በዐቢይ አህመድ ዓሊ ፊተውራሪነት የሚመራ የኦሮሞ የባሪያ መንግሥት ስልጣኑን ጠብቆ ለማስጠበቅ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የገጠመው የፖለቲካ ቀውስ ለማብረድና ለማስቀስ የት ድረስ መሄድ እንደሚችልና በውጭ ኃይሎች አይዞህ ባይነት እንደ ውሻ ጃስ! ሲባል ሰውዬው ውለታም ሆነ ይሉኝታ የሌለውና የማያውቅ፣ ፈፅሞ የማይታመን ክፉ የማይገልፀው ወስላታ ባለ እንጀራና አውሬ ለመሆኑ የሌላ ሰው ምስክርነት ሳይሻት ኤርትራ ለራስዋ አይተዋለች። እውነት ነው፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደ ህወሓት መሪዎች ሙሉ ለሙሉ ከስህተቱ የማይማር ሰው ነው ለማለት አይቻልም፥ በሆነ ምክንያት አንድ ጊዜ ጥርስ የነከሰብህ፣ በክፉ ዓይን ያየህና የተመለከተህ እንደ ሆነ ግን የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ልክ እንደ ህወሓት መሪዎች ቂመኛና ቂሙ ሳይወጣም ተኝቶ የማያድር ሰው ነው።

እዚህ ላይ፥ በኢሳይያስ አፈወርቂ እና በህወሓት መሪዎች መካከል መቃቃር የማይገልፀው የለየለት ጥላቻ እንዳለና ኤርትራም ዕድሉን ስታገኝ ከሶማሊያ፣ ከኢትዮጵያ ሰራዊት፣ ከአማራ ኢንተርሃምዌ ሚሊሻና ታጣቂ ጋር ግንባር በመፍጠር በትግራይ ህዝብ ላይ በሰብአዊነት የሚፈፀም የጦርና የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀምዋን ይታወቃል። በርግጥ፥ የኤርትራ ምክንያት በሁለቱም በኩል ከሚገኙ መሪዎቹ የለየለት ጥላቻና ቂም ያለፈ ኤርትራ እንደ አገር ለመገንባት ሲታሰብ የትግራይ ህዝብ ጠንካራ ትግራዋይ ማንነት እንደማይዋጥላት የአስመራ መንግስት ተደጋጋሚ መንግስታዊ መግለጫዎችና በስርዓቱ ደጋፊዎች ዕለት ዕለት የሚዘራ ትግራይ-ፎቢያ ፕሮፓጋንዳ መመልከት በቂ ነው። ኤርትራ ዘንድሮ ከኢትዮጵያ ዘንድ የተጋረጣት አደጋ ታድያ ይህ ከወያነ ጋር አለኝ የምትለው ጥላቻና ቂም ሲበዛ እጅግ ቀላልና እንዳለፈ ወንዝም የሚያስረሳ ነው። አንድም፥ የኤርትራ መንግስት እና ህዝብ እንደ ህዝብ ለመቀጠል ሲጀመር አገር ሲኖሮው ነውና።

የኦሮሞ ወለጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔርሰቦችና ህዝቦች ሁሉንም በደም አጨቅይቶና አዳርሶ ሁለተኛ ዙር አማራ ውስጥ የገባው ዐቢይ አህመድ ዓሊ የትግራይ ጦርነት ያስከተለበት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መቃወስ ሊገታውና ሊያስቆመው ባለመቻሉ፤ አንድም፥ ከገባበት መቀመቅ ለመውጣት አስልቶ ኤርትራን የጦስ ዶሮ ለማድረግና በዋናነትም ኢሳይያስ አፈወርቂም እንደ ጋዳፊና እንደ ሙባረክ እንደ አልበሽርና እንደ ቢን አሊ መሄድ አለበት! ብለው የሚያምኑ የውጭ ኃይሎች መልዕክተኛ በመሆን “ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ዳር ድንበር ነው… የባህር በር ለኢትዮጵያ የመኖርና አለመኖር ነው … እኔ ካልቻልኩም ልጆቻችን ያደረጉታል” ብሎ ይፋዊ መግለጫ መስጠቱ የኤርትራ እንደ አገር የመቀጠልዋ ነገር ስጋት ውስጥ ከቶታል። ቀደም ሲል ለማንሳት እንደ ተሞከረም ይህ ዓይነቱ የኢትዮጵያ ገዢዎች ተደጋጋሚ ጨፍላቂ አጀንዳና ደመኛ ዛቻ ለኢሳይያስ አፈወርቂ ሆነ ለኤርትራዊያን የሞት ውሳኔ ለመሆኑ ለመረዳት የሚቸገር ባለ አእምሮ አይኖርም። ቀለል ባለ አማርኛ፥ ኢሳይያስ አፈወርቂ ከህወሓት መሪዎች ጋር ያለው ዘመናት ያስቆጠረ ቂም በቀል አሁን በዚህ ሰዓት ኤርትራ ከኢትዮጵያ የገጠማት እንደ አገር የመኖርና ያለ መኖር የህልውና ስጋት ጋር ሲነፃፀር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።    

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ‘የባህር በር ያስፈልገናል” በሚል ሰበብ የውጭ ኃይሎች አጀንዳ ተሸካሚና አስፈፃሚ በመሆን “ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ዳር ድንበር ነው… የባህር በር ለኢትዮጵያ የመኖርና አለመኖር ነው … እኔ ካልቻልኩም ልጆቻችን ያደረጉታል” ብሎ ይፋዊ መግለጫ ከሰጠ በኃላም ቢሆን ዐቢይ አህመድ ዓሊና ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍትፍት ይጎራረሳሉ! ብሎ መጠበቅ ሆነ ማሰብ እጅግ የሚከብድ ነው። በሆነ ተአምር እነዚህ ሁለት ሰዎች ዳግም ለመጨባበጥ እንኳ ቢበቁ፤ የኤርትራ ሰዎች፥ ኢትዮጵያ ቀዳሚና ተከታይ የሌላት ፀረ ህልውናችን አገር ናት! የሚል ቀዋሚ ፋይል ከፍተው ነው። ኢትዮጵያም በተመሳሳይ፥ አሰብ በስምምነት ቢሰጣትም ምፅዋንም ጨምሩልኝ ማለትዋ ስለማይቀር መቼም ቢሆን ዕድልና አጋጣሚ ያገኘች ቅፅበት፥ ኤርትራ እንዲሁ እጅህን ሰደህ መጉረስ ብቻ የሚሻት ሰው አልባ አገር ናት! ብላ ቀን ጠብቃ አገሪቱን ለመዋጥ ነው አድብታ የምትጠብቀው።      

እንግዲያውስ፥ በዐቢይ አህመድ ዓሊ መገለጫ ጨርቃቸው የጣሉ የኤርትራ ሰዎች ነገሩ እንግዳ ቢሆንባቸውም ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና በዙሪያቸው የሚገኙ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ጉዳዩ ድቡዳ ነው ተብሎ አይታሰብም። በመሆኑም፥ ትግራይና ኤርትራ የሚነጋገሩበት ዕድል ቢፈጠር፥ ኤርትራ የትግራይ ሰራዊት ራሱን ለማስታጠቅ ምፅዋና አሰብ የማትፈቅድበት ምክንያት አይኖርም። አንድም፥ ኤርትራ በቀጠናው ደረጃ ከግብፅ ልታገኘው የምትችል ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ላቅ ያለ ስንቅ እንዳለ ሆኖ በአንፃሩ ከሱዳን፣ ከሶማሊያና ከኬንያ በድምር ልታገኘው የምትችል ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ እርዳታ ከትግራይ ጋር ሲነፃፀር ከትግራይ ጋር ዕርቀ ሰላም በማውረድ የምትፈጥረው ወንድማማችነት የሚያስገኝላት ወጤት የላቀ ነው የሚሆነው። ሕሱም ጓሳ ቁርሱ ዝነበረ ድራሩ ይኾኖ!

By aiga

2 thoughts on “ትግራይና ኤርትራ የሚነጋገሩበት ዕድል ቢፈጠር ኤርትራ የትግራይ ሰራዊት ራሱን ለማስታጠቅ ምፅዋና አሰብ የማትፈቅድበት ምክንያት አይኖርም”
  1. So, you only want Eritrea mend good relation with Tigry and still continue name calling Amhara. Since Amhara’s relationship with Eritrea is very good why don’t you try to bring peace with Eritrea, Amhara and Afar which represent the Northern people of Ethiopia. If you do that you can counter what Abiy is trying to do by allying with Somali and Afar people in addition to the Southern people.
    It shame Tigray intellectuals and TPLF consider the people of Amhara as their sworn enemy. Historically there had been competition between the two people. But, there was more cooperation than competition until TPLF came to power.

Comments are closed.