ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

መንደርደሪያ፥ ሰው በባህሪይው ያየው የመሆን ፍላጎት ያለው ተፈጥሮ ነው። ልጆች ሳለን፥ በእጃችን የያዝነው እየጣልን ያየነው ሁሉ ገንዘባችን/የእኛ የማደረግ ፍላጎትና ባህሪይ ነበር። በተጨማሪም፥ ሃኪም ስናይ ሃኪም፣ ቄስ ስናይ ቄስ፣ ፓይለት ስናይ ፓይለት፣ ሮዋጮች በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳል ሲሸለሙ ስናይ – ሩጫ፣ የአፍሪካና የዓለም ዋንጫ ሲመጣ ደግሞ እንዲሁ እግር ኳስ መጫወት ያምረን ነበር። ይህ ሁሉ ምኞትና ፍላጎት ግን የሚዘልቅ ነገር ሳይሆን ከአንዲት ሳምንት ሞቅታ በላይ አያልፍም ነበር። የሩጫም የኳሱም ወቅት ሲያልፍ በዚያ ልክ ሯጭና የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ፍላጎታችን አብሮ ይክስምና ወደ ቀድሞ ኑሮአችን እንመለሳለን። ለምን? ጳውሎስ “ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ (1ኛቆሮ. 13፥11) ሲል እንደሚገልጸው የሰው ህይወት/ኑሮ የእውቀቱና የመረዳቱ ልክ ነውና። ሰው ከመረዳቱ በላይ የሆነ ኑሮ ሊኖር አይችልም። የሰው ኑሮ የመረዳቱ ልክ/ውጤት ነው። በልጅነታችን ዘመን የምናስበውና የምንሰራው ስራ ሁሉ ልጆች ስለ ነበርን ነው። ከዚያ በላይ የምናውቀው ነገር የለም አልነበረምም። የልጅነት ዘመን ታልፎ ሃያና ሳላሳ ዓመት አልፈን የምንኖረው ህይወት በአንጻሩ ቀድሞ ከነበርንበት ህይወት ፈጽሞ የተለየ ነው። በዚህ ጊዜ ክስማችን በቀር የማይለወጥ ነገር አይኖርም። አካላዊ ለውጥ ብቻ ሳይሆን አስተሳሰባችን ጨምር ስለሚለወጥ ብዙ ነገራችን አብሮ ይለወጣል። ይህ ማለት፥ ልጆች ሳለን የምናስበውና የምንሰራው የነበረ ነገር ሁሉ እንተዋለን ማለት ነው። ይህ ግን ሁሉ ጊዜ ትክክል ነው ማለት አይደለም። ሰው (የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ሰው) በአርባዎቹ መጨረሻ ሆኖም በአስተሳሰቡ የአራት ዓመት ህጻን ልጅ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ፥ በአስተሳሰቡ ከአራት ዓመት ህጻን ልጅ የማይሻል፤ በብልጭልጭ የሚያምን፤ የህግ፣ የፋይናንስ፣ የህክምና፣ የፖለቲካ፣ የሳይንስ፣ የውትድርና፣ የግብርና ባለሞያዎች ባያ ቁጥር ላስተምራችሁ እያለ ባላለፈበት ትምህርትና ሞያ እውቀትን በማጨለም የሚታወቀው አፈ-ህፃን ዐቢይ አህመድ ዓሊ አሁን ደግሞ ራሽያ በዩክሬን ላይ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ላይ ይህን አለች ይህን አደረገች የሚል ዜና እያየና እየሰማ እኔስ ከማን አንሼ?! በሚል ጨቅላ አስተሳሰብ በቴሌቪዥን መስኮት ያየውና የሰማው ሁሉ ለመሆንና ለማድረግ ቀድሞ የገባው የሰላም ስምምነት አፍርሶ በአገሪቱ ላይ የደቀነው አደጋ የሚያትትና የሚያስረዳ ጽሑፍ ነው። ወደ ፍሬ ነገራችን ከመዝለቃችን በፊት ግን በውኑ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ማን፥ በጀን ወይስ ፈጀን? ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ ርዕስ ማዕከል ያደርገ ከውቅያኖስ በጭልፋ የመቅዳት ያህል ሁለትና ሦስት ነጥቦች ለማንሳት እወዳለሁ።  

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይዞት የመጣ መንግስትነት የዝርፍያና የግድያ መንፈስ ነው

ዐቢይ አህመድ ዓሊ ማን ነው? ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ ግለሰቡን ለመግለጽ በርካታ ተጨባጭ ነገሮች ማንሳት ይቻላል። ግለሰቡ ከሚታወቅባቸው ባህሪያት መካከል በጥቂቱ አንስተን የተመለከትን እንደሆነ ታድያ፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ራዕይ አልባ (Image driven) ዓይነት ሰው ከመሆኑ በላይ ያልሆነውን ሆኖ ለመታየት በሚያደርጋቸው ጥረቶች የተነሳ በራሱ ላይ በመተክሶስ ራሱን በማቆሳሰል የሚታወቅ፤ ሰውዬው ከእውቀት የጸዳ፣ መጽሐፍ ማንበብ ያላለፈበትና ያልፈጠረበት፣ እውቀት የሚያስታውከው ዓይነት ሰው ሆኖ ሳለም አዋቂና የተማረ ሰው ለመምሰል በሚያደርገው ጥረት በደጋፊዎቹ ሰፈር ሳይቀር ከነ ስሙ “አያልቅበት” ተብሎ ለመጠራት የበቃ የለየለት የውሸት ፋብሪካ (compulsive lair) ነው። በደጋፊዎቹ ዘንድ ሳይቀር እንዲህ ዓይነት ዋሾ ሰው አይተንም ሰምተንም አናውቅም – አሁንስ አበዛኸው! ያስባላቸው ትንግርተኛ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ውሸት ለማስታወስ ያህል። አማራን ለማታላል መቀደድ ብቻ ነው ብሎ የሚያምን ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከዚህ ቀደም በፓርላማው ፊት ቀርቦ የተናገረው ሁላችን እናስታውሳለን። ይኸውም፥ ኤዥያና ኣውሮፓ እንኳን ያልተቻላቸው እኔ ግን ዝናብን ማዝነብ የሚችል ቴክኖሎጂ በመፍጠር ይሄው የአማራ ሰማይ በደመና እሞለዋለሁ፣ ምድሪቱም በቅርቡ ጎርፍ በጎርፍ አደርጋታለሁ፣ ይህን ማድረግ የታቸለው ብቸኛ ኣፍሪካዊ መንግስት እኔ ነኝ! ሲል ተደብቆ አልነበረም።

ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ አንዲት ቀን ክላስ ውስጥ ሳይገኝ በተጭበረበረ የትምህርት ማስረጃ ሳይገባው ያለ ስሙ ለመጠራት የበቃ፣ እዚህም እዛም ባልገባውና በማያገባው ዘርፍ ሁሉ ደረቱን ገልብጦ ሲያወራ ከተራ ወታደር ቤት ለሚኒስትርነት ማዕረግ የበቃ አገር ሸያጭ የአገር እርግማን ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ከህወሓት በላይ ኢህአዴግ ሆኖ የራሱን ወገን ኦነግ ነህ ኦብነግ ነህ እያለ የኦሮሞ ወጣት ሲያሳድድ፣ ሲያስር፣ ሲገርፍና ሲገድል የነበረ፣ በግልና በቡድን ተደራጅቶ የኦሮሞያ መሬት ሲቸበችብ ዘመኑን የፈጀ ግለሰብ ነው። ከዚህ ሁሉ በኋላም የመጣው ለውጥ ለግሉ ክብርና መጠቀሚያ እንዲሁም የስም ግንባታ ለማዋል ሲጣደፍ ይሄው አገርና ህዝብ መቀመቅ ውስጥ የከተተ የኢትዮጵያ ቅራሬ ፖለቲካ የፈጠረው ተረፈ ምርት ነው።

ይህ “የአገር መሪ ነኝ” ብሎ የሚያምን፣ ሳይገባው አለ ቦታው የተቀመጠ ውስላታ ግለስብ ወደ ስልጣነ መንበሩ መምጣት ተከትሎ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ለክብሩ ሲባል የጠፋው ነፍስ ቁጥር ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። መጽሐፍ “ጻድቃን በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋል፤ ኀጥኣን (ወንጀለኞች) በሠለጠኑ ጊዜ ግን ሕዝብ ያለቅሳል” እንዲል (ምሳሌ 29፥2) የዋይታ፣ የሐዘን፣ የእልቂትና የጥፋት በር የሆነ የሲኦል ደጅ ተከፍቶ ዜጎች በዚህ ደረጃ እርስበርስ ሲገዳደሉ፣ በአገሪቱ ላይ የነገሰው ስርዓት አልበኝነትና ጋጠ ወጥነት የተነሳ በዜጎች ማካከል የሚሆነውና የሚፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊትና ወንጀል እውን ሆኖ ያየነው በዚህ ሰው ዘመነ መንግስት ነው። በትግራይ አንስቶች፣ ወጣቶችና ሽማግዎች ላይ የተፈፀመ ከአእምሮ በላይ የሆነ ግፍና በደል ሁሉ ለፈጣሪ ትተን በኢትዮጵያውያን መካከል ዛሬም ድረስ የቀጠለው መገዳደልና መተራደድ፤ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል የተፈጠረች ነፍስ እንደ እባብ በዱላና በድንጋይ ተወግራና ተቀጥቅጣ ስታልፍ ለጥቆም ነፍስ የተለያት ስጋ መሬት ለመሬት ሲጎተትና ቆዳው ለመገፈፍ እንደ ተዘጋጀ በግ ቁልቁል ተደፍቶ የተሰቀለበት ክስተት ያየነው በዚህ ለፌ ወለፌ የሆነ ግለሰብ ዘመነ መንግስት ነው።  ስልጣኑን ለማደላደልና ዙፋኑ ለማስጠበቅ ህፃን ልጅ የማያሳምን ምክንያት እያስተጋባ በጠራራ ፀሐይ የአገር መሪዎችና ባለስልጣናት በጥይት ደብድቦ የሚገድል የሰው ፍጥረት የሌለው አውሬ ነው። ዐቢይ አህመድ ዓሊ፥ ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም አገር ሸያጭ ማንነቱ እንደ ቀጠለ በመሆኑ ከዙፋኑ የተፈነገለ ዕለት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ትቶላቸው የሚሄደው ዕዳና ብድር በጥቂቱ አገሪቱ ሩብ ክፍለ ዘመን ወደኋላ የሚያስቀር ነው።

እንግዲያውስ፥ ይህ ሰው (ዐቢይ አህመድ ዓሊ) ይዞት የመጣ መንግስትነት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በታሪክዋ አይታው የማታውቅ የዝርፍያና የግዲያ መንፈስ ለመሆኑ የሚጠራጠር ሰው አይኑር። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ማብራሪያ እሰጥበት ዘንድ የሚጠይቅ ሰው ይኖራል የሚል ግምት የለኝም። በአማርኛ ለመግለጽ ይህል ግን፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይዞት የመጣ ባለተራ ነኝ ብሎ የሚያምን የአዳማ ፖለቲከኛ ከጅምሩ ዓላማው ለማሳካት የነቀለው በፖለቲካ መድረክ የተሻለ ሃሳብ ይዞ በመቅረብ ተወዳድሮ አሸናፊ በመሆን ሳይሆን ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ ከፊቱ የቆመ ሁሉ በመግደለና በመዝረፍ ነው። የማይመስለን ሁሉ በሜንጫ ነው አንገቱ የምንለው! ብሎ ሲነግረህ ጽንፈኛው ቀልዱን አልነበረም፤ እውነቱን ነው የነገረህ። ጽንፈኛ ሲናገር ደግሞ ልታምነው በተገባ ነው። ለእነዚህ ሰዎች የሰው ነፍስ ምናቸው አይደለም። የሰው ነፍስ ከዶሮ ነፍስ ይበላጣል ብለውም አያምኑም። ለዚህም ነው ሰውን የሚያክል ፍጥረት ሲገድሉም ሲቀነጥሱም ዶሮ የማረድ ያህል ትርጉም የማይሰጣቸው ያለ። ዝርፊውያው እንደሆነም ያለን ጊዜ አጭር ነው ብለው ስለሚያምኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምን የሚያዳግት ስራ እየሰሩ ነው። በርግጥ፥ ጦርነቱም ቢሆን በተወሰነ መልኩ ለኦሮሚያ ፓርቲና ባለ-ስልጣናት ሰርግና ማላሽ ሆኖላቸዋል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ሀብት ያለ አንዳች ጠያቂና ቁጥጥር ወደ ኦሮሚያ ክልል በማሸሽ ረገድ በትግራይ ላይ የተፈጸመ ወረራ ትልቅ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል። በሃያ ዓመት ሊያደርጉት የማይችሉትን ነገር በሁለት ዓመት ውስጥ መዘረፍ የሚችሉትን ያህል ለመዝረፍ አስችላቸዋል። ወደ ምዕራቡ ዓለም እየሸሸ ያለ ዶላርና የተጀመረው ንግድም ነጮቹ የገንዘቡ ምንጭ አጥተውት ሳይሆን አገራቸው ላይ መጥቶ ኢኮኖሚያቸው ላይ እስከ ጠቀመ ድረስ ግድ ስለማይሰጣቸው ብቻ ነው። አሁን ወደ ወቅታዊው ጉዳያችን እንመለስ፥

ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጥዋት

ኢትዮጵያ፥ ቀደም ሲል በምንሊክ፣ በሃይለስላሴና በደርግ (መንግስቱ ሃያለማርያም) ዘመነ መንግስት እንዲሁም ከዚያ ቀደም ብለው በነበሩ የኢትዮጵያ ሰዎች በትግራይ ህዝብ ላይ ስትከተለውና ስትፈጽመው የመጣ ዘር የማጥፋት ወንጀል ቀጥሎ፥ ይሄው የድመትና የውሻ መብት በሚከበርበትና በሚጠበቅበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ እናቴ 7ኛ ንጉስ ትሆለህ ብላኛለች ብሎ በሚያምነው በዐቢይ አህመድ ዓሊ ፊተወራሪነት ኢትዮጵያ በግዛትዋ ውስጥ የሚኖር ህዝብ መታሰቢያ ላይኖረው ዘሩን ለማጥፋት ጎረቤት አገራትና መንግስታት በመጋበዝ የፈጸመችው ወረራ ተከትሎ በትግራይ ህዝብ ላይ በቀጣይነት እየፈጸመችው ያለና የሚገኝ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም የጦርና የዘር ማጥፋት ወንጀል ማለትም ትግራይ በሁሉም አቅጣጫ በመክበብ የትግራይ ህዝብ የእህልና የመድሃኒት እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችና የሰው ልጅ በህይወት ይኖር ዘንድ የሚያስፈልጉት ግብአቶች እንዳያገኝ በመከለከል እንድን ህዝብ እንደ ህዝብ የማብረስ ዘመቻዋ ዛሬም አጠናክራ እንደ ቀጠለችበት ይገኛል። ይህ ሁለት ዓመት ሊሞላው ሁለት ወራት የቀረው የግፍና የበደል ድርጊት ጅማሮው አሁን ባለበት መልክና ቅርፅ አልነበረም። ትግራይን በሁሉም አቅጣጫዎች ከበባ ውስጥ በማስገባት የትግራይ ህዝብ በርሀብና በብሽታ እንዲያልቅ የማድረግ ሴራ በዋናነት ኢትዮጵያ ቀደም ሲል በትግራይ ምድር ኋላም በሜዳዋ ላይ የገጠማት ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ሽንፈትና ኪሳራ ተከትሎ የመጣ ድርጊት ሲሆን ዓላማው ቀደም ሲል እንደ ተገለፀው የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ (ትግራዋይ የሚባል ደም ያለበት ሁሉ ኣንስት፣ ህጻናትና ሽማግሌዎችን ጨምሮ) ያለ አንዳች አድልዎና መገለል እንደ ቅጠል ረግፎ ላማየት ያለመ አረመኔያዊ ምክር ነው።     

የሃይማኖት መሪዎች ነኝ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የተለየ ግኙንነት አለን፣ የጌታ ነቢያቶችና መልዕክተኞች ነን ብለው የሚያምኑ ዳሩ ግን የሐሰት አባት ሰይጣን የሰለጠነባቸውና የንጹሐን ዜጎች ደም የተጠማ ክፉ መንፈስ የሚዘውራቸው የኢትዮጵያ ሰዎች በአደባባይ ሳይቀር የእግዚብሔር ስም እየጠሩ፥ ጌታ እንዳትፈራቸው ይልሃል! በላቸው ጨፍጭፋቸው አውድማቸው! በትግራይ ካህናትና አብያተ ክርስትያናት እንዲሁም እናቶችና ሴቶች የፈጸምከው ግፍና በደልም ቢሆን የጽድቅ ሃሳብ ነው! ደግሞም እንዳትደራደር ብሎሃል!  እህል ውሃ ቆልፈህ ያዝባቸው! እያሉ ሲያበረታቱትና ሲያጃጅሉት ዐቢይ አህመድ ዓሊም ዓይኑን ጨፍኖ አሜን እያለ በሚሰማው የምዋርተኞች ቃል ተወስዶ፥ አልደራደርም! ድርድር ብሎ ነገር የማይታሰብ ነው፣ አንገቴ ለካራ! ሲል ከርሞ ያሰማረው ሰራዊት በትግራይ መሬት ላይ ረግፎ ሬሳው ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሆኖ ሲያይ ደግሞ በዛችው ግፍ በተናገረባት ምላሱ ተመልሶ ከትግራይ ጋር ያለን ችግር በሰለማዊ መንገድ ለመፍታትና ለመደራደር ኮሚቴ አቋቁሜለሁ፣ በየትኛም ስፍራ በማንኛውም ሰዓት ለድርድር እቀመጣሉ! ሲል የሰጠው መንግስታዊ መግለጫ ሁላችን ሰምተነዋል። አሁንም ቢሆን ታድያ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ለውይይትና ለድርድር ዝግጁ ነኝ ሲል የሰማነው ወዶ ሳይሆን፥ ትግራይ ከካርታ ለመፋቅ የታጠቀው የጦር መሳሪያና ያሰለፈው የሰው ሃይል እንዲሁም ከጎረቤት አገራትና መንግስታት ያገኘው እርዳታ ተማምኖ በትግራይ ላይ የፈጸመው ወረራ ዓላማው ስለ ከሸፈበት፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ሽንፈትና ኪሳር ስለ ተከናነበ ከዚህ የተነሳም የመዋጋት አቅም ስለሌለው ብቻ ነው። አንድም፥ ዐቢይ አህመድ ዓሊ “በየትኛም ስፍራ በማንኛውም ሰዓት ለድርድር እቀመጣሉ!” ያለው ለትግራይ ብሎ ሳይሆን ይህን ካላደርገ ሌላ አማራጭ ሆነ ማምለጫ ስለሌለው ብቻ ነው። አገሪቱ ከመበታተን ህዝቦችዋም ከከፋ ዕልቂትና ጥፋት መታደግ የሚቻለው ኢትዮጵያ ከትግራይ ጋር ያላት ችግር በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ውጭ ሌላ አመራጭ ስለሌላት ነው።    

ዐቢይ አህመድ ዓሊ በህይወት መትረፍ የሚችለው አሁንም ከትግራይ ጋር ያለው ችግር በውይይትና በደርድር ለመፍታት ሰላማዊ መንገድ የተከተለ እንደሆነ ብቻ ነው። ከርሞ ጥጃ ዐቢይ አህመድ ይህን እያወቀ ነው እንግዲህ ራሽያ በዩክሬን ላይ የምትከተለውና የምትፈጽመው ያለ ወታደራዊ እርምጃ እንዲሁም ቻይና ታይዋንን በማስመልከት የምትሰጣቸው ያለ የሉዓላዊነት መንግስታዊ መግለጫዎች በማየትና በመስማት በኮፒ ፔስት ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርጋገው ያለ ከንቱ ሙከራዎች የተነሳ ነው ለሰላም እንቅፋት ሆኖ አገሪቱ ለከፋ ጥፋትና ውድመት (protracted military conflict) ለመማገድ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ የሚገኝ ያለ። ትግራዋይማ ለህልውናውና ለደህንነቱ ለክብሩና ለማንነቱ አራትና አምስት መንግስታት አሸምድምዶና አጥመልምሎ ይሄው ህልውናው አረጋግጦ ያደረ ብርቱና ታጋይ ህዝብ ነው። ቡራኬያቸው ሰጥተው ጦር መሳሪያ አታጥቀው የላኩት ሃያላንም ቢሆኑ ከትግራይ ጋር ጦርነት አያዋጣህም ብለንህ ነበር እስኪሉት ድረስ ትግራዋይ በትግሉና በመስዋዕትነቱ ጀግንነቱ በዓለም መድረክ ላይ ዳግም አስመክረዋል። ኢትዮጵያ ለውይይትና ለድርድር ዝግጁ የምትለው ያለችው ከሱዳን ወይም ከኬንያ መንግስት ሳይሆን ትናንት ሞተዋል፣ የሉም አልቀዋል እያልክ ስታባርቅና ስትሳለቅበት ከነበከው ከትግራዋይ ጋር ነው። ባይሆን አእምሮ ላለው ሰው የትግራዋይ የትግል መንፈስና ጀግንነት ሳያላምጥ አምኖ ለመቀበል ይህ በበቃው ነበር። 

ሲሰበር እያነከሰ እደራደራለሁ ዕረፍትና ፋታ ያገኘ ሲመስለው ደግሞ እዋጋለሁ እያለ ለሰላም እንቅፋት የሆነው ዐቢይ አህመድ ዓሊ ይህ የሚደርግበት ያለ ዋና ምክንያትዋ ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ችግሩ፥ ሽምግልናው በማን ይመራ፣ የት ቦታ ይካሄድ፣ መቼ ይጀምር የሚል ሳይሆን ከዚህ ሁሉ ሰበብና ምክንያት ጀርባ ያለ ምክንያት ሳይገባው አለቦታው የተቀመጠ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ከጥዋቱ 8 ሰዓት እደራደራለሁ ይላል 8፡30 ስራ ፈትቶ በሚመለከተው የቴሌቪዝን መስኮት ራሽያ በዩክሬን ላይ ይህን አደረገች፣ ቻይና በታይዋን ጉዳይ ላይ እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጠች የሚለው ዜና ሲያይና ሲሰማ ደግሞ ደግሞ 9 ሰዓት ላይ እኔስ ከማን አንሺ ነው?! በሚል ጨቅላነት ያየውና የሰማው ለመሆን በሚያደርገው ያለ ጥረት ምክንያት ነው።  ዐቢይ አህመድ ዓሊ ምክንያት እየፈጠረ ወጣ ገባ የሚል ያለው፥ እስቲ እኔ ደግሞ ይህችን የማርያፑልን ስልት ድጋሜ ልሞክራት በሚል ውዥንብር ስለ ተያዘና የደረሰበት ሽንፈትና ኪሳራ ለማካካስ አልሞ ዕድሌን ልሞክር በሚል ስሌት ነው የጦርነት ነጋሪት የሚጎስመስው ያለ። ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጥዋት! ይሉሃል ይሄ ነው።   

በነገራችን ላይ፥ የኢትዮጵያ ለድርድር መቀመጥ ፖለቲካዊ አንድምታው በሚገባ እንዲገባን ከተፈለገ መጀመሪያ የዐቢይ አህመድ ዓሊ ዓይነቱ ደካማዋ ዶሮ ጭራ የማታጣው ያልበሰለ የፖለቲካ ምክር ሊበራልን ይገባል። ይኸውም፥ የኢትዮጵያ ለድርድር መቀመጥ ከምንም በላይ በጉልህ የሚያሳየው ነገር ቢኖር አገሪቱ የተከናነበችው ወታደራዊና ፖለቲካዊ  ሽንፈትና ውድቀት ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ አቅም ቢኖራት ኖሮ ለድርድር የምትቀመጥበት ምንም ምክንያት የላትም። በተመሳሳይ ይህን ካላደረገች (ለድርድር ካልተቀመጠች) ደግሞ እንደማትተርፍ ታውቃለች። በተሳሳተ ስሌት፣ በዓለማችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ጎረቤት አገራትና መንግስታት በማስተባበር የእኔ በምትለው ግዛት ውስጥ የሚኖር ህዝብ ላይ የፈፀመችው ወራራ በዚህ ሁኔታ ይጠናቀቃል ብሎ የገመተ ኢትዮጵያዊ በኩራዝም ቢሆን ተፈልጎ አይገኝም፤ ይኖራል ተብሎም አይታመንም። እንደ ኢትዮጵያና ግብረ አብሮችዋ እቅድና ምኞት በትግራይ ላይ የተፈፀመ ወረራ ግቡና ዓላማው የትግራይ ህዝብ መታሰቢያ ላይኖረው ስመ ዝክሩ ፈጽሞ ማጥፋትና ትግራይን ከካርታ መፋቅ ነበር የነበረው። ይህ ደግሞ አልሆነም። ያልሆነበት ምክንያትም ደግሞ ሁሉም እንደሚያውቀው ምህረት የማታውቅ ነፍሰ በላዋ ኢትዮጵያ ምህረት ስላደርገችልን ሳይሆን የትግል ምልክት የሆነው የአሸናፊነትም ታሪክ ያለው ትግራዋይ ትጥቅና ስንቁን ከጠላት እየማረከ ሰራዊት ፈጥሮ ለህልውናው በደረገው ትግልና በከፈለው የህይወት መስዋዕትነት ነው። በመሆኑም፥ የኢትዮጵያ ለድርድር መቀመጥ ከምንም በላይ አገሪቱ ህልውናዋ ለማስቀጠል ያለመ ለመሆኑ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል።  

  • ወራሪው ሃይል እንዳቀደው ሳይሆንለትና ሳይሳካለት ቀርቶ/ከሽፎበት ችግሬን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት እወዳለሁ ማለት በአማርኛ የተረጎምነው እንደሆነ ሽንፈት የሚል ሃያለ ቃል በአጭሩ ይገልጽልናል።  
  • እንደ አማራና እንደ ሶማሌ እንደ ወለጋና እንደ ጋምቤላ በሁለት ሳምንት ውስጥ የሚገደል ገድዬ የሚሾም ሹሜ እወጣለሁ ብሎ ምሎና ተገዝቶ የገባ ሃይል በግፍ የረገጣት የትግራይ መሬት መቃብሩ ሆናበት በህይወት የተረፈ ደግሞ በምርኮ ሰብስበነው ስናበቃ የሴት ቀሚስ ለብሶና መሳሪያውን እየሸጠ የፈረጠጠ ሰራዊትና አዲስ ምልምል ሰብስቦ ዘራፍ ሲል ለባለ አእምሮ መልዕክቱ ግልጽ ነው። አሁንም ይህ ዐረፍተ ነገር በአጭር ቃል ያስቀመጥነው እንደሆነ ወታደራዊ ሽንፈትና ኪሳራ ይባላል። ይህ ደግሞ ተጋሩ ያቀመስዋት እየተባለ በኢትዮጵያ የክሽፈት ታሪክ ውስጥ እንዲሁ እንደወረደ ሲነገር የኖራል።

መፍትሔው?

ቅድም ኢልና ዝረኣናዮ ናይ ዐቢይ አህመድ ዓሊ ኮን ደኾን ይኾነለይ ዝዓይነቱ ፈተነታት መፍትሕኡ እንታይ ‘ዩ? ንዝብል ሕቶ ሕፅር ዝበለ ናይ መፍትሒ ሃሳብ ከካፍል። ኩልና ከም ንፈልጦን ከም ንርድኦን ውፅኢታዊ ዝኾነ ውሳነ ንምግባር ዘኽእል ከይዲ (decision-making process) ብዝምከት ተዓጻጻፋይ ምዃን አድላይን ውሳኒን ‘ዩ። ከም ስትራቴጂ ግን፥ ወታደራዊ ኾነ ፖለቲካዊ መሪሕነት ትግራይ ክኽተሎን ተግባራዊ ክገብሮን ዘለዎ ኣንፈት ሓፂርን ግልጽን ዝኾነ ቅዋም/መትከል ዝሓዘ ክኸውን ይግባእ። እዚ ማለት፥ ድሌትን ራዕይን መሪሕነት ትግራይ ሽትኡ ንኽወቅዕ እግሪ እግሪ ኢትዮጵያ እናረኣየ እናሰዓበን ዘስተኻኽሎን ዘመዓራርዮን ነገር ዘይኮነ ኢትዮጵያ ናብ ድሌታ ተብል ድሌታ ‘ውን ትግበር ረብሓታት ትግራይ ዝሕለውሉ መንገዲ ከነፅር ክኽእል ኣለዎ ዝብል እምነት ኣለኒ። ጉዳይ ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ ብዝመረፀቶ መንገዲ ገጢምካ ኣብ ዝሓፀረ ጊዜ ዕልባት ክግበሮ ይግባእ ክበሃል ከሎ፥ ከምቲ ሕዚ ሰበ ስልጣናት ኢትዮጵያ ዝገብርዎ ዘለዉ እትው ውፅእ ዝዓይነቱ ፖለቲካዊ ሸፈጥ እናሰዓብና ምስኣቶም ነኹድድ ማለት ኣይኮነን። ጦርነት መሪፃ ጦርነት ክትከፍተልና ኸላ ጦርነት፤ ብምርጫኣ ኣተኣናጊድና ምስ ሰበርናያ ድማ ፀገመይ ብምይይጥ ንምፍታሕ ድልዊ ኣየ! እናበለን ብማንካን ብኢዳን እናገብረት ትፈጥሮም ዘላ ማሕልኻታት መሪሕነት ትግራይ ደው ከብሎ ክኽእል ኣለዎ። መሪሕነት ትግራይ፥ ኢትዮጵያ ነዚ ሕዚ ትገበሮ ዘላ ወደኽደኽ ብሕዚኡ ገደብ ክገብረሉ ኣለዎ። እዚኣ ክገብር ዝኽእል ድማ ወታደራዊ ስጉምቲ ኣጣናኺሩ ብምቕፃል ጥራሕ ‘ያ። ንረብሓታትና ብናትና ተርም ተኸይድና ድኣምበር ንኢትዮጵያ እናተፀበና እንገብሮን እንኸዶን ጉዕዞ ናዓና ኣይጠቕመናን ‘ዩ። ንኢትዮጵያ ዝርድኣ ቛንቛ ዋላ ሓሙሽተ ሰባት ንትረፍ ተዓጢቕና ምቅላስ ተኾይኑ ካሊእ መማረፂ ክህልወና ስለ ዘይኽእል ክንገብራ ኣለና። እቲ ናይ ምይይጥ ዝብሃል መድረኽ ‘ውን ተኾነ ላዕለዋይ ኢድ ሃልዮና ብዓወት ክንወፅእ እንኽእል ከምታ ክሳብ ሕዚ ዝመፃናያ ወታደራዊ ዓወታትና ብምዕቃብ ስለ ዝኾነ ሕዚ ‘ውን ወታደራዊ ዓወታትና ክንዕቅብን ክንቅፅለሉን ይግባእ። ኢትዮጵያ ተግብሮ ዘላ ንኽትገብር ዘገድዳ ዘሎ እቲ ሓደ ምኽንያት፥ ዕድል ተሂብናያን ተረኺባን ክንዲ ዝኸኣለቶ ዘበለ ጉድኣት ድሕሪ ምብፃሕ ኣብቲ ናይ ምይይጥ መድረኽ ድማ ላዕለዋይ ኢድ ረኺባ ብናታ ድሌት ክተኽደና ስለ ትደልይ ጥራሕ ‘ዩ።

ምስዚ ዝተተሓዘ፥ መሪሕነት ትግራይ ፕሮኣክቲቭ ኮይኑ ዕማሙ ንኽዋፃእ ሓጋዚ ክኸውን ይኽእል ‘ዩ ኢለ ዝኣምኖ ዝምልክት ይኸውን። እዚ ድማ፥ ብዝተፈላለዩ መንገድታት (ብቐጥታ ኾነ ብተዘዋዋሪ፣ ብመልክዕ ፕሮፓጋንዳ ኾነ ኻሊእ ዝንገር) ብቐንዱ ካብ ኣፍ ሰበ ስልጣናት ኢትዮጵያ ከምኡ ድማ ተኸፈልቲ ናይቲ ስርዓት ዝኾኑ ግለሰባትን ናይ ሚድያ ተቋማትን ዝንገሩ ሓበሬታታት ህልው ኩነታት ናይቲ ኣብ ስልጣን ዘሎ ሓይሊ ዝገልፁ ብምኻኖም ብቑልዕ ዝርከብ ሓበሬታታት ሓበሬታ ጥራሕ ካብ ምኻን ሓሊፉ ብስሩዕ ፕሮሰስ ተገይሮም አካል ናይቲ ወታደራዊን ፖለቲካውን ቃልሲ ዝኾኑሉ ኣሰራርሓ ብዝበለፀ ተጠናኺሩ ንኽቕፅል ክሕብር እደሊ።

ከርሞ ጥጃ ዐቢይ አህመድ ዓሊን ማመን ነፋስን ማከተል ነውና አስጢምካ ሓዝ!

By aiga