክብርና ቦታ ከመስጠት ይልቅ በራሳቸው ወይንም ከሌላ የውጭ ባዕድ ሃይል ጋር በመመሳጠር የትግራይን ህዝብ በማንኳሰስ አራሳቸውን የታሪክ ፈጣሪ አድርገው ከመቁጠራቸውም በተጨማሪ ለትግራይና ለሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ዜግነት ሰጪና ከልካይ ሆነው የተገኙበት ግዜ ላይ ደርሰናል። ከዚህም አልፎ በአቢይ አህመድና በኤርትራው ጨካኝና አረመኔ መሪ ፊትአውራሪነት እንዲሁም በአንዳንድ የኢትዮጵያ ብሄር ጽንፈኞች ጋሻ ጃግሬነት አልፎም በአንዳንድ የአረብ ሃገራት እገዛና አይዞህ ባይነት በትገራይ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን መሬቷ አቅፋ በያዘቻቸው የተፈጥሮ ሃብቷ አና በታሪኳ ላይ ሁሉ አቀፍ የሆነ የጥፋት ጦርነት አውጀው በመዝመት ታረክ ይቅር የማይለው ወንጀል በትግራይ ህዝብ ላይ በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

ይህን ግፍ የተመለከተ የትግራይ ህዝብ ወጣት፡ ሽማግሌ፡ ሴት ወንድ የተማረ ያልተማረ ጤነኛ በሽተኛ ሳይል ተጠቂነቱ ባስከተለበት ቁጭት ተነሳስቶ ዱር ቤቴ ብሎ በከተማ የነበረው ጨርቄን ማቄን ሳይል ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎና ትቶ ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ብሎ አጁ ጠብመንጃ ወደመያዝ ተሸጋገረ። በዚህም በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተደራጅቶና ሰልጥኖ ዘመናዊ አስተሳሰብ ሳይላበስ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ አስከአፍንጫው የታጠቀውን የአቢይ እና የኢሳያስ መንጋ ሰራዊት የትግራይ ሰራዊት በጥቂት ግዜ በአካሄደው ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከአብዛኛው የትግራይ መሬት ጠራርጎ ጥጋቸውን አስያዛቸው።

የዚህ ጽሁፍ አላማ የትግራይን ህዝብ ድል ወይንም በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውንና እየደረስ ያለውን ግፍ ለማውሳት አይደልም። ይህን ላድርግ ብልም የተሰራው ግፍ አሁን ህዝቡ እያየ ካለው መከራ እጅግ የገዘፈ በመሆኑ ዜና ቦታ የሚበቃኝ መስሎ አይታየኝም። ስለሆነም ከላይ በጠቀስኩት ርዕስ ላይ በማተኮር ዘለግ ያለ አስተያየት ወደመስጠቱ ልሽጋግር።
የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ጥያቄው ምንድነው?