————————————–!

እንደሚታወቀው ሁሉ በትግራይ ተፈጥሮ የነበረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጋር ዘላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት በፕሪቶርያ ደቡብ ኣፍሪካ ሕዳር 02/2022 መፈራረማቸው ይታወቃል። በተደረሰው ስምምነት መሰረትም፣ ኣፈሙዝ በመዘቅዘቅ ውግያ እንዲቆም ተደርጓል፣፣ ትጥቅ የመፍታት ስራ ተከናውኗል፣ ህወሓት የኣሸባሪነት ፍረጃ ተነስቶለታል፣ በከፊልም ቢሆን እንደ ባንክና መብራት የመሳሰሉ ግልጋሎት ሰጪ ተቋማት ስራ ጀምረዋል፣ ከፊል ህዝባችንም ሰላም ኣግኝቶ ዕለታዊ ስራውን ማከናወን ጀምሯል። የተጀመረዉ የሰላም ስምምነት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ መተግበሩ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የትግራይ ማህበር በሰሜን ኣሜሪካ በፅኑ ያምናል። ይህን አቋሙንም በተደጋጋሚ ባወጣቸው ኣቋም መግለጫዎች አስተጋብቷል።

ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠረው የተፈናቀለው የትግራይ ህዝብ ወደ ቀየው አልተመለሰም፣ በስምምነቱ እና በህገ መንግስቱ መሰረት የትግራይ ህዝብ ሉኣላዊ ግዛት እስከ ኣሁን ድረስ አልተመለሰም። የትግራይ ደቡባዊ ፣ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች በአማራ ታጣቂዎችና የሻዕብያ ወራሪ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ብቻ ሳይሆን በስፍራዉ የሚገኝ የትግራይ ህዝብ በየቀኑ እየተንጋላታ እና እየተገደለ ይገኛል። በመሆኑም የከፊሉ የትግራይ ህዝብ ስቃይና መከራ እንዲቀጥል እድርጎታል። ስለሆነም ከተፈረመ ሰባት ወራት ያስቆጠረው ስምምነት አለመተግበሩ በምንም መለኪያ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። የትግራይ ማህበር በሰሜን ኣሜሪካ የሰላም ስምምነቱ ባስቸኳይ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አሁንም አጥብቆ ይጠይቃል። በዚህ ረገድ የአፍሪቃ ሕብረት፣ የአሜሪካ መንግስት እና ሌሎች ባለድርሻ ወገኖች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።

ይህ ሳያንስ አሁንም ቢሆን የኢፈድሪ ምርጫ ቦርድ በትግራይ የፖለቲካ ድርጅቶች እውቅና ከመስጠት ጋር በተያያዘ የሰጠው አሉታዊ ምላሽ፣ በመሰረቱ በትግራይ ህዝብና በፓርቲዎች፣ በፓርቲዎች እና በፓርቲዎች፣ እንዲሁም በፓርቲዎች እና በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር መካከል ሽኩቻ እንዲነግስና እና መተማመን እንዳይኖር የሚያደረግ፣ ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት እንቅፋትና ደንቃራ ሆኖ ኣግኝተነዋል። ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈረመን ፓርቲ እውቅና መንፈግ፣ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ብሎም ስምምነቱ እንዲፈርስ መንገድ የሚጠርግ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመዉ እና እየተፈፀመ ያለዉ ጆኖሳይድ ተጠያቂነት እንዲያጣና እንዲዳፈን የሚያደርግ በየጊዜው የሚፈጠር አጀንዳ አካል ከመሆን ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የኢፈድሪ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ፖለቲካዊ ፖርቲዎች ላይ የወሰነዉ ዉሳኔ ያለ ፌደራል መንግስት እውቅና የተፈፀመ ነው ብለን ኣናምንም። ስለሆነም የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ከፕሪቶርያ ውሳኔ ጋር የሚጣረስ በመሆኑና ፀረ ህዝብም ከመሆኑ ኣንፃር፣ የትግራይ ማህበር በሰሜን ኣመሪካ (UTNA) ውሳኔውን በፅኑ ያወግዛል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዉሳኔውን ዳግም በማየት፣ በትግራይ ዉስጥ የሚገኙ ፖለቲካዊ ፖርቲዎች ህጋዊ እዉቅና እንዲያገኙ እና የትግራይ ህዝብ በፍላጎቱ በመረጠዉ ፓርቲ እና መንግስት እንዲተዳደር እድል ይሰጠዉ ዘንድ እንጠይቃለን።

ፍትህ ለትግራይ ህዝብ !!!

05/15/2023

May be an image of text

All reactions:

280Desnet G-medhin and 279 others

By aiga