ሁለት  ድፍን አመት በቦምብ ስትቀጠቅጡ

ትግራይ መሬቷን ወራችሁ ለቀማኞች ስትሰጡ

ህዝቡን አፈነቅላችሁ

ከመንደሩ ስታስወጡ

ምርኮኞቻችሁ በዝተው

መሣሪያችሁን ስታጡ

እነደራደር ብላችሁ ሄዳችሁ ፕሪቶርያ

አላችሁ ቲዲኤፍ ትጥቁን ይፍታ

ትግራይ ነች ኢትዯጵያ

እንዴት ሆኖ ምን አግኝተን?

የነበረንን ህዘብና

እሸት ትውልዳችንን አጥተን?

ተረሳ እንዴ

ልጃገረዶች እናቶች መነኩሴዎች በግፍ በስቃይ ተደፍረው

ህሊናቸው ተናውጦ ያላሰቡትን ልጅ አርግዘው

ይህን መቀበል ያልቻሉ ራሳቸውን አጥፍተው

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተጋሩ

ክቡር ህይወታቸውን አጥተው

የተረፉትም  በሰማይና በመሬት ተቀጥቅጠው

ለህክምና መድሃኒት የሚበላ እህል ተነፍገው

ልጆቻቸው በየቦታው እሳት ነዶ ተጠብሰው

በየገደሉ በየወንዙ እንደ ድንጋይ ተወርውረው?

ታዲያ በምን ሂሳብ ነው

የትግራይ ትጥቅ የሚወርደው

ከዚህ ከሃዲ ሰምምነት ምንድነው ያተረፍነው

ኣብይ የጣለውን ህገመንግስት ነፍስ  ልንዘራለት ነው?

በ360 ዲግሪ ተጋሩዎች ተከበው

የህዝብ ጥያቄ ሳይመለስ የምን ትጥቅ መፍታት ነው

ለማን ተብሎ

ለአብይና ለኢሳያስ ማለቂያ ለሌለው ሴራ?

እነሱ ጮቤ እንዲረግጡ

ኦባሳንጆ እንዲኮራ

በዘር ማፅዳት የሚታማው በናይጀርያ ቢያፍራ

አፍሪካ አንድነት ዝና እንዳያተርፍ

በትግራይ ህዝብ ኪሳራ?

ትግራይ ከዚህ በኋላ የምታወርደው የምትፈታው

ኢትዮጵያ የምትባል አገርና ኢትዮጵያዊ የሚሉት ልቦና ነው

ይታያችሁ

ኢሳያስ ዓዲግራት ሲሰፍር

ፋኖ ራያና ወልቃይትን እጁ አስገብቶ ሲቆጣጠር

ትግራዋይ ዘበኛ ተደርጐ

ቆሞ ሊጠብቅ ድምበር

አይታሰብም

በምንም ተአምር ከቲዲኤፍ

የሚፈታ ትጥቅ የለም

የትግራይን እድል መወሰን ነው የህዝቧን ጥቅም ማስቀደም

ቃል እንግባ ለራሳችን ከእንግዲህ ኢትዮጵያን ላንሸከም

ኤሪቶጵያን ይስሙት እቅጩ እውነታ ይኸው ነው

ትጥቅ ማውረድ የሚባል እማይታሰብ እማይሆን ነው

ትግራይ እንደ አገር ሳትሰራ

በሁለት እግሯ ሳትቆም

አንድ የሚወርድ ብረት የሚፈታ ትጥቅ የለም!!

ትግራይ ትስዕር!!

የሩሳሌም    Nov 3/ 2022

By aiga

One thought on “የሚፈታ ትጥቅ የለም”
  1. I have bad news for you, the soldiers already started handing their weapons to the military in many front way before the official disarmament started.

Comments are closed.